Get Mystery Box with random crypto!

በምዕራብ ሸዋ ዞን በባኮ ትቤት ወረዳ ስር የሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የኦነግ ሸኔ ሐይል | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

በምዕራብ ሸዋ ዞን በባኮ ትቤት ወረዳ ስር የሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የኦነግ ሸኔ ሐይል መሽጓል ሲሉ ኗሪዎች ለአጉልዞ ጥያቄ ገለፁ። በዚህም የተነሳ በሰሞኑ የባኮ ትቤ ወረዳ አስተዳደር በከተማዋ ለሚገኙ ማህበረሰብ የእራሳችሁን አትርፉ ተማጽኖ እያሰሙ ዛሬ ላይ በከበባ ውስጥ ሆነን እያሳለፍን ነው፤ የመንግስት አካል ተጨማሪ ሐይል በመላክ የባኮ ከተማ ኗሪዎችን ሊያተርፈን ይገባል ሲሉ ተማጸኑ።

በአሁኑ ሰዓት የባኮ ከተማን ለመውረር የተዘጋጀው የኦነግ ሸኔ አሸባሪ ቡድን በከተማዋ በዙሪያው በሚገኙት አከባቢዎች መሽጓል። ከመሸገባቸው አከባቢዎች መካከል ደግሞ፦
1- ጋጆ
2- ሸቦቃ
3- ለገኢያ (ምስራቅ ወለጋ ስር የምትገኝ ቀበሌ)
4- በጨራ እና
5- ባሪ አቦ ሲሆኑ መንግስት በአስቸኳይ በከተማዋ ከሚገኙት ተጨማሪ ሐይል ሊልክልን ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፏል።
ንስር ብሮድካስት

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet