Get Mystery Box with random crypto!

#ATTENTION ወልድያ ! ከወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ቤት ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ በ | all in one hawasa

#ATTENTION

ወልድያ !

ከወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ቤት ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ ክልክለዎችን አስተላለፈ።

የፀጥታ ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ  ክልከላዎችን ማስቀመጡ ይታወሳል።

ሆኖም ነባራዊ ሁኔታ በማየት ተጨማሪ ክልከላዎች በማስፈለጉ ከነገ መስከረም 22 2015 ዓ.ም ጀምሮ  የሚተገበሩ ተጨማሪ ዉሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል።

በዚህ መሰረት :-

1. ከ ነገ መስከረም 22  ቀን ጀምሮ ጫት ወደ ከተማዋ ማስገባት በጥብቅ ተከልክሏል።

2. ከነገ ጀምሮ ጫት መቃም ሆነ ማስቃም በጥብቅ ተከልክሏል።

3. ከነገ ጀምሮ የጎዳና ላይ ቁማር (ቢንጎ የመሳሰሉትን) መጫወት ተከልክሏል።

ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ጨምሮ ከዚህ በፊት የተላለፉ ዉሳኔዎችን ማንኛውም አካል የማክበርና ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ አለበት የተባለ ሲሆን ውሳኔዎቹን የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

መረጃው ከከተማው ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው
@fetazonee