Get Mystery Box with random crypto!

‹‹የእናቴ አገር ኮኔክቲከት አሜሪካ ነው፡›› ‹‹እዚያ ብዙ ትቆያላችሁ?›› ‹‹እናትና አባቴ ቢ | 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

‹‹የእናቴ አገር ኮኔክቲከት አሜሪካ ነው፡››

‹‹እዚያ ብዙ ትቆያላችሁ?››
‹‹እናትና አባቴ ቢያንስ ጦርነቱ እስኪያልቅ ይቆያሉ፡፡ ምናልባትም
አይመለሱም ይሆናል››

‹‹አንቺ ግን መሄድ አትፈልጊም››

«አዎ አልፈልግም›› አለች ፈርጠም ብላ ‹‹እኔ እዚህ ቆይቼ ለአገሬ መዋጋት እፈልግ ነበር፡፡ ፋሺዝም አስከፊ በመሆኑ እሱን የሚከላከል ጦርነት
ደግሞ ፍትሃዊ ስለሆነ በዚህ ጦርነት ውስጥ የራሴን አስተዋጽኦ ማድረግ
ፈልጋለሁ……...>> ስለ ስፓኒሽ የእርስ በእርስ ጦርነት ማውራቷን ቀጠለች
ሄሪ ግን በግማሽ ልቡ ነው የሚሰማት፡፡ አንድ ልብ የሚሰቅል ነገር በሃሳቡ
ስለመጣ እንዳይታወቅበት ፊቱ ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዳይታይ
መጠንቀቅ ይኖርበታል፡ የመጣበት ሀሳብ ሰዎች ጦርነት ተቀስቅሶ ሲሰደዱ
ውድ ጌጣ ጌጦቻቸውን አገራቸው ጥለው አይመጡም› የሚል ነበር፡

ነገሩ እንዲህ ነው: ወራሪው ጦር እየገሰገሰ ሲመጣ ገበሬዎች ከብቶቻቸውን እየነዱ ይሰደዳሉ፡ ይሁዲዎች ከናዚ ጀርመን ተሰድደው የወጡት የወርቅ ሳንቲሞቻቸውን በየልብሶቻቸው ሰፍተው ነው፡ የ1917 የሩሲያ አብዮት ሲፈነዳ እንደ ልዕልት ላቪኒያ ያሉ የሩሲያ ባላባቶችና መኳንንት በመላው የአውሮፓ ከተሞች የእንቁላል ቅርጽ ያለውን ውድ የከበረ ሉሎቻቸውን በእጃቸው እንደያዙ ነበር፡

ጌታ ኦክሰንፎርድም ቢሆኑ ወደ አገራቸው እንደማይመለሱ ሳያስቡበት
አይቀሩም:፡ በተጨማሪም የእንግሊዝ መንግስት ባለጸጎች ከአገር ሲወጡ
ገንዘባቸውን እንዳያሸሹ የውጭ ምንዛሬ ቁጥጥር ህግ አውጥቷል፡
የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ጥለው የመጡትን ንብረት ባለበት ሁኔታ መልሰው
እንደማያገኙት አውቋል፡፡ ታዲያ ከአገር የወጡት በእጅ ሊያዝ የሚችለውን
ውድ ንብረት በሙሉ ይዘው ነው፡፡

በእርግጥ ውድ ጌጣጌጥ በሻንጣ ይዞ መጓዝ አስተማማኝ አይደለም:
በአሁን ጊዜ አስተማማኝ የሆነው የቱ ነው? በፖስታ ቤት መላክ ወይስ
በተበቃይ መንግስት እንዲወረስ ትቶ መምጣት ወይስ በወራሪ ጦር መዘረፍ?

የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ውድ ጌጣጌጦችን ይዘው ነው የመጡት በተለይም ዴልሂ ስዊት› የተባለውን ጌጣ ጌጣቸውን፡፡

ሄሪ ይህን ሲያስብ ትንፋሽ አጠረው፡ ዴልሂ ስዊት ከእመቤት ኦክሰንፎርድ የጌጣጌጥ ስብስቦች ውስጥ ምርጡና ውዱ ጌጣጌጥ ነው፡ ይህ
ጌጣጌጥ ከአልማዝና ከወርቅ የተሰራ ሲሆን የአንገት ሃብል፣ አብሮ የሚሄድ የጆሮ ጌጥና አምባር ያካተተ ኮምፕሌት የሆነ ጌጣጌጥ ነው፡፡ ጌጣጌጦቹ ከበርማ የተገኙ ሲሆን በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን በህንድ አገረ ገዥ የነበረ አንድ የእንግሊዝ ጄነራል ነው ያመጣው፡፡ ዴልሂ ስዊት ሩብ
ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ ያወጣል ተብሎ ይታመናል፡ ይህ ገንዘብ
ደግሞ አንድን ሰው ዕድሜውን በሙሉ ያኖረዋል፡

ይህም ጌጣጌጥ እዚህ አይሮፕላን ላይ ነው ያለው፡፡

ማንም ልምድ ያለው መንታፊ ደግሞ አይሮፕላን ወይም መርከብ ላይ
ለመስረቅ አይሞክርም፡፡ ምክንያቱም የተጠርጣሪዎች ቁጥር ጥቂት ነውና ይባስ ብሎ ደግሞ ሄሪ አሜሪካዊ ነኝ ብሎ በሃሰት ፓስፖርት እየተጓዘ ነው በእንግሊዝ ፍርድ ቤት የሚፈለግበትን የዋስ ገንዘብም አልከፈለም
የተቀመጠውም ፖሊስ አጠገብ ነው፡፡ ስለዚህ የዴልሂ ስዊት ጌጣጌጥ ላይ
እጅን ማሳረፍ እብደት በመሆኑ ማሰቡ እንኳን በፍርሃት አርዶታል፡

ግን ደግሞ ሌላ ጊዜ እንደዚህ አይነት ዕድል ላይገጥመው ይችላል
ወዲያው ውሃ ውስጥ እየሰጠመ ያለ ሰው አየር ለማግኘት እንደሚጎበስተው
ሁሉ እነዚህን እንቁዎች በእጁ ማስገባት ክፉኛ ተመኘ፡፡

ምናልባትም ጌጣጌጦቹን ከግማሽ ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ሊሸጣቸው እንደማይችል አውቋል፡፡ ምናልባትም ሃያ አምስት ሺህ ፓውንድ እንኳን
ቢሽጣቸው ከአንድ መቶ ሺህ ዶላር በላይ ያገኛል፡ ይህም ገንዘብ እድሜውን
ሙሉ ሊያኖረው እንደሚችል ገምቷል፡፡

በርካታ ገንዘብ እጁ እንደሚገባ ሲያስብ አፉ ምራቅ ሞላ፡
ጌጣጌጡን ለመስረቅ ወሰነ፡፡
ሲሰርቅ ከተያዘ አለቀለት፡ ሆኖም እሱ ሁሌም በዕድል ከአደጋ እንዳመለጠ ነው፡፡

ይቀጥላል