Get Mystery Box with random crypto!

Fano Media Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ fanomedianetwork — Fano Media Network F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fanomedianetwork — Fano Media Network
የሰርጥ አድራሻ: @fanomedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.49K
የሰርጥ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ ከእጥፋት እና ከመከራ
መውጫ መንገድ ፋኖነት ብቻ ነው!!!
ፋኖነት የአባቶቻችን ውርስ መንገድ ነው።
@FanoMediaNetwork

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-03 15:45:31 በዓድዋ በዓል ላይ የጸጥታ ኃይሎች በፈጸሙት ድርጊት ተጠያቂ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ፡፡

በ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ በመንግሥት የጸጥታ አካላት የተፈጠረውን ችግር አስመለክቶ ባወጣው መግለጫ፣ የጸጥታ ኃይሎች ከገደብ ያለፈ ድርጊት ፈጽመዋል ብሏል፡፡

በበዓሉ ላይ አላስፈላጊ ኃይል የተጠቀሙ እና ከመጠን ያለፈ እርምጃ የወሰዱ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በሕግ ተጠያቂ ከመሆናቸው በተጨማሪ በሕግ አስከባሪዎች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ፣ በበዓሉ ላይ የተከሰቱትን ክስተቶች አስመልክተው በሰጡት ሀሳብ፣  የጸጥታ ኃይሎች በዓሉን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ከልክ ያለፈ አላስፈላጊ ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ ጥይትና ሌሎች ከመጠን ያለፉ እምጃዎችን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተወሰደው እርምጃ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችና ህጻናት ሳይቀሩ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ጠቅሰው፣ ቢያንስ አንድ ሰው መገደሉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

በርካታ ሰዎችም የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ኮሚሽነሩ አክለዋል፡፡

በምኒልክ አደባባይ የዓድዋን ድል ለማክበር፣ እንዲሁም በአቅራቢያው በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን  ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር የተሰበሰበው ሕዝብ  በኃይል መበተኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

@FanoNetwork
850 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:28:53
925 views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:28:27 #ተፈተዋል!

ታጋይ አሸናፊ አካሉ ፣ የአርበኛ #ዘመነ ካሴ ሹፌር ዘሪሁን አወቀ እና የዘመነ የእህት ልጅ ፍታለው በዋስትና ከእስር ተፈተዋል ሲል ጠበቃ ህሩይ ባዬ ተናግረዋል።

   እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ።

@FanoNetwork
915 viewsedited  11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 11:43:20
1.0K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 11:43:14 ትናንት በዓሉን በማክበር ላይ የነበረን ወጣት በአፈሙዝ ወግቶ የጣለው የኦሮሚያ ፖሊስ ነው። ምስሉ እየተፈፀመ ያለውን ነውር የሚገልፅ ነው። ጥላቻቸውን የሚገልፅ ነው። እብሪታቸውን የሚገልፅ ነው። ችግር ፈጣሪ እያሉ የሚከሱበትን ውሸታቸውን በደንብ የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያን ታሪክና እሴት እንዴት እንደሚፀየፉት ማሳያ ነው።

በነገራችን ላይ ለአዲስ አበባ ፖሊስ እየተባለ የመጣላት ችግር በተፈጠረ ቁጥር ንፁሃንን የሚገድለው መንጋ ነው።

ህዝብ በሚከፍለው ግብር የሚተዳደር የፖሊስ ተቋም እንዲህ አይነት አረመኔ ነው ህዝብ ላይ የሚያሰማራው። የተሰማራው የገዥዎቹን አስተሳሰብና እቅድ ይዞ እንጅ በግሉ አይደለም።
1.0K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ