Get Mystery Box with random crypto!

በአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በሚሰጠው ስልጠና መሳተፍ ለምትፈልጉ | Farankaa - ፈራንካ

በአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በሚሰጠው ስልጠና መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተደራሽነቱን በማስፋት የዲስትሪክቶቹን ቁጥር ከ12 ወደ 24፤ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ደግሞ ወደ 108 በማሳደግ ይበልጥ በማሳደግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በያዝነው የ2015 ግማሽ ዓመት ለአራተኛ ጊዜ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ለመስጠት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
ባንካችን እያደገ የመጣውን የሰልጣኞችን ፍላጎት እና ቁጥርን ታሳቢ በማድረግ ስራዎች ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ ለአራተኛውን ዙር ስልጠና ምዝገባም በ24 ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፎች ለማካሄድ ባንካችን ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
ተሳታፊዎች ሥልጠናውን ለመውሰድ የሚያስችላችሁን ምዝገባ ለማድረግ ከጥር 06 እስከ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ በመላ የሀገሪቱ ከተሞች በሚገኙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲስትሪክቶች ስር በሚገኙ 108 ቅርንጫፎች ማለትም፡-
1. በአዲስ አበባ  
2. ጎንደር  
3. ባህርዳር  
4. ደሴ 
5. አሶሳ  
6. ደብረብርሃን 
7. ነቀምት 
8. ሁመራ 
9. ጅግጅጋ 
10. አዳማ  
11. ደብረማርቆስ 
12. ወላይታ ሶዶ 
13. ጅማ 
14. ድሬዳዋ 
15. ሻሸመኔ 
16. ጎባ 
17. መቐለ 
18. ሽረ 
19. ወልቂጤ 
20. አርባምንጭ 
21. ቦንጋ 
22. ሐዋሳ 
23. ሰመራ እና 
24. ጋምቤላ
25. ሰቆጣ ከተሞች በሚቀርባችሁ አካባቢ በመሄድ እንድትመዘገቡ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ 
በመሆኑም ተሳታፊዎች ከጥር 5 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ባሉት ቀናት ተገኝታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በስልጠናው ለመሳተፍ ብቁ የሚያደርጉ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፡-
1ኛ. ማንኛውም ሰልጣኝ ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ይዞ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በአካል በአቅራቢያው በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ መመዝገብ ይኖርበታል፣
2ኛ. ሰልጣኞች የትምህርት ዝግጅታቸው ቢያንስ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወይም በቀድሞው የ10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወይም በአሁኑ የ12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብሎ በንግድ ስራ ላይ ቢያንስ ሶስት ዓመት ሲሰሩ የቆዩ ሆነው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በማቅረብ ስልጠናውን መሳተፍ የሚችል፣
3ኛ. ሰልጣኙ በግል፣ በሽርክና ወይም በአክሲዮን ተደራጅቶ ለመስራት ፍላጎት፣
4ኛ. ሰልጣኙ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳያቋርጥ መሰልጠን ይጠበቅበታል፣
በተጨማሪ ከአሁን ቀደም በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ተመርቃችሁ በህብረት ስራ ኮሚሽን በኩል ምዝገባ ያካሄዳችሁ በሙሉ በአራተኛው ዙር ስልጠና መሳትፍ ስለሚጠበቅባቸው በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፎች በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
ባንካችን በቀጣይ የሚሰጣቸውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመጠቀም የተዘጋጃችሁ እና የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሆናችሁ ስልጠና መውሰድ የምትፈልጉ በሙሉ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች በመገኘትና በመመዝገብ ስልጠናውን መሳተፍ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡ 
ማሳሳቢያ
ስልጠናውን ለአምስት ተከታታይ ቀናት ያልወሰደ ለሰርተፊኬት ብቁ አይሆንም፡፡
ባንኩ አዲስ ያቀረበውን የአክሲዎን አማራጭ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን በባንካችን የማህበራዊ ትስስር ገጾች አልያም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ የምታገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
           የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
               የልማት አጋርዎ!


For all those who want to participate in the fourth round of training for small and medium enterprises
The Ethiopian Development Bank is expanding its reach and increasing the number of districts from 12 to 24 and the number of branches to 108. It has completed its preparation to give training to enterprises for the fourth time in the half of the year 2015
Our bank has been working keeping in mind the growing number of trainees in mind. Our bank has completed its preparation to conduct registration for the fourth round of training in different branches of the bank found in 24 cities.
Participants to register to take the training from January 06 to 16 2015 E.C. In the coming days, including weekends, in all cities of the country, Ethiopia Development Bank's 108 branches found under districts.
1. In Addis Ababa
2. Gondar
3. Bahir Dar
4. Dessie
5. Assosa
6. Debre Birhan
7. Neqemt
8. Humera
9. Jigjiga
10. Adama
11. Debremarkos
12. Wolayta Sodo
13. Jimma
14. Dire Dawa
15. Shashemene
16. Goba
17. Mekelle
18. Share
19. Wolkite
20. Arba Minch
21. Bonga
22. Hawassa
23. Semera and her husband
24. Gambella
25. Sekota cities, we invite you to go and register.
Therefore, participants from January 5 to February 15, 2015 E.C. We invite you to register on the following days including Saturday and Sunday.
Registration requirements that make you eligible to participate in the training:-
1st. Every trainee should have to register with evidence that shows his identity or his legal agent in person at the nearest bank branch.
2nd. Trainees must have at least completed their high school education or have completed their previous 10th grade or current 12th grade. However, those who have been in business for three years and can participate in the training by providing a legal business license.
3rd. The trainee is willing to work individually, in partnership or in an organization.
4th. The trainer is supposed to train for five consecutive days.