Get Mystery Box with random crypto!

ኑዛዜ አቤቱ ጌታዬ ሆይ በጣም ደከምኩኝ ከኅጢአት ጋር ግብግብ አዛለኝ እምነቴም ሲፈተን ተሰማኝ ው | GRACE FAMILY

ኑዛዜ

አቤቱ ጌታዬ ሆይ በጣም ደከምኩኝ ከኅጢአት ጋር ግብግብ አዛለኝ እምነቴም ሲፈተን ተሰማኝ ውስጤ ሰላም በማጣቱ ተንኮታኩቻለው ድሮ የነበረኝ ግለት አሁን ላይ የት እንደገባ ግራ ገብቶኛል

ዳዊት እንደፀለየው "የማዳንህን ደስታ መልስልኝ" ብዬ እኔም እቃትታለው ያኑን ግለት በራሴ ልመልሰው እንዲሁ እጣጣራለው ግን ጌታ ሆይ ፈፅሞ አልቻልኩም አው ጌታዬ ሆይ በራሴ እንደማልችል በደምብ ተረድቼአለው

ደሞስ ክርስትናስ እኔ አልችልም ማለት አይደለምን? ምርኩዜ ሆይ ለመቆም ዝያለውና እባክህን በምህረትህ ድገፈኝ ወናነት ሲሰማኝ በሀልወትህ ሙላኝ ባዶነቴን ምትሞላልኝ ብቸኛ መድህኔ አንተ ነህና ዝም አትበለኝ

ደሬ እንደዘመረው አክሊሌን በደምህ እንድሽሸገው እርዳኝ የቆሰለው ልቤን በቁስልህ አክምልኝ የተዋረደን ልብ ስጠኝ ጉልበቶቼን ከዙፋንህ ደጆች ጋር አጣብቅልኝ ሌላ ሌላ እንዳላይ ለአይኖቼ ልጓም አበጅላቸው

ትምክህቴ ሆይ እመካብሀለው ፈፅሞ እንደማትጥለኝ አስረግጬ አውቃለው ግን ዝም ያልከኝ ሲመስለኝ ልቤ ይጨነቃልና በማስተዋል እንድመላለስ በእርጋታ መቀመጥ እንድችል አቤቱ ጌታዬ እርዳኝ