Get Mystery Box with random crypto!

#ይቺ_ናት_ኢትዮጵያ !! የዘር ፓለቲካ ዘልቆ የሚታይባት ወንድማማችነታችን ተረስቶ ከአንድ እ | all in one hawasa

#ይቺ_ናት_ኢትዮጵያ !!

የዘር ፓለቲካ ዘልቆ የሚታይባት ወንድማማችነታችን ተረስቶ ከአንድ እናት ሀገር ኢትዮጵያ መፈጠራችንን እረስተን ፣ፈርሀ እግዚአብሔርን ዘንግተን መገዳደላችንን ቀጥለናል አሁንም አለን ።በዚሁ ከቀጠልን ግን ኢትዮጵያስ የምትባል ሀገር ትኖር ይሆን ?

መቼ ይሆን ግን ማብቂያው ?
መፅሐፍ አገብጬ ፣አባቶቼን ጠይቄ፣ ጎግል ጎልጉዬ ...መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ነው ።
መቼ ነው ፖለቲከኞች ህዝባቸውን ለእኩይ ተግባር መጠቀማቸውን የሚያቆሙት ? መቼ ነው የነሱን ልጅ በሞቀ ቤት በአውሮፓ እና አሜሪካ አስቀምጦ እዚህ ያለውን ባዶ ሆዱን የሚያድረውን ወጣት መጠቀሙን የሚያቆመው ? መቼ ነው አንድነታችን የሚመለሰው ? መቼ ነው ወጣቱ የእናትን ጓዳ ሊጥ መድፋት ትቶ ለእናቱ ንፁህ እንጀራ የሚያመጣው ? መቼ ነው ...? መቼ ነው ....? መልስ ያላገኘሁላቸው ጥያቄዎች ።

አስታውሳለሁ በአንድ ወቅት የአማርኛ ቋንቋ መምህራችን እንዲህ ብላን ነበር ''አንድ አዛውንት ሲሞት አንድ ቤተመፃህፍት እንደተቃጠለ ይቆጠራል'' ... እና እስካሁን ስንት ቤተመፃህፍት ፣ስንት የእውቀት አባቶችን አተን ይሆን ?

ከሀገራችን ሰንደቅዓላማ ይልቅ ሰባራ ሰንደቅ ከልካይ ሳይኖራቸው ሲውለበለቡ አያለሁ ያሳዝናል ኢትዮጵያን መርሳታችን ያሳዝነኛል።
''እዛ ጋር ጤፍ ቆጠራ
እዚህ ጋር ቃል ምንዘራ
ሀገር ምድሩ ባንቺ እየተጠራ''

ስኬት ያለ ውድቀት ማግኘት እንደማይቻለው ይህም ግዜ አልፎ የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንደምናይ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም የንፁሀን ነፍስ ወደ ፈጣሪዋ አብዝታ ስለምትጮህ ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና ።

''የአሜሪካው ከመጣ አለን መመለሻ
የሱዳኑ ቢመጣ አለን መመለሻ
እኛን ያስቸገረን ሀበሻ ላበሻ''

ከፊት ነበርን አሁን ግን ከሁሉም ኃላ ቀርተናል ወደ ቀድሞ አንድነታችን እና ስልጣኔአችን የሚመልሰን የኢትዮጵያ ሙሴን ፈጣሪ እንደሚልከልን አምናለሁ ።

''ሰላም ፣አንድነት እና ፍቅር ፈጣሪ አብዝቶ እንዲያድለን ከልብ እመኛለሁ ።''
https://t.me/fetazonee