Get Mystery Box with random crypto!

አየኋት ሰገድኩኝ አየኋት ተሳልኩኝ አየኋት አየኋት ተስዬ አገባኋት አግብቼም አየኋት አይቼ አልጠገ | አፈ–ቅኔ ሄና

አየኋት ሰገድኩኝ
አየኋት ተሳልኩኝ
አየኋት አየኋት
ተስዬ አገባኋት
አግብቼም አየኋት
አይቼ አልጠገብኩም
አሁንም መልሼ
ጭኗን ተንተርሼ
በጨረፍታ አየኋት
በአትኩሮት አየኋት
የኋሊት አየኋት
የፊትም አየኋት
ፊቷ አልተቀየረም
ምንም ስህተት የለም
ከእንቁ የምታምር
እፁብ ድንቅ ተዓምር
ከዛን ተደፋሁኝ
እሷን ማየት ልተው
ፈጣሪን ልጠይቅ
አይኔን ከሷ መንቀል ለምን እንዳቃተው?
ጌታ ግን ሳቀብኝ በፀሎቴ አስካካ
ስሩ ተደፍቼም ሳያት አይቷል ለካ
*------------------*

(ሚኪያስ ፈይሣ)

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
@eyetaye12
Share