Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ክፍል(የፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት ደብረ ዘይት)

የቴሌግራም ቻናል አርማ felegetbebmazkenat — የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ክፍል(የፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት ደብረ ዘይት)
የቴሌግራም ቻናል አርማ felegetbebmazkenat — የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ክፍል(የፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት ደብረ ዘይት)
የሰርጥ አድራሻ: @felegetbebmazkenat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 723
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ክፍል ነው ስለተቀላቀሉን በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ።
YouTube : https://youtu.be/XfB6zF176w4
Tiktok :
Facebook :

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-11 18:48:22
107 views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 18:48:22 እሳቸው ግን በሠርጉ ሌሊት ከጫጉላ ቤት ጠፍተው በርሃ ገቡ:: ከዚያም በቅዱስ መልአክ መሪነት ሃገረ ምሑር ደረሱ:: በቦታውም ጣዖትን ሰባብረው: ተአምራትንም አድርገው: ሕዝቡን ወደ ክርስትና መለሱ:: መስፍኑ አውጊት ግን ተፈታተናቸው: አሠራቸው: አሥራባቸው::

በጦር እወጋለሁ ሲል ግን መሬት ተከፍታ ከነ ተከታዮቹ ውጣዋለች:: ከ5 ዓመታት በኋላ ግን ማልደው: ከሰጠመበት አውጥተው አጥምቀውታል:: ቀጥለውም ምድረ ጉራጌ ወርደው: ሕዝቡን አሳምነው አጥምቀዋል::

የአዳልን ሕዝብና ንጉሡን አብደልማልን አስተምረው ያጠመቁም እርሳቸው ናቸው:: ድል አሰግድ የሚባለውን መስፍንም ያሳምኑ ዘንድ ጠንቅዋዮቹን ድል አድርገው አጥፍተዋል::

ጻድቁ ዜና ማርቆስ ከዚህ ሐዋርያዊ ሥራቸው በተጨማሪ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምንኩስናን ከተቀበሉባት ቀን ጀምረው በጾም: በጸሎትና በሰጊድ ኑረዋል:: ፀሐይን በምድረ ጉራጌ እስከ ማቆም ደርሰውም ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል::

አእላፍ ደቀ መዛሙርትን ሲያፈሩ 200 አንበሶች በቀኝ: 200 ነብሮች በግራ ይከተሏቸው ነበር:: ደብረ ብሥራትን ጨምሮም ገዳማትን አንጸዋል:: በመጨረሻም የምሕረት ቃል ኪዳንን ከፈጣሪ ዘንድ ተቀብለው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ዐርፈዋል::

††† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

††† ታኅሣሥ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ብጹዓን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ካህናት ዘካርያስና ስምዖን
4.ቅዱስ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት
5.አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ (ዘደብረ በንኮል)
2.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
3.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)

††† "ድንግል ሆይ! አንገታቸውን እንደሚያረዝሙ እንደ እብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም:: በቅድስናና በንጽሕና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ::
ድንግል ሆይ! ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ሕብስትን እንጂ::
ድንግል ሆይ! ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን እንጂ::" †††
(ቅዳሴ ማርያም)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
107 views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 18:48:21 ወዲያው ግን ያቺ በትር እባብ ሁና ሽፍቶችን አጥፍታቸዋለች:: ጻድቁ ለቤተሰብ እየታዘዙ: ንጽሕናቸውንም እየጠበቁ ኑረው 30 ዓመት ሲሞላቸው ወላጆቻቸው ግድ ብለው ማርያም ክብራ ለምትባል ወጣት አጯቸው::
88 views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 18:48:21 ††† እንኳን ለእግዝእትነ ማርያም (#በዓታ): አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ እና ቅዱስ ፋኑኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም †††

††† ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር::

ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ::
እርሱ:-
*ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::

እርሷ ደግሞ:-
*የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

††† "ለጽንሰትኪ በከርሥ::
እንበለ አበሳ ወርኩስ::
ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት፣ ኢሳ. 1:9)
"ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ::
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::"
"ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን::
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን)"

የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኳ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::

ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: ቅዱሳኑ እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::

እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9)

††† የእመቤታችን የዘር ሐረግ:-
*አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
*በእናቷ:-
ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::

*በአባቷ በኩል:-
ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::

ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,023 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ድንግል እመ ብርሃንን ከወለዱ በኋላ ለ3 ዓመታት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ: ነዳያንንም ሲጠግኑ ኖሩ:: በእነዚህ ዓመታትም ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከእቅፏ አውርዳት አታውቅም::

ቅዱሳን መላእክትም ዘወትር እየመጡ ያጫውቷት ይንከባከቧትም ነበር:: 3 ዓመት በሞላት ጊዜም በቅድስት ሐና አሳሳቢነት ብጽዓታቸውን (ስዕለታቸውን) ይፈጽሙ ዘንድ ተዘጋጁ::

እንደ ሥርዓቱ የሚዘጋጀውን (መባውን) ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሲደርሱ አበው ካህናትና የመቅደሱ አገልጋዮች ሁሉ ሊቀበሏቸው ወጡ:: ሕዝቡ: ሊቃነ ካህናት ቅዱሳን ዘካርያስና ስምዖን: ኢያቄም ወሐና ከድንግል ማርያም ጋር ቆመው ሳሉም ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ከሰማይ ወርዶ ረቦ ታየ::

ከቅዱስ ዘካርያስ ጀምሮ ሁሉም ሰው ሕብስትና ጽዋዑን ለመቀበል ቀረበ:: ግን መልአኩ ራቀ:: ድንግል ማርያም በቀረበች ጊዜ ግን ከመሬት አፈፍ አድርጐ አንስቶ: ክንፉን ጋርዶ ሰማያዊውን ማዕድ መገባት:: በዚህ ደስ የተሰኙ ካህናትና ሕዝቡ እየዘመሩ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል::

አማናዊት መቅደሰ መለኮት ድንግል ማርያም ወደ ኦሪቱ ቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ጸሎታችን እንድትሰማን እንደ ሊቃውንቱ:-
"ማርያም አንቲ ሰዋስው ዘምድረ ሎዛ::
ዲቤኪ ትዕርግ ጸሎትየ ከመ ጼና ሠናይ መዓዛ::
ኀበ ለነፍስየ ታሰስል ትካዛ" እንላለን:: (አርኬ)

††† አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ †††

††† አባ ዜና ማርቆስ በሃገራችን በተለይ በደቡብ ምድረ ጉራጌ ስመ ጥር ሐዋርያዊ ጻድቅ ናቸው:: ምድረ ሽዋ ደግሞ እርሳቸውን ጨምሮ የብዙ ቅዱሳን መፍለቂያ ናትና ክብር ይገባታል:: ነቢየ ጽድቅ ዳዊት "ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ-የጻድቃን (የቅኖች) ትውልድ ይባረካል" (መዝ. 111) ያለው ነገር በምድረ ዞረሬ (ጽላልሽ) ተፈጽሟል::

ሦስት ወንድማማች የተባረኩ ካህናት በስፍራው ነበሩ:: ስማቸው ጸጋ ዘአብ: እንድርያስና ዮሐንስ ይባላል:: ከእነዚህ መካከልም ጸጋ ዘአብ: እግዚእ ኃረያን አግብቶ ኮከበ ከዋክብት ተክለ ሃይማኖትን ሲወልድ ካህኑ ዮሐንስ ደግሞ ዲቦራ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ ዜና ማርቆስን ወልዷል::

የአቡነ ዜና ማርቆስ ጽንሰታቸው ሚያዝያ 30 በብሥራተ ማርቆስ ወንጌላዊ ሲሆን ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 24 ቀን በበዓለ ሱራፌል ካህናተ ሰማይ ነው:: ዘመኑም 13ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::

ዜና ማርቆስ በተወለዱ በ40 ቀናቸው አጐታቸው ቀሲስ እንድርያስ (የ72 ዓመት ሽማግሌ ናቸው) ሊያጠምቁ ቀረቡ:: ሕጻኑ ዜና ማርቆስ ግን ከእናታቸው እቅፍ ወርደው 3 ጊዜ "እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" እያሉ ቢሰግዱ የመጠመቂያው ገንዳ ውኃ ፈላ::

ይህንን የተመለከቱት ካህኑ ደንግጠው ወጥተው ሲሮጡ ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት ተገልጦ "አትፍራ! ይልቁኑ ከጠበሉ ራስህን ተቀባ" አላቸው:: እንዳላቸው ቢያደርጉ ራሰ በራ ነበሩና ጸጉር በቀለላቸው::

ሕጻኑ ዜና ማርቆስ ግን 5 ዓመት ሲሞላቸው ወደ ጉባኤ ቤት ገብተው በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ዲቁናን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱም ሽፍቶች አግኝተው: በትራቸውን ቀምተው: አንገላተው ሰደዋቸዋል::
102 views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:51:09
1.0K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:50:26
1.0K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:49:57 ሰበር ዜና!

ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል ፡፡

ታኅሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

የበርካታ መናንያን መኖሪያ ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል ፡፡ ማምሻው የታጠቁ ኃይሎች በሁሉም አቅጣጫ ወደ ገዳሙ ሰብረው በመግባ መነኮሳትን በማገት ገዳሙን እያመሱት ይገኛል ፡፡

ሚዲያችን የሚመለከታቸውን አካላት ቦታው ድረስ በመደወል እየደረሰባቸው የሚገኘውን እንግልት ተረድተናል "ከገዳሙ የጥበቃ ኃይሎች የሚገኙትን መሣሪያዎች በከበባ ነጥቀዋል ፡ ገዳሙን በሁሉም አቅጣጫ በመግባት እያስጨነቁ ይገኛሉ ሦስት አገልጋዮችን አግተዋቸዋል ድረሱል ድረሱልን" የሚል ድምፅን አሰምተዋል ሲል ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።
(#FTM)
1.5K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:21:44
165 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:21:44 =>አምላከ ጻድቃን ቅዱሳን ከነደደ እሳት: ከዲያብሎስ ክፋትም ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::=>ታሕሳስ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ (አናንያ: አዛርያ: ሚሳኤል)
2.አባ ሖር ጻድቅ
3.ቅዱስ አውካቲዎስ ሰማዕት
4.አባ አንበስ ሰማዕት
5.7,033 ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስማሕበር)
6.ቅዱስ ናትናኤል መነኮስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)
6.ሊቁ አባ ሕርያቆስ
7.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

=>+"+ ናቡከደነፆርም መልሶ:- 'መልአኩን የላከ: ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ: ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን: የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን: በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ: የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::' +"+ (ዳን. 3:28)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
158 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:21:43 ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን "ሠለስቱ ደቂቅ" እና "አባ ሖር ገዳማዊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

" ታኅሣሥ 2 "

+*" ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ "*+

=>አናንያ: አዛርያና ሚሳኤልን እንዲያው በቀድሞው አጠራር ሠለስቱ ደቂቅ (ሦስቱ ሕጻናት) እንላቸዋለን እንጂ ለእኛስ በእድሜም: በጸጋም: በትሩፋትም አባቶቻችን ናቸው::

+ቅዱሳኑ የወቅቱ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጆች ናቸው:: ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ ሕዝቡን ሲማርክ አብረው ተማርከው ባቢሎን ወርደዋል::

+ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ:: ምንም እንኩዋ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

+አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

+ከነገር ሁሉ በሁዋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጉዋዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

+ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳም አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

+ከዚያች ቀን በሁዋላ አናንያ: አዛርያና ሚሳኤል በአት አጽንተው: በጾምና በጸሎት ተወስነው ኑረዋል:: ነፍሳቸው ከሥጋቸው ስትለይ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆኗል:: ቅዱስ ዳንኤልና ናቡከደነጾር ተሯሩጠው ቢሄዱ ሦስቱም በአንድነት ዐርፈው ተገኝተዋል:: ንጉሡ በእጅጉ ይወዳቸው ነበርና በወርቅ በተለበጠ ሳጥን ቀብሯቸዋል:: ስሞት ከመካከላቸው ቅበሩኝ በማለቱ ዛሬ ድረስ ለበቁ አባቶች የአራቱ መቃብር ባቢሎን ውስጥ ይታያል::

+ቅዱሳን አናንያ: አዛርያና ሚሳኤል (ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ) ያረፉት ግንቦት 10 ቀን ሲሆን ዘመኑም ከክርስቶስ 500 ዓመት በፊት ነው:: ይህቺ ዕለት ደግሞ ናቡከደነጾር ወደ እሳት ሲጥላቸው መልአከ እግዚአብሔር እነርሱን ያዳነበት ቀን ናት::

+አምላካቸው ከአሳት ባወጣቸው በዚህ ቀንም:-
"ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ::
ስቡሕኒ ውዕቱ ወልዑልኒ ውዕቱ ለዓለም::" የሚለውን ምስጋና ፈጣሪ ገልጾላቸው ደርሰውታል:: በእሳቱ ውስጥ ሆነው ተናግረውታል::

+ድርሰታቸው 2 ወገን ሲሆን ባለ ስድስት አንቀጹ ምስጋናቸው ከ600 ዓመት በሁዋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ የሚያሳይ ነው:: ሌላኛውና 33 አንቀጾች ያሉት ምስጋናቸው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ለ33 ዓመታት እንደሚመላለስ ያጠይቃል::

+ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ካረፉ ከ900 ዓመታት በሁዋላ (ማለትም ከክርስቶስ ልደት በ400 ዓመታት) ታላቁ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ቤተ ክርስቲያንን አንጾላቸው ነበርና አጽማቸውን ሊያገኝ ተመኘ::

+ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ጠርቶ "አባ! አጽመ ቅዱሳንን ባቢሎን ወርደህ አምጣልኝ?" አለው:: ቅዱሱ ሐጺር ዮሐንስም በደመና ተጭኖ ባቢሎን ገባ:: በቅዱሳኑ መቃብር ፊትም ሰግዶ አለቀሰ:: ሠለስቱ ደቂቅም "ወዳጃችን! ምን ሆንክ?" አሉት::

+ቅዱሱም መልሶ "ወደ ግብጽ እንሒድ:: አባ ቴዎፍሎስ ይፈልጋቹሃል" አላቸው:: እነሱም "ለቅዱሱ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው:: እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ:: ግን አጽማችን እስከ ዓለም ፍጻሜ ባቢሎንን አይለቅም:: ለክብርህ ግን እንመጣለን::"

+"ለምልክትም ይሆን ዘንድ መብራት ሳታበራ በሌሊት ጠብቀን በለው" ብለው ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ባርከው ሸኙት:: ሐጺርም መጥቶ መልአክቱን አደረሰ:: በዕለተ ቅዳሴ ቤታቸው ቅዱሳን:- ቴዎፍሎስ: ቄርሎስ: ሐጺር ዮሐንስና ሌሎችም ከምዕመናን ጋር በጨለማ ሳሉ ቤተ ክርስቲያኑ ቦግ ብሎ በራ::

+እጅግ የሚደነቅ ብርሃንም ከበባቸው:: በብርሃኑ መካከል ሠለስቱ ደቂቅ ሲያልፉ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ሕዝቡም በደስታና በዝማሬ የቅዱሳኑን ቅዳሴ ቤት አክብሯል::

+"+ አባ ሖር ገዳማዊ +"+

=>በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ከጻድቃንም: ከሰማዕታትም አሉ:: ከጻድቃኑ መካክል: በተለይም ከታላላቆቹ አንዱ ቅዱስ አባ ሖር ነው:: አባ ሖር በዘመነ ጻድቃን የነበረና በደግነቱ የሚታወቅ ክርስቲያን ነው::

+በዓለም ያለውን በጐነት ሲፈጽም ድንግልናውን እንደ ጠበቀ ገዳም ገባ:: በዚያም በአገልግሎት ተጠምዶ ዘመናትን አሳለፈ:: ከዚያም መነኮሰ:: ከመነኮሰ በሁዋላ ደግሞ አበውን በማገልገል: በጾምና በጸሎት: በበጐው ትሕርምት ሁሉ የተጠመደ ሆነ:: ግራ ቀኝ የማይል ("ጽኑዕ ከመ ዓምድ ዘኢያንቀለቅል" እንዲሉ አበው) ብርቱ ምሰሶ ሆነ::

+ሰይጣንም አባ ሖርን በብዙ ጐዳና ፈተነው:: ከእርሱ ጋር መታገል ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት በገሃድ ተገለጠለት:: "አንተኮ የምታሸንፈኝ በአበው መካከል ስለ ሆንክ ነው:: በበርሃ ብቻህን ባገኝህ ግን እጥልሃለሁ" ሲል ተፈካከረው::

+አባ ሖርም የዳዊትን መዝሙር እየዘመረ ጭው ወዳለ በርሃ ገባ:: በዚያም ሰይጣን ታገለው:: ግን ሊያሸንፈው አልቻለም:: ምክንያቱም ኃያሉ እግዚአብሔር ከጻድቁ ጋር ነበርና:: ሰይጣን እንደ ተሸነፈ ሲያውቅ እንደ ገና ሌላ ምክንያት ፈጠረ::

+አሁንም በገሃድ ተገልጦ ተናገረው:: "በዚህ በበርሃ ማንም በሌለበት ብታሸንፈኝ ምኑ ይደንቃል! ወደ ከተማ ብትሔድ ግን አትችለኝም" አለው:: ቅዱስ ሖር ግን አሁንም ሰይጣንን ያሳፍር ዘንድ በፈጣሪው ኃይል ተመክቶ ወደ ዓለም ወጣ::

+"እግዚአብሔር ያበርሕ ሊተ ወያድኅነኒ: ምንትኑ ያፈርሃኒ - እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው:: የሚያስፈራኝ ማነው!" ሲል (መዝ. 26:1) ይጸልይ ነበር:: በከተማም በነበረው ቆይታ አልባሌ ሰው መስሎ ደካሞችን ሲረዳ: ነዳያንን ሲንከባከብ: ለድሆች ውሃ ሲቀዳ: እንጨት ሲሰብር ይውልና ሌሊት እንደ ምሰሶ ተተክሎ ሲጸልይ ያድራል::

+ሰይጣን በዚህም እንዳላሸነፈው ሲያውቅ ከሰዎች ጋር በሐሰት ሊያጣላው ሞከረ:: ፈረስ ረግጦ የገደለውን አንድ ሕጻን ሲያይ ሰይጣን ሰው መስሎ ወደ አባ ሖር እየጠቆመ "እርሱ ነው ረግጦ የገደለው" አላቸው:: የሕጻኑ ወገኖች ቅዱሱን ሲይዙት አባ ሖር "ቆዩኝማ" ብሎ የሞተውን ሕጻን አንስቶ ታቀፈው::

+ጸልዮ በመስቀል ምልክት አማተበበትና "እፍ" ቢልበት ሕጻኑ ከሞት ተነሳ:: ለወላጆቹም ሰጣቸው:: ይሕንን ድንቅ የተመለከቱ የእስክንድርያ ሰዎችም ይባርካቸው ዘንድ ሲጠጉት ተሰውሯቸው በርሃ ገባ:: ውዳሴ ከንቱን ፈጽሞ ይጠላት ነበርና::

+ጻድቁ አባ ሖር ቀሪ ዘመኑን በበርሃ አሳልፎ በዚህች ቀን በክብር ዐርፏል::
150 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ