Get Mystery Box with random crypto!

* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

* Confirmed

በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች በኩል ዝርዝሩን በተመለከተ በግልፅ ለህዝቡ ምንም ሳይባል ሰዓታት አልፈው ነበር።

ይህም አንዳንድ ሲሰራጩ የነበሩ የስምምነቱ " Draft " ወረቀቶች ትክክል ናቸው / ሀሰት ናቸው የሚሉ አካላትን ፈጥሯል።

ዛሬ ጥዋት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በሰላም ንግግሩ ተሳታፊ የሆኑት እና እዚህ የስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ብዙ የቡድን እልህ አስጨራሽ ክርክሮች ተደርጎ የተፈረመበት ያሉትን ትክክለኛውና ዝርዝር ስምምነቱን የያዘውን ወረቀት አሰራጭተዋል።

(አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በተረጋገጠ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያሰራጩት የስምምነቱን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ከላይ ተያይዟል)

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet