Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮ- ቻይና የቴክኒክና ሙያ ልማት ህብረት ይፋ ተደረገ በቻይና አዘጋጅነት ዛሬ በተካሄደው የዓ | Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

የኢትዮ- ቻይና የቴክኒክና ሙያ ልማት ህብረት ይፋ ተደረገ

በቻይና አዘጋጅነት ዛሬ በተካሄደው የዓለም አቀፉ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት እድገት ኮንፈረንስ የኢትዮጵያ- ቻይና የቴክኒክና ሙያ ልማት ህብረት ተመስርቶ ይፋ ተደረጓል፡፡

በኮንፈረንሱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስት ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የትብብር ማዕቀፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡

ቻይና በኢትዮጵያ በትምህርትና ስልጠናው ዘርፍ እያደረገች ያለችው ድጋፍ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እውን እንዲሆን ያደረገ ሲሆን ይህም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው፡፡

የልማት ህብረቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ የንግድ ማህበራት፣ ባለሙያዎችና ምሁራንን የሚያስተሳስር ከመሆኑም በላይ ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለመስጠር የሚያስችል ምህዳር ለመፍጠር የሚረዳ ነው ብለዋል።

በመድረኩ በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 30 የሥልጠና ማዕከላትን በመገንባት 20 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን እንደሚሰለጥኑ፣ 100 የሚሆኑ ተቋማት ዓለም አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ደረጃዎችን እንዲያሟሉ እንዲሁም አንድ ሺህ ለሚሆኑ አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና ሰራተኞች የአጫጭርና የረዥም ጊዜ ስልጠናን እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡