Get Mystery Box with random crypto!

የሩሲያና የቻይንን 50 ሺህ ወታደሮች የሚሳተፉበት “ቮስቶክ 2022” የጦር ልምምድ እየተካሄደ ነው | Feta Daily Press

የሩሲያና የቻይንን 50 ሺህ ወታደሮች የሚሳተፉበት “ቮስቶክ 2022” የጦር ልምምድ እየተካሄደ ነው

በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ግዙፉ ቮስቶክ 2022 የጦር ልምምድ በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል።

ቮስቶክ 2022 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ ከዛሬ ጀምሮ ለ7 ቀናት በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ እና በጃፓን ባህር ላይ የሚካሄድ መሆኑ ተነግሯል።

በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ አዘጋጇ ሩሲያን ጨምሮ ቻይና፣ ቤላሩስ፣ ታጃኪስታን፣ ህንድ እና ሞንጎሊያን ጨምሮ በድምሩ 14 ሀገራት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከሀገራቱ የተውጣጡ 50 ሺህ ወታደሮች በልምምዱ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ከ5000 በላይ የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሏል።