Get Mystery Box with random crypto!

የአፈና ዜና…!! • 11 ካህናት ታግተዋል። • 1 ዲያቆን ተገድሏል። '…እዚሁ ነው። እዚሁ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የአፈና ዜና…!!

• 11 ካህናት ታግተዋል።
• 1 ዲያቆን ተገድሏል።

"…እዚሁ ነው። እዚሁ ቅርብ። አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ከአዲስ አበባ 150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በኩዩ ወረዳ ገርበ ጉራቻ ከተማ በምትገኘው ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመ ነው።

"…ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓም ቅዳሜ ሌሊት ካህናት ዲያቆናቱ የጽጌ ማኀሌት ቁመው ሳሉ ነበር የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የገቡት። ማኅሌቱን አስቆሙ። ወዲያው 1 ዲያቆንን ገደሉ። 11 ካህናትንም አፍነው ወሰዱ። የታፈኑቱ ካህናት እስካሁን የገቡበት የደረሱበትም አልታወቀም።

"…በሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት በርካታ ካህናት ተገድለዋል። አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል። በርካቶችም ታፍነዋል። በአካባቢው የሚታፈኑ ሰዎች ከ100 ሺ ብር አንሥቶ እስከ 2 ሚልዮን ድረስ ተመን ተተምኖባቸው ቤተሰብ የታፈኑትን ለማስለቀቅ ከፈለገ የተተመነውን ብር እንዲከፍሉ እንደሚደረግም ተሰምቷል። በዚህ መልክ ኦርቶዶክሳውያኑ ተራቁተው፣ ደህይተውም አካባቢውን መልቀቃቸው እየለቀቁ እንደሆነ ነው የሚሰማው። ለአፋኞቹ የሚከፈለው ገንዘብ በኦሮሚያ ባንክ መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን አስደማሚ ያደርገዋል።

ዘመድኩን በቀለ

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet