Get Mystery Box with random crypto!

የህወሓት የሽብር ቡድን ከያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ተጠየቀ የህ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የህወሓት የሽብር ቡድን ከያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ተጠየቀ

የህወሓት የሽብር ቡድን ከያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ አሳሰቡ።

የሽብር ቡድኑ ዳግመኛ ጦርነት መክፈትን የወቀሱት ሚኒስትሯ፣ የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን መተው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

ይህ ድርጊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን አደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑን ገልፀው ጦርነት ፈፅሞ መፍትሔ እንደማይሆን ሁለት ዓመት የተጠጋውን ጦርነት መገምገም ብቻ በቂ ነበር ብለዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም ይህንን ማገናዘብ ያልቻለው የሽብር ቡድኑ ጦርነት መጎሰሙን በማቆም እና የያዛቸውን የአማራ ክልል አካባቢዎች በመልቀቅ ለሰላም ፊቱን እንዲያዞር መክረዋል።

ጦርነቱ በትግራይ አማራ እና አፋር ክልሎች 13 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ሰብዓዊ እርዳታ ጠባቂዎች አድርጎቸዋል ያሉት ሚኒስትሯ፣ የህወሓት የሽብር ቡድን የዓለም የምግብ ፕሮግራምን ነዳጅ በመዝረፍ ለእኩይ ዓላማው ማዋሉም ለህዝቡ ደንታ ቢስ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet