Get Mystery Box with random crypto!

FENOTE MIND SET

የቴሌግራም ቻናል አርማ fenotemindset — FENOTE MIND SET F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fenotemindset — FENOTE MIND SET
የሰርጥ አድራሻ: @fenotemindset
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 524
የሰርጥ መግለጫ

ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ
📖 አነቃቂ ፣ አስተማሪ ጽሑፎችን ንግግሮችን በተከታታይ እናቀርብላችኋለን

ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ጥቆማ ወዘተ..
ካሎት እንዲሁም ፕሮሞሽን ለማሠራት ከፈለጉ
@Mindset123_bot ላይ ይላኩልን።
እናመሠግናለን ።

https://telegram.me/fenoteMindset

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-28 21:15:31
#ቅምሻ

ከእጅህ ወጣ እንጂ፣ ከሕይወትህ አልወጣም!

በንግግር ወይም ደግሞ በተግባር አንድ ጊዜ ከአንተ የወጡ ነገሮች ከሕይወትህ በፍጹም አይወጡም። አንድ ጊዜ ልናገርና ይውጣልኝ ያልከው ነገር ተናግረኸው ከአንደበትህ ወጣ እንጂ ከሕይወትህ በፍጹም አይወጣም። የተናገርከው ነገርም ሆነ የተገበርከው ነገር ተጽዕኖ መልካምም ሆኖ መጥፎ እስከወዲያኛው ፍሬ እያፈራ ይኖራል።

በማንኛውም የሕይወት መስክህ ከእጅህ የወጣው ዘር፣ ጥሩም ሆነ መጥፎ፣ ለወደፊቱ ተባዝቶ ይጠብቅሃል እንጂ አይሞትም። ስለዚህ፣ ማንኛውም አይነት በንግግርም ሆነ በተግባር ከአንተ ያወጣኸው ነገር እንደ ዘር ስለሆነ ከሕይወትህ በፍጹም እንደማይወጣ በማስታወስ ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ ለማድረግ የምትችለውን አድርግ።

ማንኛውም ለማረግ ወይም ላለማድረግ የወሰንከው ተግባር ወይም ደግሞ ለመናገር ወይም ላለመናገር የወሰንከው ንግግር ከአንተ እስካልወጣ ድረስ አልተዘራም፤ ሆኖም አንድ ጊዜ ከአንተ እንደወጣ ግን ዘር ተዘርቷል።

በሌላ አገላለጽ፣ ከእጅ የወጣና የተበተነ ዘር ከእጅህ ወጣ እንጂ ከሕይወትህ አይጠፋም። ይህ እውነታ ለምትናገራቸውን ንግግሮችም ሆነ ለምታደርጋቸው ነገሮች ምን ያህል ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበህ ያስታውስሃል።

ሰዎች ከዓመታት በፊት ለተናገሩት ነገርና ላደረጉት አጉል ተግባር በየተራ መልስን እንደሰጡና ዋጋ እየተከፈላቸው ወይም ዋጋን እየከፈሉ ይኖራሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ ሰዎች ከረጅም ጊዜ በፊት ላደረጉት መልካም ተግባር ዋጋቸውን እንደተቀበሉ ይኖራሉ።

(Dr. Eyob Mamo)
157 viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 15:52:47 ያለህን ተመልከት !

ደስታህን ለማግኘት ሩቅ መሄድ አይጠበቅብህም ያሉህን ነገሮች በቂ ናቸው ፤ ሁል ግዜ ግን ችግሮችን የምታይ ከሆነ እና ፈተናዬ የበዛ ነው እያልክ የምታስብ ፣ ባለህ የማትደሰት ፣ በሆነው ሁሉ ቅሬታ ያለህ ከሆነ እመነኝ ዛሬ የምታማርራቸውን ቀናቶች የሚያስመሰግኑ ሌሎች ከባድ ቀናቶች ይመጣሉ ስለዚህ ሁሌም ባለህ ተደሰት አመስግን ያኔ በእጥፍ ይጨመርልሀል !

መልካም ሰንበት ተመኘን
https://t.me/FenoteMindset
212 views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 19:35:32 "አለማንበብ አለማበብ ነው."
አንብቡ! ብሎ መምከር ነውር የሚሆንበት ጊዜ ይናፍቀኛል።የሚያነብ ትውልድ እንደ አሸን የፈላበት ሀገር እመኛለሁ አንዳንዶች "አንባቢ የለም!ደራሲውም ቢሆን ለፍቶ መና ነው የሚሆነው"የሚሉ ሰዎችን አዳምጣለሁ ግን ደግሞ እኛ የጠፋን አንባቢ ሳይሆን እያሰበ የሚያነብ፤እያነበበ የሚያስብ አካል ነው!የሚል ሀሳብ በአዕምሮዬ ያቃጭላል።
አንብቦ መጠየቅስ?ብሎ አዕምሮዬ ግብረ መልስ ይሰጠኛል።መልሱን ወዲያው አገኘዋለሁ።ለመጠየቅ ማሰብ ይቀድማል እላለሁ። አንዳንድ አንባቢን(አሳቢን)የሚተቹ ፣ለመብላት የሚኖሩ ሰዎችን ስመለከት ደግሞ በንዴት(በቁጭትና)እበግናለሁ።
ዝኮነ ኮነና አንብቡ !ምክሬ ነው።
280 views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 23:28:17 #life_hacks

የሆነ ሰው የተሳሳተ ስልክ ቁጥር እንደሰጠህ ከተሰማህ መልሰህ በተሳሳተ መልኩ #ቁጥሩን አንብብላቸው ካስተካከሉህ ልክ ናቸው፤ ካላስተካከሉህ ግን
268 viewsedited  20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 21:00:13 #የተጋበዝከውን_ሁሉ_አታግበስብስ

የሆነ ሰው በምክንያትም ይሁን ያለ ምክንያት ሊያበሳጭህ ወይም ሊያናድድህ ቢጀምር ልክ በዚያ ቅፅበት የተቀበልከውን ነገር በአይነት መመለስ እንደማይገባህ አስታውስ ፡፡ ምክንያቱም ላናደደህ ሰው እንደዚያው አይነት ምላሽ ስትሰጥ ወደ ሰውዬው ሃሳብ ተወሰድክ ማለት ነው ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው ሲያበሳጭህ ተረጋግተህና ራስህን ተቆጣጥረህ እሱ እንዳደረገው አይነት ምላሽ ከመስጠት ከተቆጠብክ የሰውነቶችህን አካላት ሁሉ በመደበኛ ስራቸው ላይ ሳይረበሹ እንዲቆዩ ማድረግ ትችላለህ ፡፡ ይህም በምክንያት እንድትመራ የሚያስችልህ የዘወትር ተፈጥሮህ ነው ፡፡

ስለዚህ ሁልጊዜ ሌሎች ባቀረቡልህ ግብዣ በመወሰድ ራስህን በሌሎች ቁጥጥር ስር ላለማዋል ተጠንቀቅ ፡፡ ይልቁንም ግብዣውን አንተ ለማድረግ ሞክር ፡፡ ሰዎች ብዙም በማያውቋቸው መሳሪያዎች አማካኝነት የመጋበዙን ቅድሚያ ውሰድ ፡፡ ያን ጊዜ ሌሎችን የምትቆጣጠረው አንተ ትሆናለህ ፡፡

ሁሉም ነገር የሚስበው የሚመስለውን ነው ፡፡ ይህ መቼም የማይካድ ሃቅ ነው ፡፡

#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ
ናፖሊዮን ሂል
═══════❁✿❁ ═══════
@fenotemindset
360 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 08:56:56
"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም፤የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም፤የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።

እናም አንድን ነገር ለታይታ ማድረግ ሞኞች የፈለሠፉት የመከበር ሙከራ መሆኑን ተረድተህ" በቀጥተኛው መንገድ ለመጓዝ ሞክር....!!


@fenotemindset
475 viewsedited  05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 22:08:18 መበርታት አለብህ

ህይወት ትርጉም የሚኖራት አንተ እስካለህ ድረስ ነው፤ አንተ ከሌለህ እኮ ያ ለቤተሰቡ የሚያስበው፣ ለሚወዳቸው ዋጋ የሚከፍለው ጠንካራው ሰው የለም ማለት ነው።

መጥፎ ስሜት ሊሰማህ ተስፋ መቁረጥ ሊፈታተንህ ይችላል፤ ወዳጄ አንተ መበርታት ያለብህ ለራስህ ብለህ ብቻ አይደለም፤ በዙሪያህ ፈጣሪ ላስቀመጣቸው ስጦታዎችህም ስትል ነው!
@Fenotemindset
361 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 21:14:00 ከፍታው ላይ እንገናኝ!

ውስጥህ የሚናገር አንበሳ የሆነ ድምፅ አለ፤ ምንም ነገር እንደማያቅትህ፣ እንደምትችል፣ ጀግና እንደሆንክ አጥብቆ የሚነግርህ፤ በደምብ አርገህ ስማው! እመነው! እስከዛሬ ሰው ጫን አርጎ የሚነግርህን ድክመት አምነሀል እኮ፤ ከዚህ በኋላ ግን ጆሮህ የሚከፈተው ለሚለውጥህ ወይ ለሚያሳድግህ ነው እንጂ ወደ ኋላ ለሚጎትትህ አይደለም!

"የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም" ነው አባባሉ፤ አሁን ራስህን ለመለወጥ ልብህ ተነስቷል ማፈግፈግ የለም! ከፍታው ላይ እንገናኝ ወዳጄ

@fenotemindset
348 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 08:19:07 የተግባር ሰው ሁን!

"ስፖርት መስራት እጀምራለሁ፣ አንድ መፅሀፍ በሳምንት አነባለው፣ በጠዋት እነሳለው፣ ራሴን አሻሽላለው" ብለህ ካሰብክ ቆየህ ፤ ግን መቼ ነው ወደ ተግባር የምትገባው? ሁልጊዜ ሰኞ ሲመጣ ወይ ወሩ ሲያልቅ፣ ወይ አመቱ ሲፈፀም ማቀድ አልሰለቸህም?

ወዳጄ ምግብ የበላ እንጂ ለመብላት ያሰበ አይጠግብም እኮ! መድሀኒቱን የዋጠ እንጂ ስለ መድሀኒቱ አብዝቶ ያወቀ አይድንም እኮ! ማወቅ ማሰብ ማቀድ አሪፍ ቢሆንም ተግባር ከሌለው ግን በዜሮ ነው ሚባዛው! ስለዚህ አንዱን ዕቅድ አሁኑኑ ጀምረው! ዳይ ወደ ተግባር!

የተግባር ህይወት ተመኘንላችሁ
@Fenotemindset
322 views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 13:41:52
#ይህን_ያዉቁ_ኖሯል?

ኢትዮጵያዊዉ ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ከዳኝነቱ ባሻገር

የአስትሮፊዚክስ ሊቅ እና የስነ-ህዋ ተመራማሪ ብላቴና የሮቤልበአምላክ ወላጅ አባት ነዉ።

በነርሲንግ ሙያ ተመርቆ በህክምና ሙያዉ በጤና ተቋም ዉስጥ ሃኪም ሆኖ አገልግሏል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሶሾሎጂ ዲግሪዉን ያገኘ እና በአንድ የጥናቶ ምርምር ተቋም ዉስጥ ረዳት ተመራማሪ ሆኖ ሰርቷል።

በአምላክ ከሜዳ ስራዉ ባሻገር በማህበራዊ ህይወቱ ትሁት እና ደግ መሆኑ ይነገርለታል።

@fenoteMindset
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !
352 viewsedited  10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ