Get Mystery Box with random crypto!

ፈለገ ፅድቅ ሰንበት ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ felege1623 — ፈለገ ፅድቅ ሰንበት ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ felege1623 — ፈለገ ፅድቅ ሰንበት ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @felege1623
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 329
የሰርጥ መግለጫ

የኮተቤ ካራ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት የፃዲቁ አቡነ ሃብተ ማርያም ቤተክርስቲያን የፈለገ ፅድቅ ሰንበት ት/ቤት
ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
@felegetsdike_Bot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-08 10:33:38
87 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 10:33:27
87 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 15:52:21 "ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው።"

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መግለጫ ሰጡ።

ሐዋ. ፳፫፥፭ "በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር" የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻ በማድረግ መግለጫውን የጀመሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ላይ በጥራዝ ነጠቅነት የተሳሳተ መረጃ መስጠት ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ታዝናለች" ብለዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አባትን በዚህ መንገድ መናገር ሉዓላዊ የሆነች የኢ/ኦ/ቤ/ክንን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን መድፈር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው
ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ትርፍ ማግኘት አይቻልም ሲሉ አብራርተዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን በውጪ ሀገር መትከል ከጀመረች ጀምሮ ጽላት በአሠራሯ መሠረት ትልካለች።
የታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እና ልጆቿ በረሃብ እየተገረፉ የጠበቁትን ሁኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ታሸሻለች ብሎ ማሰብ ንስሐ ያስገባል።
ይህ የቅዱስነታቸውን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ክብር መንካት ነው ብለዋል።

መንግሥት ለምን ብሎ መጠየቅ እና መመርመሩ ተገቢ ነው። ነገር ግን ቅርጽና ቅርስ መለየት ያስፈልጋል። በቀጣይም በጉዳዮ ላይ ግልፅነት ለመፍጠር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በቀጣይ እንወያያለን በማለት በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

https://t.me/felege1623
228 views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 13:19:17
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለሕክምና ከሀገር ውጭ እንደሚሄዱ ገልፀው ሕክምናቸውን አጠናቀው እስኪመለሱ ካህናትና ምዕመናንና ተረጋግተው የሚጠበቅባቸውን ተግባር እያከናወኑ እንዲቆዩ መልዕክታቸውን አስተላለፉ !!!


https://t.me/felege1623

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሕክምና ከሀገር ውጪ መጓዝ ማሰባቸውን በማስመልከት ዛሬ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በአስቸጋሪ የጤና ሁኔታ መቆየታቸውን ጠቅሰው ከሀገር ውጪ ለመታከም ማሰባቸውን ገልፀዋል፡፡ በተቻለ መጠን የተለየ ችግር ካልገጠማቸው ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ በመንበረ ፕትርክናቸው እንደሚመለሱ የገለጹት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስለ ሀገርና ስለወገን እየፀለዩ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንዲቆዩ ጠይቀዋል፡፡

የዐይን ሕክምና ጨምሮ ሙሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው አስኪመለሱ አባቶችና ምዕመናን በጸሎት ያስቡኝ ያሉት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ክብር አስጠብቀው ሥራቸውን በኃላፊነት እንዲያከናውኑ አደራ ብለዋል፡፡

ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ለሕክምና ሊሄዱ እንደነበር የተናገሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ሁኔታቻዎች ባለመመቻቸታቸው እንደቆዩ ገልፀው አሁን ግን ነገሮች ስለተስተካከሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው እስኪመለሱ ምእመናንና ካህናት ተረጋግተው የሚጠበቅባቸውን ተግባር እያከናወኑ እንዲቆዩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

https://t.me/felege1623
https://t.me/felege1623
511 viewsedited  10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 09:30:42
#እንኳን_አደረሳችሁ።
297 views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 13:08:00
በገና መማር ለምትፈልጉ ምዝገባ ተጀምሯል።
ትምህርቱ ሐምሌ 3/2014 ይጀመራል።
ለበለጠ መረጃ :- 0975254348 0927953135
1.1K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 22:03:03 ሰኔ 12 በደብራችን ሰንበት ት/ቤት የቀረበው ወረብ





994 viewsedited  19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 17:10:02
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በወቅታዊ ጉዳይ አባታዊ የኀዘን መልእክት አስተላለፉ።
378 views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 21:47:28
†† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። ††

https://t.me/felege1623

† ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት †

††† ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::
ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች እናከብረዋለን:-
1.በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
2.ቅዳሴ ቤቱን (ግብፅ ውስጥ)
3.ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
4.ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
5.ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
6.ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና::
††† ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::
†††
1.1K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 13:05:11
335 views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ