Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ ማህበር አንድ መንበር አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fenot2 — ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ ማህበር አንድ መንበር አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fenot2 — ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ ማህበር አንድ መንበር አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ
የሰርጥ አድራሻ: @fenot2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 659
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓት እና ደንብ የተከተለ ሃይማኖታዊ መልእክት እሚተላለፍበት ነው ሃይማኖት እንደ አባቶቻችን ቴክኖሎጂ እንደዘመናችን!
ተጠቅመን የገዳማት ታሪክ ወቅታዊ የቤ/ክ መልዕክት እና መረጃ የምንለዋወጥበት ቃለ እግዚአብሔር የምንማርበት ነ የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ሃይማኖት ይህች ናት:: እንኖርባታለን

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-05 18:26:46
በቅዱስ ላሊበላ የሚከበረውን ልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ ከሰኔ 9-15 የገዳማት ጉብኝት ጣና ሃይቅ ላይ የተወሰኑትን ገዳማት ሌሎቹንም ጨምሮ በዙር የሚጎበኙትን ልዩ ጉዞ ይሳተፉ ባጭር ግዜ ብዙ ገዳማትን ይጎብኙ 0911646037/0945445414
የጉዞ መነሻ እና መመዝገቢያ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ( መርካቶ ) በባንክ ከፍሎ ቦታ ማስያዝ ይቻላል ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር ። https://t.me/fenotz
47 viewsEndale Seyoum, 15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 21:01:57
90% የተያዘ ይፍጠኑ አንድ ቀን የቀረው የደርሶ መልስ ጉዞ ነው ማን ያውቃል የጥያቄዎ መልስ ቀን ይሆናል የጻድቁ የአቡነ ሀብተማርያምን በዓል በአዲሱ ገዳማቸው ያክብሩ ።
56 viewsEndale Seyoum, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 15:41:11 ሊቃውንት ድምጻቹ ተሰማ!!!
የሴረኞች የጥፋት የክፋት ሰንሱለት ተበጣጠሰ!!!

✿ፍየል አዳይ ሁላ ያደልካቸውን ፍየሎች ሰብስበህ አርባ✿!!! ፍየል ሙክት የደረሳቸው 17 አባቶች እንደሆኑም ታውቋ፡፡

ክብር ለአረጋዊያን ሊቃነ ጳጳሳት ቤ/ክ ከወንበዴ መንጋጋ ፈልቅቃቹ ቤተክርስቲያንን ለታደጋጉቹ !!!

ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ መልካም የአገልግሎት ዘመን!!!

ህዝቡ ሁሉ እናንተን ተስፋ አርጓልና ታሪክ ትቀይሩ ዘንድ እነሆ መንፈስ ቅዱስ እናንተን አስቀምጧል!!!

በዛሬው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት በእጩነት

1ኛ. ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፳፮ ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2ኛ. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦንስ ፲፪ ድምጽ
3ኛ. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፯ ድምጽ አግኝተዋል፡፡

ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በእጩነት ከቀረቡት መካከል
1ኛ. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፳ ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2ኛ. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ፲፯ ድምጽ
3ኛ. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ፰ ድምጽ አግኝተዋል፡፡

ስንደማመጥ ስንሰማማ ብዙ ታሪክ እንሰራለን!!!!!
50 viewsEndale Seyoum, 12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 15:28:05
በአቋማቸው የሚታወቁት በቤተክርስቲያን ክብር ዙሪያ ድርድር የማያውቁት ታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ እስኪያጅ ሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበዋል።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ሆነው ተመድበዋል።
መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሁንላቹ !!!!
36 viewsEndale Seyoum, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 00:19:02
በቅዱስ ላሊበላ የሚከበረውን ልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ ከሰኔ 9-15 የገዳማት ጉብኝት ጣና ሃይቅ ላይ እና ሌሎቹንም ጨምሮ በዙር የሚጎበኙትን ልዩ ጉዞ ይሳተፉ ባጭር ግዜ ብዙ ገዳማትን ይጎብኙ 0911646037/0945445414
የጉዞ መነሻ እና መመዝገቢያ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ( መርካቶ ) በባንክ ከፍሎ ቦታ ማስያዝ ይቻላል ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር ።
42 viewsEndale Seyoum, 21:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 23:53:24 + ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 23 2014
አዲስ አበባ

ፎቶ :- ኢያሪኮ "የዘኬዎስ ዛፍ" የነበረበት ሥፍራ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
33 viewsEndale Seyoum, 20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 16:49:08 በዚህ ግዜ ሊያመልጣችሁ የማይገባ ጉዞ
35 viewsEndale Seyoum, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 16:48:34
32 viewsEndale Seyoum, 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 06:47:56 ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡
ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡

ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡

አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡

የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡

እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡

በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳
እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡

ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡

የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡
ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’
ብዬ ላመስግነው፡፡

ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡

የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ”

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የብርሃን እናት - ገፅ 305-308
46 viewsEndale Seyoum, 03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 07:07:10 " እናቴ_ማርያም_ደጓ_እናቴ"

እንኳን_ለደብረ_ምጥማቅ_አመታዊ_የመገለጥ_በዓል_
በሰላም_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን ◈።
◇ ግንቦት ❷❶_
"እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም"➺በድብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ
ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት (5) ቀን የታየችበት ነው።
◇ ጥንት ነገሩ እንዲህ ነው።
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ስግደት ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮጵያ በተሰደደበት ጊዜ።
◈ ከድንግል እናቱ፣ ከዮሴፍ፣ ከሰሎሜ ጋር በደብረ ምጥማቅ ነበር።
◇ እመቤታችን ቦታውን ስለወደደችው።
ልጇ እንዲህ አላት ይህ ቦታ ወደ ፊት ያንቺ መገለጫ ያሆናል ብሎ ቃል ኪዳን
ገባላት።
እመቤታችን በልጇ ፍቃድ ግንቦት 21 ቀን ከአእላፍ መላእክት፣ ፆድቃን፣
ሰማዕታት አስከትላ መታ ለአምስት ቀን ና ለክርስቲያኑና ለአሕዛቡ የተገለፀችበት
ቀን ነው።
◈➺ ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ ቀን ግብጽ
ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን
መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር።
እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር።
◈ ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው
ይከትማሉ ፤ ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት
ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤
◇ ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን? ይሏታል
◈ ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን
◈ ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል?
◈ አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል?
◇ እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤
አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር
ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ
ጋር ነው።
◇ ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤
◇ አሁን ግን ኃጢያታችን ሲበዛ በረድኤት ወይም ለበቁ ካልሆነ
በገሃድስ ተገልጻ አትታይም።
➺ ለእናቱ ለቅዱስተ ቅዱሳን ለንፅህተ ንፁሀን
◈ ለአዛኝቷ ድንግል እመቤቴ ለቅድሳን እናታቸው
◈ ለነቢያት ትንቢታቸው
◈ ለሰማእታት እክሊላቸው ለሆነች ለእናቱሲል ይማረን። ኣሜን፫
➺◇በቃቹህ ይበለን ከመጣብን ከዚህ ክፉ የዘር በሽታ በቃችሁ ይበለን።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ በልባችን ጣዕሟ በአንደበታችን
ይደርብን።
➺ወስብሐት ለእግዚአብሔር
➺ወለወላዲቱ ድንግል
➺ወለመስቀሉ ክብር


https://t.me/fenot2
48 viewsEndale Seyoum, 04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ