Get Mystery Box with random crypto!

ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ በሥራ ቦታ ስርጭቱ ለመግታት የአሰሪና ሰራተኞች ግንዛቤ የሚያሳድጉ ተግባራት | Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ በሥራ ቦታ ስርጭቱ ለመግታት የአሰሪና ሰራተኞች ግንዛቤ የሚያሳድጉ ተግባራት ማከናወን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዓለም የኤች አይቪ ኤድስ ቀንን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

በዉይይት መድረኩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ የአሰሪና ሰራተኛ ፌዴሬሽንና ኮንፌዴሬሽን ተወካዮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተካልኝ አያሌዉ እንደገለጹት፤ ኤች አይ ቪ ኤድስ በስራ ቦታዎች ወጣቶችንና አምራች ኃይል ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ በተለይ አሠሪና ሠራተኞች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራት ወሳኝ ነው፡፡

በመሆኑም ፋብሪካዎች እና ድርጅቶች ከመደበኛ ስራቸዉ ጎን ለጎን የቫረሱ ስርጭት መግታት የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በስራ ቦታ ላይ የሰራተኞች የሙያ ደህንነትና ጤንነት ላይ አቅዶ እየሰራ ይገኛል ያሉት መሪ ስራ አስፈፃው በተለይ ኤች አይቪ ኤድስ በስራ ቦታ ለመቆጣጠር እና ስርጭቱን ለመግታት የሶስትዮሽ ፖሊሲ ማዕቀፍ በኢትዮጰያ አሰሪዎች ፌዴሬሽንና ኮንፌዴደሬሽን፣ በኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽንና በስራና ክህሎት ሚኒስቴር መካከል በጋራ ለመስራት በመፈራረም አበረታች እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥርና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ዴስክ ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ታደሰ በበኩላቸዉ ስራዉ የሁሉም አካላት ቅንጅትና ትኩረት የሚሻ በመሆኑ በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ስርጩቱን ለመግታት ይሰራል ብለዋል፡፡//

ሕዳር 30/2015 ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር