Get Mystery Box with random crypto!

ጤና  ይስጥልኝ  ወላጆች  የሁለተኛ መንፈቅ አመት የማጠቃለያ ፈተና  ከአርብ  ሰኔ 16 - ሰኔ | Falcon Grade 11Natural 2015 E.C

ጤና  ይስጥልኝ  ወላጆች 
የሁለተኛ መንፈቅ አመት የማጠቃለያ ፈተና  ከአርብ  ሰኔ 16 - ሰኔ 23/2015ዓ.ም  ተማሪዎቻችንን ለመፈተን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ቀኑን እየጠበቅን እንገኛለን :: ለፈተና ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ነገ ሐሙስ 15/10/2015 ዓ.ም ት/ርት ዝግ ይሆናል። አቅደን  ዓርብ 16/10/2015 ዓ.ም ፈተናው የሚጀምር ሲሆን 9ኛ እና 10 ኛ የጠዋት ፈረቃ ተፈታኝ ሲሆኑ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የከሰዓት ፈረቃ ተፈተኞች ይሆናሉ። ከተፈታኝ ተማሪዎች የሚጠበቁ ተግባራት
1ኛ - ለፈተና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ይዞ መምጣት
2ኛ - ዩኒፎም እና ፀጉርን ተስተካክሎ ት/ቤት መምጣት
3 ኛ - ሰዓትን አክብሮ ት/ቤት መገኘት ይኸውም የጠዋት ፈተና 2:00 - 5:00 ሲሆን
የከሰዓት ፈረቃ ከ 7፡ዐዐ - 9:30 ይሆናል ::
4ኛ - ከፈተና ፈረቃ ወጪ ት/ቤት መገኘት አይቻልም።
5ኛ- ፈተናው የሚሰጥባቸው ቀናት ዓርብ (16/10/2015 ዓ.ም)፤ ሰኞ (19/10/2015 ዓ.ም)፤ ማክሰኞ (20/10/2015 ዓ.ም) እንዲሁም ዓርብ (23/10/2015 ዓ.ም) ናቸው።
6ኛ- የፈተና ወረቀት ታርሞ ለተማሪዎች የሚመለሰው ሰኞ (26/10/2015 ዓ.ም) ይሆናል ::
ኪዳኔ ብርሃኔ ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ስራ ሒደት መሪ