Get Mystery Box with random crypto!

#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ሄ | 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ሄሪ ፍርድ ቤቱ የጣለበትን የዋስ ክፍያ ሳያስይዝ፣ በሃሰት ፓስፖርትና
ስም ተጠቅሞ አሜሪካዊ ነኝ እያለ እንዳልመጣ አሁን ሌባ መሆኑን የምታውቅ ልክ በስሙ ስትጠራው አመዱ ቡን አለ፡፡

ካገር ያሰደደው አስከፊ ነገር ሁሉ ዓይኑ ላይ ድቅን አለበት፡ የፍርድ ቤቱ እሰጥ አገባ፣ እስር ቤት የቆየባቸው ቀናትና የግዴታ ውትድርና
አገልግሎት፡

በኋላ ግን ዕድለኛነቱ ትዝ አለውና ፈገግ አለ፡፡

ሄሪ ልጅቷ ግራ እንደገባት አየ፡፡ ስሟን ለስታወስ ሞከረና መጣለት
እመቤት ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ፡

ልጅቷ በመገረም አፈጠጠችበት።

‹‹ስሜ ሄሪ ቫንዴርፖስት ነው›› አላት፤ ካንቺ ይልቅ እኔ የተሻለ አስታውሳለሁ፡ አንቺ ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ አይደለሽም? እንዴነት ነሽ?››

‹‹ደህና ነኝ›› አለች በድንጋጤ ደንዝዛ
ለሰላምታ እጁን ሲዘረጋላት ልትጨብጠው እጇን ስትሰድ መጨበጡን
ትቶ ‹‹ከዚህ በፊት ፖሊስ ጣቢያ እንዳላየሽኝ ሁኚ፧ እኔም እንዲሁ አደርጋለሁ›› አላት፡፡

ግራ መጋባቷ ሲለቃት ፈገግ አለች፡፡ የነገራት ገባትና ‹‹እንዴ ምን ነካኝ
ሄሪ ቫንዴርፖስት›› አለች፡

ሄሪ አሁን ቀለል አለው፡፡ በዓለም ላይ መቼም እንደኔ እድለኛ የለም አለ በሆዱ፡፡

ማርጋሬትም ‹የሆኖ ሆኖ የት ነበር የምንተዋወቀው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አንድ ዳንስ ቤት የተገናኘን ይመስለኛል›› አላት፡፡

‹‹ልክ ነው እዚያ ነው የማውቅህ›› አለች
በዚህ ጊዜ ፈገግ አለ፡፡
የሴራው ተካፋይ አደረጋት፡፡

በመቀጠልም ‹‹ቤተሰቦቼን ላስተዋውቅህ›› አለችና ‹‹እማማ አባባ ሚስተር ቫንዴርፖስትን ተዋወቁት ከ. . . ስትል ከአፏ ነጥቆ ‹‹ከአሜሪካ
ፔንሲልቫኒያ›› አለና ንግግሯን ጨረሰላት፡፡
ፔንሲልቫንያ የሚለው ቃል ካፉ ሲወጣ ዕድሉን ረገመ፡፡ ፔንሲልቫኒያ የት እንደሚገኝ አያውቅም፡፡

‹‹ይቺ እናቴ ናት፤ ይሄ አባቴ፤ ይሄ ደግሞ ወንድሜ ነው›› በማለት በማዕረግ ስማቸው አስተዋወቀችው:: ሄሪ ሁሉንም በዝና ያውቃቸዋል፡ ሄሪ የማርጋሬትን ቤተሰቦች ልባዊ በሆነ በአሜሪካውያን ተግባቢነት ባህሪ ሰላምታ
ሰጣቸው፡፡


ሎርድ ኦክሰንፎርድ እንደልማዳቸው በትዕቢት ተጀንነው ተኮፍሰዋል:
ሄሪ እናቷን ማነጋገር መረጠና ‹‹እንደም ነዎት የኔ፧ እመቤት? የተሰማራሁት
በእንቁ ጌጣጌጥ ንግድ ላይ ነው፤ እርስዎም በዓለም ላይ አለ የሚባል የዕንቁ ስብስብ እንዳለዎት ሰምቻለሁ›› አላቸው፡፡

‹‹እውነት ነው፤ ዕንቁ እወዳለሁ›› አሉት፡፡

ሄሪ የእመቤት ኦክሰንፎርድን የአሜሪካውያን የአነጋገር ቅላጼ ሲሰማ ቀልቡ ተገፈፈ፡፡ ስለእኚህ እመቤት መጽሔት ላይ አንብቧል፡፡ሴትየዋ እንግሊዛዊት ይመስሉት ነበር፡፡ መጽሔቶች ላይ ስለ ኦክሰንፎርድ የተጻፈው ሃሜት ትዝ አለው፡፡ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ በጦርነት ምክንያት እህል መሸጥ
ባለመቻሉ ምክንያት ከርስታቸው የሚያገኙት ገቢ በመቆሙ ኪሳራ ላይ መውደቁን፣ ሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት የቀራቸውን ሀብት ይዘው በጣሊያንና በፈረንሳይ መኖር እንደጀመሩ፣ ነገር ግን ሎርድ ኦክሰንፎርድ አንድ የአሜሪካ
የባንክ ባለንብረት ቤተሰብ ልጅ በማግባታቸው የተንደላቀቀ ኑሮዋቸው እንዳልተቋረጠባቸው አንብቧል፡፡ ስለዚህ እኚህን አሜሪካዊ ሴት ለማታለል
ከመነሳቱ በፊት መጠንቀቅ እንዳለበት ተረዳ፤ ቢያንስ ለሚቀጥሉት የበረራ ሰዓቶች፡፡

ለእኚህ ሴት መልካም ባህሪ ማሳየት እንዳለበት አውቋል፡ መቼም
ወይዘሮዋ ከመልከ መልካም ወጣት የሚጎርፍላቸውን የሙገሳ ቃላት የሚጠሉ አይመስሉም፡፡ አንገታቸው ላይ የተንጠለጠለውን ውድ የአንገት ጌጥ ጠጋ ብሎ አየው፡፡ እውነተኛ ጌጥ ነው፡፡ የፈረንሳይ አገር ስሪት ሲሆን
በ1880 ዓ.ም የተሰራ መሆኑን ገመተ፡፡

‹‹የአንገት ጌጥዎ የተሰራው በኦስካር ሚኒን አይደለም?›› ሲል
ጠየቃቸው እመቤቲቱን፡

‹‹ልክ ብለሃል››

‹‹በጣም ግሩም ጌጥ ነው››

‹‹አመሰግናለሁ፡፡››

እመቤት ኦክሰንፎርድ ቆንጆ ናቸው፡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ለምን
እንዳገቧቸው አወቀ፡፡ ነገር ግን ሴትየዋ ለምን እሳቸውን እንዳገቧቸው ሊገባው አልቻለም፤ ምናልባትም ከሃያ ዓመት በፊት ሰውየው የሴትየዋን ልብ መስረቅ ችለው ይሆናል፡

‹‹ፊላደልፊያ ውስጥ
የማውቃቸው መሰለኝ፤ የኔ ቤተሰቦች ስታንፎርድ ኮኔክቲከት ውስጥ ነው የሚኖሩትን የቫንዴርፖስት ቤተሰብን
የሚኖሩት›› አሉት እመቤት ኦክሰንፎርድ

‹‹በውነት!›› አለ ሄሪ የተደነቀ ይመስል፡፡ አሁንም ስለፊላደልፊያ ነው የሚያስበው ቅድም አገሬ ፊላደልፊያ ነው ወይስ ፔንሲልቫኒያ ነው ያለው? ጠፋበት፡፡ ወይ የተለያየ ስም ያለው አንድ ዓይነት ቦታ ይሁን ወይም አይሁን የሚያውቀው ነገር የለም፡፡

ትንሹ ልጅ ‹‹እኔ ፔርሲ እባላለሁ›› አለው፡፡

‹‹እኔ ሄሪ እባላለሁ›› አለው ሄሪም፡፡ ፔርሲ የራሱ የማዕረግ ስም
አለው የባላባት ዘር ስለሆነ፡፡ ይህን የማዕረግ ስም አባቱ እስኪሞት ይዞ
ይቆይና ከአባቱ ሞት በኋላ ሎርድ› የተባለውን የማዕረግ ስም ይወርሳል፡፡እነዚህ ሰዎች በማዕረግ ስማቸው ይኮራሉ፡፡ ፔርሲ ግን ለየት ይላል፡ በማዕረግ ስሙ መጠራት እንደማይፈልግ ለሄሪ ነግሮታል፡

ሄሪ ተቀመጠ፡፡ ማርጋሬት አጠገቡ ስለተቀመጠች ሌሎች ሳይሰሙ
ሊያናግራት እንደሚችል ተረድቷል፡፡ አይሮፕላኑ ጸጥ ረጭ ብሏል፡፡ ሁሉም ሰው በአግራሞት አይሮፕላኑን ይቃኛል፡፡

ሄሪ ዘና ለማለት ሞከረ፡፡ ጉዞው ውጥረት የበዛበት ሊሆን እንደሚችል አውቋል፡ ማርጋሬት እውነተኛ ማንነቱን ስላወቀች መጠነኛ ችግር ይገጥመው ይሆናል፡፡ ያቀረበላትን ሃሳብ የተቀበለች ቢሆንም ሀሳቧን
ልትለውጥ ወይም አፏ ሊያመልጣት ይችላል አምርረው ካልጠየቁት የአሜሪካን አገርን ኬላ ማለፍ አያቅተውም፡: ነገር ግን አሜሪካዊነቱን
ከተጠራጠሩትና አጥብቀው ከመረመሩት በሃሰት ፓስፖርት እንደሚሄድ
ያውቁበትና አለቀለት ማለት ነው፡

አንድ ሌላ ተሳፋሪ ሄሪ ፊት ለፊት ያለው መቀመጫ ላይ ተቀመጠ፡፡
ሰውየው ረጅም ሲሆን ራሱ ላይ ኮፍያ ደፍቷል። የለበሰው ሱፍ ልብስ
በጊዜው አሪፍ ልብስ ነበር፡ አሁን ግን ጊዜው አልፎበታል ጫማው ያረጀ
ሲሆን ክራቫቱ ካንገቱ ላይ ሳይወርድ አስር ዓመት የሞላው ይመስላል፡
ሰውየው ፖሊስ ይመስላል - ነጭ ለባሽ ፖሊስ፡፡

ሄሪ ከአይሮፕላኑ ወጥቶ መሄድ እንደሚችል ያውቃል፤ ማንም ተው
ሊለው አይችልም፤ ከአይሮፕላኑ መውጣት ከዚያም መጥፋት፡፡

ነገር ግን ለጉዞው የከፈለው 90 ፓውንድ አሳዘነው፡ ከዚያም በላይ ሌላ
የጉዞ ተራ ለማግኘት ሳምንታት ሊጠብቅ ይችላል፡፡ በዚያ መሃል ቢያዝስ!?

ሌላ ሃሳብ መጣለት፤ እንግሊዝ አገር እየተሽሎከለከ መኖር፡፡ ወዲያው ይህን ሀሳብ ከአዕምሮው አወጣው፡፡ በጦርነት ወቅት አገር ላገር መንከራተት ደግ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የውጭ አገር ሰላይ ካለ ብሎ ሲያማትር ይውላል፡፡ ከዚያም በላይ ደግሞ የስደተኛ ኑሮ ቀላል አይደለም፡፡ በየቀኑ
የተለያየ ሆቴል ማደር፤ ፖሊስ ሲመጣ መደበቅና ሁልጊዜ መንከራተት፡

ፊት ለፊት የተቀመጠው ሰው ፖሊስ ቢሆንም እሱን ሊፈልግ እንዳልመጣ አውቋል፡ ምክንያቱም ሰውየው ተመቻችቶ ተቀምጦ ጉዞውን
ይጠብቃል፡ ለጊዜው የጎን ውጋት የሆነችበት ማርጋሬት ናት፡፡