ክፍል (44) #ነገረ ድኅነት #ሰው በበደሉ ምክንያት ያ ተወስዶበት የነበረው ዘለዓለማዊው ሕይወት የዘለዓለም #ክብርና ነፃነት ተድላና #ሰላም #ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በተዋህዶ ሰው ሆኖ #ወደዚህ ምድር በመምጣት #በፈቃዱ በተቀበለው ጸዋትወ መከራና #ሕማም በፈጸመው #የድህነት ተግባር የተመለሰለት ቢሆንም #ይህን ለመውረስ #ማመን #መታመን #መመስከር ይጠበቅብናል ። #የክርስትና #መገለጫዎችም እነዚህ ናቸው። #በክርስትና ሕይወት ሃይማኖትና ምግባር አይነጣጠልም #በሃይማኖት የእግዚአብሔርን #ህልውናና #የማዳን ሥራ አምነን እንቀበላለን ። #በምግባር ደግሞ ለአመነው እግዚአብሔር እንታመናለን። ( ያዕ 2 ÷ 14 ) ሰው #ለአምላኩ የሚያቀርበው ግብሩ የሚገዛበት ዓይነቱና መታወቂያው ፍትወቱንና (ፍላጎት ) #ጉልበቱን በሚሰጥበት ምግባር (ሥራ ) ነው እንጂ #የጉልበት ድካም የሌለበትን ያቺን የልብ ሃይማኖት ብቻ ይዞ (ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ #በመጮህ የሚዞሩትንና ዕምነት በልብ ነው እያሉ ከጾም ጸሎት የተራቋቱትን ማለታችን ነው) ። #ምግባር የማይሠራ ሰው #በፈጠረው በአምላኩ የሚቀልድ #ሥጋውን የሚወድ ብልጥ አምናለሁ ግን #አልገብርም የሚል ዐመፀኛ መሆኑን ማወቅ የገባዋል። #የአፍ ሀብታም #የምግባር ድኃ ከመሆን አምላክ በቸርነቱ ይጠብቀን። ስብሐት ለሥላሴ ይቀጥላል ቀሲስ ጥሩውኃ ክፍሌ። 148 viewszemari tiruwuha, 16:12