Get Mystery Box with random crypto!

ምዕራፍ 13 ፋና ላምሮት ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

ምዕራፍ 13 ፋና ላምሮት ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል


አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት ባለ ተሰጥኦ ድምፃውያን ዛሬ በምዕራፍ 13 ፋና ላምሮት የፍጻሜ ውድድር ትልቁን ሽልማት ለማግኘት ይወዳደራሉ።

በፋና ላምሮት የባለ ተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍጻሜ ተፋላሚዎች የቀረበው የገንዘብ ሽልማት መጠን 1 ሚሊየን ብር ሆኗል።

በዛሬው የፍጻሜ ውድድርም ሐብታሙ ይሄነው፣ ግርማ ሞገስ፣ በረከት ደሞዝ እና ዘውዱ አበበ በፍጻሜ ውድድሩ ከፍተኛው ሽልማት ለመውሰድ ይወዳደራሉ።

በዛሬው ፍጻሜ የባለተሰጥዖ ድምፃውያን የፍፃሜ ውድድር ላይ ተፋላሚዎቹ ከዛየን ባንድ ጋር ይነግሳሉ፡፡

ውድድሩ በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ሲሆን፥ ተወዳዳሪዎቹ የሙዚቃ ሥራቸውን በሶስት ዙር ያቀርባሉ፡፡

በዕለቱ ከመደበኛ ዳኞች በተጨማሪ አንድ አንጋፋ እና ተወዳጅ ድምፃዊ በእንግዳነት በመገኘት ውድድሩን ይዳኛል።

ከዚህ ቀደም በየምዕራፉ 500 ሺህ ብር ይካፈሉ የነበሩት የፍፃሜ ተፋላሚዎች አሁን ሽልማታቸው ወደ 1 ሚሊየን ብር ከፍ ብሏል።

በውድድሩ ÷ 1ኛ ደረጃ ይዞ የሚያጠናቅቀው 400 ሺህ ብር
2ኛ ደረጃ ይዞ የሚያጠናቅቀው 300 ሺህ ብር
3ኛ ይዞ የሚያጠናቅቀው 200 ሺህ ብር እንዲሁም
4ኛ ደረጃ ይዞ የሚያጠናቅቀው ተወዳዳሪ ደግሞ የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።

የዛሬ የፍጻሜ ተፋላሚዎች በቀጣይ ማለትም በምዕራፍ 14 እና 15 ለፍፃሜ ከሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ጋርም ዳግም በአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ይመለሳሉ።

አድማጭ ተመልካቾችም በፋና ቴሌቪዥን በዕለቱ የሚገለጸውን የተወዳዳሪዎችን ኮድ በ8222 በመላክ አሸናፊ መሆን ይገባዋል የሚሉትን መምረጥ ይችላሉ።