Get Mystery Box with random crypto!

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

የቴሌግራም ቻናል አርማ faiza_kiza — ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗
የቴሌግራም ቻናል አርማ faiza_kiza — ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗
የሰርጥ አድራሻ: @faiza_kiza
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.22K
የሰርጥ መግለጫ

ማወቅን ማወቅ ፣አለማወቅን ማወቅ ፣አለማወቅን አለማወቅ ፣ማወቅን አለማወቅ፣ አለማወቅን ማወቅ ነዉ፡፡ (sokrats ) @faiza_kiza
በብዕር እንነሳለን በብዕር እንዘቅጣለን በብዕር እናድጋለን 👍🥰
አስተያየቶቻችሁን በ @mornin_bot አድርሱኝ
Support me on https://jami.bio/faiza

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-30 13:43:55 #ተነድፈሽ_ክበሪ
:
:
እኔ አልነደፍም የሚለው ፉከራ
በገዛ አንደበትሽ በኩራት ሲወራ
ካንዴም አስር ጊዜ ደርሶ ሰምቻለው
ትክክል ነው ብሎም የሚያጎበጉብ ሰው በቅርብ አይቻለው።
:
:
እውነት ነው ወይ ብዬም በዙሪያሽ ያሉትን ዞሬ ሳጤናቸው
መላከፍ ነው እንጂ መንደፍ የማይችሉ ተራ ዝንቦች ናቸው።
:
:
አፍኜው ነው እንጂ ድሮም ያንቺ ነገር ያንገበግበኛል
ከንቱ ፉጨት ከቦሽ መኩራትሽ ገርሞኛል።
:
:
ከ ዐጀቦችሽ አንፃር መደምደምሽን ሳይ አናገረኝ እንጂ የሆዴ መከፋት
ባንቺ አልተጀመረም አደባባይ ቆሞ በጀሌ ተከቦ አጉል ጉራ መንፋት።
:
:
እውነት እውነት ስልሽ ያለመነደፍሽን ሚስጥሩን ላወቀው
ልክ እንደኔ ሁሉ ሆድ ቢብሰው እንጂ ቅንጣትም አይደንቀው።
:
:
ይልቁን አንቺ ሴት አንዣባቢሽ በዝቶ እንዳትዘናጊ
የማሩን እንጀራም ያንቺ እንድታደርጊ
ተነድፎ ለመክበር በይ ከንብ ተጠጊ።



#Semir ami
780 viewsسمير ايمي, 10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 16:02:46
ማሻአላህ የኸዉፈላህ ጀመአ እኛስ ከማን እናንሳለን ብለዉ ፆመኛን የማስፈጠር ፕሮግራም በነገው ለት ይዘዉ የፆመኛዉን መምጣት በመጠባበቅ ላይ ናቸው


አንቀርም እንመጣለን


አዘጋጅ:ኸዉፈላህ ጀመአ
890 viewsسمير ايمي, 13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 00:22:13 ሄዶን

_ከርሞ ጥጃ

ከማን ነው የምማር
ህይወትን መቀኘት?
ሀቅን አዘርፎ
በፍሬ መሸኘት?

መቼ ነው ሚ'ቀባኝ
እውነት ቀለማቱን?
መቼ ነው ሚሰጠኝ
እውነት ነፃነቱን?
ንቃቴን ሚያነጥፍ
አቁሞ ጊዚያቱን?

መች ነው ሚ'በጅለት
ለስሜቴ ልጓም?
መባተሌ ሚቀር
አንዷጋም አንዷጋም?

አውቆ አበድ ገላዬ
ከርሞም ለጋ ጥጃ
ሲያቆስል ይኖራል
ላቆሰሉት ፍርጃ።?

( እኔ እንጃ!! ) ...



ሄዶን @merekkk




╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza
785 viewsBell, 21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 20:02:27 #እምዬ እህት አለም#ያልታደለች
(በገጣሚ #ሰሚር ወለዬ

እምዬ ያልታደለች
ተመዘኚ ሲሏት ~ መዛኝ ነኝ ትላለች
እምዬ ሰከረች
ልትመዘን ወጥታ ~ መዛኝ ሆና ቀረች!
የቅቤን ስብራት ~ በቅመም ለማከም
በወቀጣ መዛል ~ በድለዛ መድከም
የቅቤን ወለምታ ~ በቅመም ለማሸት
ሲደቁሱ አድረው ~ ሲቀይጡ ማምሸት
የቅቤን ጉብዝና ~ በቅመም ለማትጋት
እያመሱ መዋል ~ እየፈጩ ማንጋት
* * *
ይልቅ ግድ የለሽም !
ለቅቤ ጥፍጥና
ለቅቤ መአዛ
ቅመም ከመደቆስ ~ ቅመም ከማበጠር
ከቅቤያችን በፊት ~ ከብቶቹን ነው ማንጠር
እንስራ ወዝውዞ
በጢሳጢስ ናውዞ
ለቅቤ ከማማጥ ~ ለአይብ ከማማጥ
ከወተቱ በፊት ~ እስቲ ላሟ ትናጥ
ማለቢያ ከማስፋት ~ ማለቢያ ከማጥበብ
ከግቷ አስቀድሞ
ከሆዷ አስቀድሞ ~ ምግቧን ነው ማጠብ
* * *
ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ
እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ
እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ
ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ !
* * *
ግራ ነኝ ይለኛል
ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል
ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል?
እውቀት አባ አያልቄ
እውቀት አባ አይፈሬ — ጥያቄ ሲያድለው
ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው
ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው
መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው
* * *
እይዉ!
ሰው መጠየቅ ትቷል
ሰው ፍለጋ ትቷል ~ ሰው ማጣጣም ትቷል
ለመንስኤ ዝሏል ~ ለአመክንዮ ታክቷል
በጥድፊያ ሊያስታግስ~የመሰንበት ሱሱን
ጥያቄ ነው ይላል ~ የከሸፈ መልሱን
ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት
መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት
መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት
* * *
ኩሬ ነው?
ወንዝ ነው?
ሃይቅ ነው?
ባህር ነው? ጎርፍ ነው?
ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ?
አዞ አለ? አሳ አለ?
.
.
እኮ የምን ጥያቄ ! ~ እኮ የምን ክርክር !
በቃ!
“ዋና ነው!” ይልሽና ~ ከነልብሱ ንክር።
አዎ!
“ዋና ነው!” ይልሻል ~ “አጨብጭቢ!” ይልሻል
“ዋናህስ?” አትበይው
አሽሟጠጠች ብሎ ~ ችሎት ያቆምሻል
ያው!
ችሎቱ የእነሱ — ችሎታው የሌላ
ይልቅ አጨብጭቢ —አዞ እራቱን ይብላ!
ለንክር ጭብጨባ —ለዝፍዝፍ ጭብጨባ
ሆዱ አሳ ሲለው — አዞ ለሚያረባ
* * *
ተመልከች!
ሽንቁራም እውቀትሽ —ንፋሱን ሲነዛ
ከጋላቢሽ ይልቅ —የሚገለብ በዛ
ንፋሳም እውቀትሽ —ውርጩን እየነዛ
ከሚያነደው ይልቅ —የሚያከስለው በዛ
ግልብልብ እውቀትሽ —ወላፈን ደሞዙ
የሚለበለቡት — ከሚበስሉት በዙ።
እይው!
ማእዘን አፍርሶ —ግድግዳ እያደሰ
ወለሉን ሰውቶ —ጣሪያ እየቀለሰ
ቅርንጫፍ ሊያሳምር —ስር እየበጠሰ
እልፍኝ ተደፈረ —አጥር ተገሰሰ
መስማት ጥንቡን —ጣለ ማየት ረከሰ
ቋንቋ መነመነ — ለትርጉም አነሰ
* * *
ቆይ እኔ የምልሽ!
ተፈጥሮ ሂደቷ — እንዲህ ሳይጓደል
ለመሮጥ መንደርደር — ግድ ነበር አይደል?!
ታዲያ! ቀረ እኮ ነው ‘ምልሽ
መንደርደር መመርመር መፈከር መዘርዘር
አኩርፈው የሄዱት — በየት በኩል ነበር?
* * *
የወል ቀማሽ ሁላ
ድፍርስ እየጠጣ — ሽርክት እየበላ
በግርድፍ አኝኮ — ለግርድፍ ተሻምቶ
“ውጫለሁ!” ይልሻል — ወደ ሆዱ ተፍቶ
* * *
የምር ደስ አይልም!
የጥርስን በአንጀት
የጆሮን በምላስ — ʻያፍንጫን በመዳፍ
ግብር እያቀማሙ — ዋጋና ስም መጻፍ
የምር ደስ አይልም!
የልብን ደረት ላይ
የነፍስን ልብስ ላይ— ቀያይጦ በማፍካት
ጣእምን መመርመር — ውበትን መለካት
ደስስስስስ አይልም!
* * *
እምዬ!
አትላፊ አትዳሪ ከእንክርዳድሽ
ይልቅ
ወንፊት ግዢ ለወንፊትሽ
ሰፌድ ግዢ ለሰፌድሽ
* * *
ቀማሽ ሲደራረብ —ጣእም ተቀያየጠ
ባለቤት ሳያጌጥ —ውበት አመለጠ
ከእህሉም አይደለ
ከቅመሙም አይደል
ጨው አንሶም አይደለ
የምላስ ህመም —ነው ጣእም የገደለ
* * *
ምን አረገሽና!
ቀቃዩ ጠባሹ
ከታፊው አማሹ
ወቃጩ ነስናሹ
ለርካሽነትሽ — ይጠየቅ ቀማሹ
ማገዶ ቢራቀቅ
ምጣድ ቢቀያየር — ጋጋሪ ቢንጋጋ
በቀማሽ ልክ ነው —የገበታሽ ዋጋ
* * *
ኧረ ሚዛን! ሚዛን!
ኧረ መዛኝ! መዛኝ!
በልክ የሚሰፍር በልክ የሚገዛኝ!
እንደየቃናችን — ማድመቅ ያላወቀ
ቀማሽ አሳነሰን — እያደባለቀ!!!
====||====


(በገጣሚ # ሰሚር አሚ
668 viewsسمير ايمي, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 17:00:03 ☞ ዝክረ ኸሚስ #6
-
መሀባ
-
አንዳንዶቻችን መሀባ ፍቅር የሁሉም ነገር ጅማሮ ፣ የመድረስ ሁሉ መነሻው እንደሆነ
ዘንግተነዋል ። እንኳን የሰው ልጅ ቀርቶ የእህል ቡሆ ‘ንኳ ለምጣድ ቢደርስም ሙሀቻው
እርሾ አይኖረውም ። " ኺትማ ድረስ ያልዘለቀ እንኳን መሀባ ቡንም ደግ አይደለም ። "
ብላናለች ሙሂቧ አቲቃችን ... መሀባ የደግ እድል በር ነው ። የሸጋ እጣ ደጃፍ ነው ፣
የእህል ውሃ መፍለቅለቂያ የዱንያ ሰታቴዋ ነው ። ተውበትን ( ንሰሃን ) ማስታወሻ ነው ።
የተጥራራ ኒያ ሸጋ ሀርፍ ፈትሎ " ያረሂም " የሚያስለፈልፍ ያብጀልኝ ደጅህን ማዜሚያ ነው ።
የጀነት መሻገሪያው መሰላልም .... መሀባ ፣ ፍቅር ።
---
.
ወቅቱን ነው አሉ ።
.
ያ የጎጋ ቅኝት ፣
በቁርበቱ ዜማ ፣
በደግ እድል በሩ ፣
በእጣው ጆሮ ግርጌ ፣
ተንጓጉቶ አንዳልነበር የገረረው ለዝቦ የጠናው ገራለት፣
ዱንያ አውታሩ ብዙ ስልት እየለወጠ ለስልሶ አዜመለት።
.
( ማነው ? አይባልም ... ! )
.
ካልሆነም ንጋቱ ፣
ካልገጠመም ምሽት ፣
ታጓጉል እሮሮ አፍታ ሳያላዝን ፣
ቀን ሰባራ ፍርዱን በመሀባ ፈጅር ይንጋልኝ እያለው፣
ሰው ብሎ ያለው ነው ... የመቸሩ ጤዛ ደጁን የበቀለው።
----
አንደዎ ሸህ ናቸው ። ደረሳቸውን ለሽንታቸው ማዳረቂያ ( ለኢስቲብራዕ ) የሚሆን ጠጠር
ድንጋይ ይዞላቸው እንዲመጣ አዘዙት አሉ ። ደረሳውም በጠጠሩ ፋንታ ትልልቅ ድንጋይ
በትክሻው ተሸክሞ መጣና ፊታቸው ላይ አስቀመጠው ። የዛኔ ሸህዮው " ኧረ አኸይ ምነው
አንተዬ ይህንን ምን ላደርገው ነው ለመቀመጫ አላልኩህ " ሲሉት « እነሸህ ላንቱ ትንሽ
ነገር እንደት ብየ ይዤ ልምጣ ! » ብሎ መለሰላቸው አሉ ። # መሀባ

አባቴም እንዲህ ሲሉ አዳምጫለሁ ። አንድ ቀን ከቁርአን ቤት ሸሆቹ ገርፈውኝ እያለቀስኩ
ቤት ገባሁ ። ምን ሆነህ ነው ? ተባልኩ ። " ሉህህን ከትክሻ ለምን አወረድክ ብለው መቱኝ "
አልኩ አቀርቅሬ ። ( ሉህ ) ከእንጨት የተሰራች መድ ቀለም እያጠቀሱ በሽንበቆ ስንጣሪ
ገላዋ ላይ ተከትቦባት ተፅፎባት ጀማሪ ልጅ አሊፍ ብሎ የሚቀራባት ማንበቢያ ናት ።
ጠፍጠፋ ሆና ከጫፍ እና ከጫፏ ተቦርቡራ ገመድ ገብቶባት ከትክሻ ትንጠለጠላለች ።
አባቴም እንዲህ አሉኝ ። « እኔ በደረስነቴ በሸሆቹ ብትር አላለቅስም ። የሸሆቹ ብትር
ያሳድጋል ። የትልቅ ሰው ቁጣ በረካ አለው ። » ካሉኝ ቡሀላ አብሯቸውቤት ለተቀመጠው
ሰው እንዲህ አሉት ። « ምን የዛሬ ልጅ አዳብ የላቸው ። እኛ ስንቀራ ሸሆቻችን ካላዋጡን
ቂረዐቱ አይያዘንም ነበር ። » ሱብሃነሏህ ... # መሀባ
----
መሀባ የሰውነት ግንዱ ዛፉ ነው ፣ ሓድራ ቅርንጫፉ ጥላው ነው ። ሓድራም ገበያ ነው
ያደባልቃል ። እንደኒያችን እንደቅዋችን የነፍስ ቀለብ የምንሸምትበት ። ሸሬታው ኸለዋ
መጅሊስ ነው ። እገሌ ተገሌ በሚል መኩራራት ሆሳ ጥላ ሓድራ ታዛውን አይዞርበትም ።
የእኔ እንዲህ ነኝ የሚል የመኮፈስ አዛ ጠለሽ ሓድራ ቀዬውን አይጥልበትም ። ሰው በመሆን
ብቻ በመርሀባ አደጌር የሚታደሙባት የፍቅር ሰርግ ያብሮነት ድግስ ነው ። ተጥራርተው
ለአቅል የሶብር ውዱእን ተጅዲድ ( እድሳት ) የሚፈጠምባት የቀልብ ወጌሻነትም ዳኢም
አሺት ነው .... መሀባ ።
.
ዛሬ ዛሬ የሓድራን ልቅና ፣ የመሀባን ደረጃ ፣ የምናይበት መልኩ ያበግናል ። « ታልደረሱ
አይደረስም ! » ቢሆንም ነገሩ ፣ ግን ክረምቱን ሳያዩት ስለወንዙ አካሄድ ያለሸርጡ ያለሃቁ
በራስ ቢሆን ግልብ የፈትዋ ኩሬ እንቀላቅልበት ማለቱን ስንሰማ ። አንዲት የዘማቾች
የሓድራ ስንኝ ድንቅ ትልብናለች በጫሌ ቀበሌ ነው ።
አርሂብ ተብሎ ደግ ሳይታደም ፣
ሓድራ አይገባም በመቀዳደም ።
-
ግደለም ሰው ማለት አያከስርም ጎበዝ ። አተረፈ አሉ ። ማን ? " ሰው ብሎ የገበየ " መገን
። .... ይቅናን ያቀናን ። መሀባም ሓድራ ነውና ቅሉ የገባያም ገድ አለውና .... ተገዱ
ሳይታገዱ የወንድም ቁናው ላይንገረበብ ቲም ያለው ሂድያ ይስጠን ። # አሚን
.
ሀቢቢ ... ረሱል ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል « አንድ ወንድሙ የሚወደውን
ነገር በማግኘቱ መደሰቱን የገለፀለት ሰው የትንሣኤ ቀን ልእልናው ከፍ ያለ አላህ
ያስደስተዋል »
« መልካምን ነገርን ትንሽ ናት ብለህ አትናቅ ።
ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘት ቢሆንም እንኳ » ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙን ሲያገኝ
እሱን በማግኘቱ ብቻ
ከምንም በላይ መደሠትና ደስ መሰኘቱንም በፊቱ ላይ
ማስነበብ ይኖርበታል ። የወንድም የወዳጅ ሀቁን ስንቶቻችን እናውቀዋለን ።
-----
ያረብ
።።።።።።
በአሪፎች ቅልስ ... ከውንህ ይሞጠላል ፣
በተቅዬች ግርዶሽ ... ሀምድ ይንከባለላል ፣
ያመሰጋኝህ ግብር
መርሀባን ሲታደል ...
ቀኑን ሊደላደል - - ምንዳው ሲሞናደል ...
እዝነትህ ሲዘንበው - - በረካህ ሲጎርፈው፣
ሰው ብሎ ይተማል ነፍስያ ሳይጠልፈው።
..
ምናለ ጌትዬ ...
.
ስለሰው ብባባው ፣
ስለሰው ባነባው ፣
ነክሮኝ ብንቧችበት - - ባህሩን ብዋኝበት ...
ሰው ብሎ ሰው ሊሆን ሰውነት ካለበት ።
ምናለ ...
( እኔም በተመኔ በቀኔ ብቃና ... ! )
በገረረው ንጋት ...
ወዙ በተላሰ ድርቅና ሰንጥቆት በተፍረከረከው ፣
የሙሂቡን ኪታብ ገልጦ ካለመቅራት ...
አይኔን በገለጥከው - - ልሳኔን ባዳንከው ?!
ሓድራ መሀል ውዬ - - ሓድራ መሀል ባድር ፣
በቻልኩት ዘምቼ ፣
ከዘመኔ አልቦ ላይ - - የቀልቤን ብሰድር ?!
..
ኸሚስ አባ መደድ ፣
ኸሚስ አባ መውደድ ፣
የሓድራ ወናፉን ባድማሱ ሲያጋግም ፣
ምሽቱን ኮልኩሎ እየገሰገሰ ህዋው ሲያስገመግም፣
እየቀጠቀጠ ፣
ደግ እያቀለጠ ፣
ሆሳን ጊዜ ‘ንዲቆርጥ - - የዛገው ቀን ሊሳል ፣
ሞረድ ያዘለው ለይል ...
ሰው በሚል ቡራቁ ከሚኔው ይደርሳል ።
.
የዛኔ ...
ያን የማይሸርፈውን ፣
የመኣና ‘ጀታ አስጨብጠኝ አንተው ፣
ሰው ብዬ ቀን ስዬ ሰው ልሁን እንደሰው ።
..
ምናለ ጌትዬ ...
አንተ ላይሳንህ - - በትናንት መከለስ ፣
በሙሂቦች ቀለም - - በደግ መሰለስ ፣
( አኔም በተመኔ በቀኔ ብቃና ... ! )
በገረረው ንጋት ...
ወዙ በተላሰ ድርቅና ሰንጥቆት በተፍረከረከው ፣
የሙሂቡን ኪታብ ገልጦ ካለመቅራት ...
አይኔን በገለጥከው - - ልሳኔን ባዳንከው !?
ሓድራ መሀል ውዬ - - ሀድራ መሀል ባድር ፣
በቻልኩት ዘምቼ ...
ከዘመኔ አልቦ ላይ የቀልቤን ብሰድር ?!
..
ምናለ ... ?!
_
Semir ami


@semiraklu
626 viewsسمير ايمي, 14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 22:30:29 ሕያው

ምነው አግኝቼሽ በጓጓሁ
ምነው አፍቅሬሽ በሳሳሁ
ምነው ብስምሽ በደነዘዝኩ
ምነው ቢቀናኝ ልቤን ባዘዝኩ

ድንዛዜዬ ቢለይለት ለመቆም ቢያንገዳግደኝ
ጠረንሽ ከኔ ቢዋሀድ ያንቺ ማንነት ቢያውደኝ

ምነኛ ደግ ነበረ ገድዬ ነገ ባነሳሽ..

አሟሟት ብዙ ነው አውዱ
ሞቶ'ኮ አይሞትም አንዳንዱ..


◍ህያው @merekkk



╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza
641 viewsBell, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 08:35:33 ሕያው

ሰው ንቃቱን ያጣል.

ማጡ ጠለቅ ሲል..
የገባበት ስርጉድ አንዳቹን ሲያካልል..
ሰው ንቃቱን ያጣል.
ያበባው ውብ ውበት ስህበቱን ሸፍኖ እሾሁ ያገጣል.

በ'ሾህ ላይ ተራማጅ ሸካር የ'ግር መዳፍ.
መቆም ብርቁ አይደለም አያሻውም ግዳፍ.

ይቆማል እስካፍታ ጉሙ ተበታትኖ ፀሐዩዋን እስኪቃኝ.
እስከጊዜው ድረስ ሰው ንቃቱን ቢያጣም መች ያውቅና በቃኝ..

@faiza_kiza
758 viewsBell, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 19:48:35 #እባክሽ
:
:
ትናንት ባማን ደና በሚያስቀና ለዛ፣
ሆነን አቻ ላቻ ያበጀነው ታዛ፣
ቀን በገፋ ቁጥር የኋላ የኋላ፣
ዘመም እዳይልብን በዳዋ እንዳይበላ፣
ዘላለም እንዲከርም የልባችን ምግብ ሆኖ በአንድ ትሪ፣
ባክሽ የኔ ፍቅር ሰው መምሰሉን ትተሽ ሰው መሆን ጀምሪ።

#semir aklu


@faiza_kiza
@faiza_kiza
1.0K viewsImposible, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 19:39:25 ሄዶን

ትዝብት ነው እንጂ ኑሮሽን ስቃኘው
እንኳንስ ጎጆዬ አያውቅሽም ቀዬው
እያልኩ እፅፍ ነበር ለራሴ ስታመን
ካቤን እየናደ እስኪያነጥፈኝ ዘመን
ልፊ ብሎሽ እንጂ ድራማሽ የበዛ
ወትሮም ቅርበት የለን አንቺ እዛ እኔ እዛ
እያልኩ እፅፍ ነበር ቀኔን ቅን ሲወርሰው
ጠዓዳ ሸማዬን ጭስ እስከማለብሰው
ዛሬ...
ያልሆነው ሆነና ህግ እንግዳ ሆነ
አድር ባይ ለቃሉ ለገላው መነነ
ብቻ...
እውቀቱን አርክሶ ለስሜት ያደረ
የሰው ሴት ይመኛል ሚስቱን እየዳረ

ወይ ነዶ...



ሄዶን @merekkk




╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza
976 viewsBell, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 07:58:35 ወደድኩሼ
ናፈቅኩሼ
ዛሬም መጣሁ ተመልሼ
ብሼ ብሼ
ብሼ ብሼ
እስክነሳ አፈር ልሼ
ጊዜ ጠና እስኪለዝብ
የከሰመው እስከሚያብብ
ነኝ ያለችው እስክትወጣ
ያልኖረችው እስክትመጣ
ልደጉምሽ ተመልሼ
ወደድኩሼ
ናፈቅኩሼ....


ሄዶን @merekkk



╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza
825 viewsBell, 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ