Get Mystery Box with random crypto!

#ፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ መንተስኖት ጌጡን አስፈርሟል!! ፋሲል ከነማ በ2015 የው | ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

#ፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ መንተስኖት ጌጡን አስፈርሟል!!

ፋሲል ከነማ በ2015 የውድድር አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ የአሰልጣኝ አባላቶችን በአዲስ መልክ አዋቅሯል!! የዋና አሰልጣኝ ሀላፊነት ለኃይሉ ነጋሽ የተሰጠ ሲሆን ም/አሰልጣኝ ሙሉቀን አቡሃይ ፣ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ አዳም ባዘዘው ሲሆኑ በፋሲል ከነማ የአካል ብቃት አሰልጣኝ በመሆን ወደ ቤቱ የተመለሰው ምንተስኖት ጌጡ ለሁለት አመት የሚያቆየው ውል በዛሬው እለት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፀድቋል።

ፋሲል ከነማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድግ በምክትል እና ዋና አሰልጣኝነት ሚና ያሳለፈው ምንተስኖት ጌጡ በአካል ብቃት የአሰልጣኝነት ሙያ የአሰልጣኝ አባሉን መቀላቀሉ ትልቅ ድጋፍ የሚሰጥ ነው!!

አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ እንኳን ደህና መጣህ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለን!!



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official