Get Mystery Box with random crypto!

ምስጋና... 'I need a reason to sing' was a line I heard as a kid | GRACE FAMILY

ምስጋና...

"I need a reason to sing" was a line I heard as a kid in a song. ክርስቲያን ስለመዘመርያ ሰበብ በእኛም ሀገር የሚጠቅሰውን ስናይ ምስጋና የፀሎት መክፈቻና ልዩ ለምንላቸው ትልልቅ ስኬቶች የምንከፍለው እዳ ወድያ እምብዛም የገባን ነገር አለመሆኑ ይታያል። 

"What can miserable Christians sing?"was an offensively true line I read somewhere. I hated how I related to it. Despite the misery in the world a Christian must fight for joy in God. And the joy of the Lord is our strength.

ስለመዝሙር ከተነሳ ክርስቲያን የሚዘምርበት ምክኒያት እልፍ ነው። መዝሙራችን የህይወታችን ነፀብራቅ ነውና ስለምድራዊ ኮተት ብቻ ካዜምን ምድራዊ ምቾት ማጣት ምስጋናችንን ይዘርፈዋል። በእርግጥ ስለ ለጋስ ስጦታውና መግቦቱ የሚያወሱ መዝሙሮች ሚና እንዳላቸው በቃሉ እናያለን።

".. ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ? .... አሁንስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል... (1ኛ ቆሮ 4:7) የምንፈልገው ነገር ሁሉ ባይኖረንም እግዚአብሔር ለመረጠልን ህይወት የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል። 

Everything we own, every friend, family, every pastor or significant person in your life has been a gift of God to you. You might think you are just likable because of your personality. Where do you think you got that from? Cant you see that God can take it all away in a heart beat ?

You might think you own stuff and take care of your health because you work hard to earn money but where do you think your energy , skill and creativity come from? Do you realize that God can just deprive you of sleep and that alone is enough to exhaust you enough to end your life let alone your job?

Our lives are filled with common grace. ለሚረግሙት፣ ለሚሰድቡት፣ ህልውናውን ለሚክዱት፣ በስሙ ምለው ለሚያጭበረብሩትም ሁሉ ከቸርነቱ እስትንፋስን ይቀጥላል፣ ፀሀይን ያወጣል። ቤቲ ተዘራ ስትዘምር
"ቸር ባይሆን ባለምህረት
አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት" እንዳለችው።

ውለታውን እየቆጠርን ማመስገን ስንጀምር ከህይወት ያጣነውን ነገር እያሰብን መነጫነጭ እንቀንሳለው። ደስታና እርካታን ፍለጋ የሚዞር ሰው ደስታ ይገባኛል፣ ከእግዚአብሔር በጎ እንጂ ክፉን አልቀበልም ብሎ የሚያምፅ ፀጋ ያልገባው ትዕቢተኛና ፈጣሪን በከንቱ ለማስገደድ የሚጥር ተላላ ነው።

 ከራዕይ 5:9 ላይ “..ምክንያቱም ታርደሃል" የሚለው የመላዕክት መዝሙር ሸለቆውንም ተራራውንም የሚያሳልፍ ፋሽን የማያልፍበት መዝሙር ነው። ሀጥያት ያላወቀው ለኛ ሀጥያት ታርዷል። ሰንበት በመጣ ቁጥር ትንሳዔውን እያሰብን እልል እንበል..መክፈል የማንችለው ዕዳ የተሻረልን ፣ ያልለፋንበት ፅድቅ የተቆጠረልን ፣ የማንረባ ሳለን እግዚአብሔር በልጁ የተወዳጀን ሁሉ የሁሌ መዝሙር አለን።