Get Mystery Box with random crypto!

መፈንቅለ መንግስት - በቡርኪናፋሶ ! ' መፈንቅለ መንግሥት ' በማደረግ ስልጣን የያዙት የቡርኪና | all in one hawasa

መፈንቅለ መንግስት - በቡርኪናፋሶ !

" መፈንቅለ መንግሥት " በማደረግ ስልጣን የያዙት የቡርኪናፋሶ መሪ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገባቸው።

የቡርኪናፋሶ የጦር መኮንኖች ትላንት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ዳምቢባ ከሥልጣን መወገዳቸውን አስታውቀዋል።

የቡድኑ መሪ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ የሚባሉ ሲሆን ባሰሙት ንግግር የወታደራዊ መሪ ሌትናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከመሪነት የተወገዱት፣ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን አማጺያንን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው። ላልተወሰነ ጊዜ ሁሉም ድንበሮች ዝግ እንደሚሆኑና የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መከልከሉን አሳውቀዋል።

አሁን ከሥልጣን መወገዳቸው የተገለጸው ዳምቢባ የሚመሩት ቡድን ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ነበር በሕዝብ የተመረጠውን አስተዳደር በመፈንቅለ መንግሥት ገልብጦ ወደ ሥልጣን የመጣው። በወቅቱ ወታደራዊ ቡድኑ መንግሥት የአማፂያንን ጥቃት ማስቆም አልቻለም በሚል ነበር መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው።

ትናንት ምሽት ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ አብዛኞቹ ፊታቸው የተሸፈነ የታጠቁ ወታደሮች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የቡድኑ መሪ ናቸው በተባሉት ትራኦሬ የተፈረመ መግለጫ አቅርበዋል።  
መግለጫው ፤ " እየተባባሰ የሚሄድ ችግር በገጠመን ጊዜ ዳምቢባ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሞክረናል፤ ነገር ግን የዳምቢባ ተግባር ለማድረግ ካቀድነው ውጪ በመሆኑ አሁን ከሥልጣን እንዲወገድ ወስነናል " ብሏል።

ከዚህ በኋላም በመላዋ አገሪቱ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን፣ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
https://t.me/fetazonee