Get Mystery Box with random crypto!

አፈ–ቅኔ ሄና

የቴሌግራም ቻናል አርማ eyetaye12 — አፈ–ቅኔ ሄና
የቴሌግራም ቻናል አርማ eyetaye12 — አፈ–ቅኔ ሄና
የሰርጥ አድራሻ: @eyetaye12
ምድቦች: ስነ ጥበብ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 137
የሰርጥ መግለጫ

ስማኝማ የሀገሬ ሰው
ወንድምህም ነው እኮ ሰው።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-21 05:18:56 አየኋት ሰገድኩኝ
አየኋት ተሳልኩኝ
አየኋት አየኋት
ተስዬ አገባኋት
አግብቼም አየኋት
አይቼ አልጠገብኩም
አሁንም መልሼ
ጭኗን ተንተርሼ
በጨረፍታ አየኋት
በአትኩሮት አየኋት
የኋሊት አየኋት
የፊትም አየኋት
ፊቷ አልተቀየረም
ምንም ስህተት የለም
ከእንቁ የምታምር
እፁብ ድንቅ ተዓምር
ከዛን ተደፋሁኝ
እሷን ማየት ልተው
ፈጣሪን ልጠይቅ
አይኔን ከሷ መንቀል ለምን እንዳቃተው?
ጌታ ግን ሳቀብኝ በፀሎቴ አስካካ
ስሩ ተደፍቼም ሳያት አይቷል ለካ
*------------------*

(ሚኪያስ ፈይሣ)

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
Share
122 views02:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11 የት ነበርሽ ??
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤

ህይወት ወጀብ
አገላብጣኝ ስብከነከን
ቀን ሲከፋ
ኢምንት በደል በኔ ሲገን
አካል ልቤ
ሰው ሰው ሰው ሲል
ናፍቆ ሲደብን...ባዛኝ አይኔ
ሺ ቢፈልግ ቢንከራተት
አጥቶሽ ነበር....
ግና ዛሬ ጭጋግ ያልኩት ድባብ ሲሸሽ
ኦና ቤቴ በሰው አጀብ
ሲምነሸነሽ
ዳግም ስቄ ፊቴ ፈክቶ ስውል ሳመሽ
ከደጃፌ ከበራፌ
አየው ቆመሽ..አዪዪዪ
ግድ የለውም
ጊቢ አለሜ ከትላንቱ የተረፈ ቅንጣት ፍቅር
በጥያቄ ተለውሶ
ከልቤ አለሽ..እስቲ አጫውችኝ
እንዲያ ስሆን ስፈልግሽ ወዴት ነበርሽ ?
:
በአንዱ ጉያ ክንድ ታቅፈሽ
ውብ ደረቱን ተደግፈሽ
ደጃች ውቤ ከሞቀው ቤት
እየደነስሽ...?

ወይስ ከሰው ተከልለሽ
ጭንቄን ላታይ በሳግ በዕምባ እየታጠብሽ
ከአራዳ ሰማዕቱ ደጅ
እየጸለይሽ...?

ወዴት ነበርሽ ?

/ ኪዮርና /

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
84 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11 እተዋት ይሆናል ሰው ሌላ አስተዋውቁኝ
እረሳት ይሆናል ከቆንጆ አለማምዱኝ
ቸገረኝ መርሳቱ ቅጡን እያጣብኝ

አምስት አመት ሆነኝ በፍቅሯ ስሰቃይ
በግልፅ ሀገር አውቆ መውደዴ እሰከሚታይ
ሀገሯ ዋሳ ነው ቆንጆ ከሞላበት
መርሻ አንዷን ስጡኝ የምታከምበት
እድሜዬ አለቀ እሷን ሳስብበት
ሀብት ነዋይ ጠፋ ስሽቀረቀርበት
እሷን ለማማል የትም ስዘራበት


የጉዴ ጉድማ ትንሹ
የደሀ ለማኝ ነኝ በስሱ
የጉዴ ጉድማ ጥቂቱ
ሌላው አፈሰሽ በአይነቱ
በምላስ ሸንግሎሽ በምናብ
አፈሰሽ ወስበሀት ለአብ
ሰዉ መርዝ ሆኗል ባካችሁ
ዘመዴ ነበር ያፈፈላቹ

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
75 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11 አንዳንድ ፊት አለ...!

አንዳንድ ፊት አለ፣
ጸዳል ያበጃጀው
ጮሌነት ያጀበው
ማስመሰል የካነው
በህይወት ጅራፍ ውስጥ፣ ፈገግታ ማይከዳው
ሀዘን የማይደፍረው
ግና ከናቱ ሆድ እግዜሩ ሲቀርጸው
"ክፉም ደግ ቢገጥምህ ስቀህ እለፍ" ያለው!

ይብላኝ ለኔ ቢጤ ፣ለተቋጠረ ፊት
መላ ለማይፈታው ፣የእድሜ ዘመን መክሊት

ፍቅር ሳይነጥፍበት ሰውነት ሳይከዳው
የገጹ ቋጠሮ ከይሲ ላስመሰለው

ታደሰ ደምሴ

#ሼርርር

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
73 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11 አረ ነሆለለ
ህዝቤ ተታለለ
ና በዚ ሂድ ሲባል
ደርሶ እየጋለበ
አረ ነሆለለ
ህዝቤ ተታለለ
የበቆሎ ትሉን ሲያበሉት
ዝም አለ
አረ ነሆለለ
በ ባዶ ገላነት እየተታለለ
ህዝቤ ነሆል ሆነ
አንዷ እንስት ሸርሙጣ
አንዷ ቀበጥባጣ
አረ ጠቢቧን ሴት የበላክ ጅብ ውጣ

አረ ተታለለ
ህዝቤ ነሆለለ
በውሸት ረካሾች
እየተራከሰ
ህዝቤ ነሆለለ
እየታለለ

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
64 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11 ከሰማይ ቤት ትዝብት

ሲገላለጥልኝ
የእግዜር ጣት ሲረዳኝ
የሳትኩትን ነገር
አድምቆ ሊያሳየኝ መሞቴን አረዳኝ
ከሞትኩ በኋላ
በቀብሬ ማግስት
ሁሉም እንደረሱኝ ሳስተውለው ቆሜ
እንደ ግፍ ሰቀቀኝ
እነሱን ሳባብል ያባከንኩት እድሜ
.
.
በሚኪያስ ፈይሳ

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
79 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11 ///ናፈቀን\\\
-------------------
በግዙፍ ታሪኳ
በድንግል አካሏ፤
ፍካሬው ደርሶባት
 የፊቱ ወደኋላ።
አላስነካም ብላ
ሀፍረቷን ብትሸፍን፤
ከልጆቿ ጠፍታ
አንዳች ሆነች ሚስጢር።
ተርጓሚው ሊፈታሽ
ቅኔውን ሲቆጥር፤
ጠቢቡ ቢጠበብ
አንዳች ሊያመሰጥር፤
እንደሙት ተቆጥረሽ
ጠላትሽ ሲከብር፤
ገደልኳት እያለ
ሲያቅራራ ሲፎክር፤
ሀገሬ ትንሳኤሽ
ከልጅ ልብ መቃብር።
ሶስት ቀን ረዝሞ
ሀዘን በዝቷል ደጅሽ፤
እሁድሽ ናፈቀን
ያ ውዱ ትንሳኤሽ።

abela_black

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
77 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11     //ልኩ ሚዛን\\
ጥፋት ሰው ሲያደርገው
   እጅጉን ያስቆጣል፤
   በራስ ሲደረግ ግን
   ያለ ነው ያስብላል።
 የህይወት ሚዛን ልክ
   ለፍርድ ማይቸኩል፤
   በሰው ጫማ ቆሞ
  ከራስ ሚያደርግ እኩል።
  መመርመር ማስተዋል
     በሰው ቦታ ቆሞ፤
    ችግሩን ስህተቱን
በእዝነ ህሊና በሀሳቡ ታሞ፤
  መፍትሄ ሚያገኝ ነው
     በሰው ቦታ ሆኖ።
  
abela_black

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
53 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:11 'እያልኩኝ...'


(ስወድሽ)
መውደዴን አምኜ ፡ ልነግርሽ ቃል ጠፋኝ
ጉልድፍ አንደበቴን ፡ ከመለጎም ሰፋኝ
ልቤ አቅም አግኝቶ ፡ ምነው በጀገነ
ምናለ ቢነግርሽ
ቃላትን በተፋ ፡ አፌም አፍ በሆነ
እያልኩኝ...

(ስነግርሽ)
ወደድኩሽ ያልኩሽ ቀን ፡ ላስብበት ያልሽኝ
መልስሽ የታል ስልሽ ፡ ቆይ ጠብቀኝ ያልሽኝ
...እንደምን አይተሽኝ?
ተው ታገስ በሚል ቃል ፡ ልቤን ገዝተሽው
ለትንሽ ቀን እያልሽ ፡ ዘላለም ገተርሽው
እያልኩኝ....

(ስጠብቅሽ)
ነይ በፈለግሽው ቀን ፡ እግርሽ ባደረሰሽ
ብዙ አትሳቀቂ ፡ ብቻ መልሴን ይዘሽ
በፈለግሽው ስልሽ
ብታጭኝ ከቦታው ፡ ድንገት ብታረፍጂ
በኔ አይደለም ማዘን ፡ በራስሽ ነው እንጂ
ትንሽ ቀን አልሞላም??
እያልኩኝ...

(ስተውሽ)
መቅረትሽ ነው ብየ ፡ በሬን ልዘጋ ስል
መልክት የላክሽልኝ ፡ አለሁኝ የምትል
በረፈደ ሰአት ፡ ደርሰሽ የመለስሽኝ
ነይ እቀፊኝ ስልሽ ፡ አይ አይሆንም ያልሽኝ
ቀርታለች እያልኩኝ ፡ አርፍደሽ የመጣሽ
ሲረሱሽ መታወስ ፡ ሆኖ ነው ወይ እጣሽ
እያልኩኝ....

(ሳስብሽ)
እል ነበር አውቃለሁ
የኔ ባትሆኝ እንኳ እናፍቅሻለሁ
ግን ቃሌ ከበደኝ
ያንተ አልሆንም ስትይ ብቻነት አወደኝ

ምኔ ነች ለጎኔ ፡ ምኗ ነኝ ለነፍሷ?
መስመሩን የሳትን ፡ እኔ ወይስ እሷ?

ምኑ ነው በደሏ ፡ የቱ ነው ኃጢአቴ?
አለመፈለጓ ፡ ወይስ ቃል መግባቴ?
እያልኩኝ...

የት ጋ ነኝ እያልኩኝ
ምኔ ናት እያልኩኝ
ምኗ ነኝ እያልኩኝ
እያልኩኝ...
እያልኩኝ...
እያልኩኝ...

(ስርቅሽ)
ዛሬ በአዲስ ዜማ ፡ አንጎራጉራለሁ
አሁኔ ላይ ቆሜ
ትናንት እና ነገ ፡ እመላለሳለሁ

(ያኔ የከበደኝ ፡ ቃሌን ቻልኩት አሁን
ያልኩሽንም ባልሆን ፡ ያልሽኝን በይ ልሁን)
አልኩ።


በአቤኒ የተጻፈ

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
53 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 04:53:10 ​​◦•●◉✿ አገሬ✿◉●•◦:

አገርን ለፈሪ ፤ አይሰጡም አደራ
ዳር አድርጎት ያድራል ፤ የማሀሉን ስፍራ፤

አገርን ለፈራ፣ አደራ ብሰጠው የዘላለም ቤቴን፣ባንድ አዳር ለወጠው፣

አባ ነጋ ሞቶ
አባ ጽልመት መጥቶ
አገሬ አንደ ዛጎለ፣ እያብረቀረቀች
ከባሕር ተገፍታ ፣የብስ ላይ ወደቀች።

╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
በእውቀቱ ስዩም
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
98 views01:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ