Get Mystery Box with random crypto!

Extol ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ extolimportandexport — Extol ™ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ extolimportandexport — Extol ™
የሰርጥ አድራሻ: @extolimportandexport
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 342
የሰርጥ መግለጫ

EXTOL is an Import and Export firm with a vision of becoming an iconic commerce and service industry in Africa.

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-11 13:20:31
በወጪ ንግድ የዋጋ ጥናት ቦርድ የሳምንታዊ የዋጋ ማነፃፀሪያ ` ማሳወቂያ ቅፅ
ሳምንቱ፡- ሀምሌ 04 እስከ ሀምሌ 08 ፣ 2014 ዓ.ም የሳምንቱ የሎጂስቲክስ እና የምርቶች ማነፃፀሪያ ዋጋ
98 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 17:55:22
ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

ሐምሌ 3/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የቡና ምርት 1ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን ገለጹ።

ይህ ገቢ የተገኘው ወደ ውጭ ከተላከው 300 ሺሕ ቶን የቡና ምርት መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በዚህ ዓመት የተገኘው ገቢ በዓመት በአማካይ ይገኝ ከነበረው ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ500 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱንም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ይህ ግብ እንዲሳካ ላደረጉ የቡና አምራቾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
45 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 11:44:57 Happy Eid Al-Adha
Wishing you a very happy Eid and may your life always be filled with light, love, happiness, and good health.

Eid Mubarak
160 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 21:16:18 በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ የንግድ ምክር ቤቶች ታሪክ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፈው አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቼምበር/ የ75ኛ ዓመት ክብረ በዓል መክፈቻውን የፊታችን ማክሰኞ ከጧቱ 3፡00 ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ያካሂዳል፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ  የተመሰረተበት 75ኛ ዓመት ክብረ በዓል ከሰኔ 21-23 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በድምቀት የሚከበር ሲሆን በበዐሉ ላይ የምክር ቤቱ አባላት፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ምሁራን ፣ የልማት አጋሮች፣ ሚዲያዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከ 400 በላይ እንግዶች ይታደማሉ፡፡
ምክር ቤቱ በስኬትና በውጣ ውረድ የታጀበ የ75 አመታት ታሪካዊ ጉዞውን የሚዘክርበትን፣ የወቅቱን ተጨባጭ ሁኔታውን የሚያሳይበትንና የመጻይ ዘመን ጉዞውን የሚተልምበትን ይህን ታሪካዊ በዓል በተለየና ታሪካዊ በሆነ መልኩ ለማክበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ታሪክ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንግድ ታሪክ ነው ብሎ የሚያምነው አዲስ ቼምበር ከምስረታው አንስቶ የግሉ ዘርፍና የንግድ ምክር ቤቱ በየዘመናቱ ካጋጠሟቸው ፈተናዎችና መሰናክሎች አልፈው አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላት እውቅና ከመስጠት ባለፈ፣ በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ታላላቅ የፖሊሲ ፓናሎችና ሲምፖዚየሞች፣ የምክር ቤቱን የ75 አመታት ጉዞ የሚያስቃኙ ዘጋቢ ፊልም እና ታሪካዊ መፅሃፍ የሚመረቁበት ሲሆን የፎቶ አውደ ርእይ እና የውይይት መድረኮችንም የሚያጠቃልል ይሆናል  ፡፡
በስካይ ላይትና ሂልተን ሆቴሎች ለ 3 ቀናት ከሚካሄዱት ፓናሎቹና ሲምፖዚየሞቹ መካከል በኢትየጵያ የግሉ ዘርፍ ልማትና ከባቢ የፖሊሲ ሁኔታዎች፣ ህገወጥ ንግድና የተወዳዳሪነት ፈተናዎች፣ የህጎችና ደንቦች አወጣጥ በግሉ ዘርፍ ልማት ፣ የቢዝነስ መጻኢ እድሎች እንዲሁም የንግድ ማህበራትና ተቋማት በኢትየጰያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸው ሚና  የመሳሰሉት ርእሶች ይገኙበታል፡፡ በእነዚህንም ፓናሎች  ታዋቂ ምሁራን፣የፖሊሲ አውጪዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋንያን የመነሻ ጽሁፍ ያቀርባሉ፡፡ 
በክብረ በአሉ መክፈቻ የአዲስ ቻምበርን ታሪክን የሚዘክር መጽሐፍም ታትሞ ለምረቃ እና ለንባብ የሚበቃ ይሆናል፡፡ መጽሐፉ በገለልተኛ እና  ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተጻፈ ሲሆን ንግድ ም/ቤቱ በእነዚህ ረጅም አመታት ውስጥ  በትውልድ  የቅብብሎሽ ሰንሰለት  ላይ ያለፈባቸውን መልካም  እና ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚዘክር ሲሆን  የወደፊቱን  የጉዞ  አቅጣጫ የሚጠቁም ጭምር ነው ተብሏል፡፡ የምክር ቤቱን 75 አመታት የሚያስቃኝ የቴቪ ዶክመንታሪ ፊልምም የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣዩ ሰኞ ምሽት በፋና ቴቪ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በ1993  ዓም የተዘጋጀው እና  ዘወትር  የአዲስ ቻምበር የሬድዮ ፕሮግራም መክፈቻ ሆኖ ሲያገለግል የቆየው እና በሕዝብ ጆሮ  የተለመደው ‘ ራዕያችን’ የተሰኘው ዝማሬ መሠረቱን ሳይለቅ በተሻለ የድምጽ ጥራት እና  ባማረ ሙዚቃዊ ቅንብር  እንደገና ተዘጋጅቶና ተሻሽሎ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የሚደገፈው በንግዱ ማኅበረሰብ ንቁ ተሳትፎ፣ በመንግሥት እና በንግዱ ማኅበረሰብ መካከል በሚፈጠር መተማመን ስለመሆኑ የንግድ ምክር ቤቱ  በጽኑ አምናለሁ ብሏል፡፡
የእስከ አሁኑን ጨምሮ ምክር ቤቱ በ 75 አመታት እድሜው በንግዱ ህብረተሰብ የተመረጡ 19 ፕሬዚዳንቶች መርተውታል ፡፡ ከነዚህ መካከል አቶ ገብረስላሴ ኦዳ፣ የቀድሞ የንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅና  የብሄራዊ ባንክ ገዥ የነበሩት ዶክተር ተፈራ ደግፌ፣የማስታወቂያው ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ፣አቶ ክቡር ገና፣ የህብረት ኢንሹራንስ መስራቹ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ፣አቶ አያሌው ዘገየ፣ አቶ ኤሊያስ ገነቲና የወቅቱ እና ብቸኛዋ ሴት ፕሬዚዳንት መሰንበት ሸንቁጤ ይገኙበታል።
የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት በ1939 ዓ.ም በቀዳማዊ አፄ ኀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በአዋጅ የተቋቋመ ተቋም ነው።ጀግኖች አባቶቻችን የፋሺስት ወረራን ቀልብሰው ኢትዮጵያን እንደገና በእግሯ ለማቆም በሚታትሩበት በ1930ዎቹ መጨረሻ ላይ በሀገር ፍቅር ማኅበር ታቅፈው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ነጋዴዎች ለምክር ቤቱ መቋቋም ምክንያቶች ነበሩ፡፡ የያኔው የአዲስ አበባ ነጋዴዎች፣ ምክር ቤታቸውን ያቋቋሙበት ምክንያትና ዓላማ በንግዱ ማኅበረሰብና በመንግሥት መካከል አገናኝ ድልድይ ሆነው ህጋዊ አግባቦችን ሁሉ በመጠቀም የሀገራችንን የንግድ ሥራን ለማሻሻል የሚበጁ ሀሳቦችን ለማቅረብ እንደነበር ይታወቃል::
የአሁኑ የ 75 አመት የበዓል አከባበር ያለፈው ታሪክ የሚዘከርበት ብቻም ሳይሆን፣ ወቅታዊ ዕድሎችና ፈተናዎች የሚንጸባረቁበት እና በቀጣይም ምክር ቤቱ ዘመኑን የሚመጥኑ አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን ከአባላቱ ጋር በመሆን ለሚመለከተው በማቅረብና የመፍትሔ አካል በመሆን የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ረገድ በቀጣይነት ሊያከናውናቸው ያሰባቸውን ተግባራት የሚያስተዋውቅበት እንደሚሆንም ንግድ ም/ቤቱ አስታውቋል፡፡
475 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 10:25:29 Long-awaited Africa free trade area takeoff delayed by six states
……………

Six countries drawn from three regional economic blocs are yet to ratify the African Continental Free Trade Area (AfCFTA), delaying its implementation more than a year after it was formally launched in January 2021.
The AfCFTA, a brainchild of the African Union’s integration and prosperity Agenda 2063, was supposed to create one large market for its member states. But more than a year after inception, some countries are still dragging feet in adopting its legal framework in domestic laws.
In the East African Community (EAC), South Sudan is yet to ratify the AfCFTA and in Southern African Customs Union (SACU), Botswana is yet to ratify and deposit its instrument of ratification.

Ten State Parties and non-State Parties — Comoros; Djibouti; Eritrea; Ethiopia; Mozambique; Libya; Somalia; Sudan; Tunisia; and Sahrawi Republic — are yet to submit any tariff offer.

The east african
413 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 12:10:18 አማራ ባንክ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ ይጀምራል፡፡


በምስረታ ላይ የቆየው የአማራ ባንክ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ባንኩ በዛሬዉ እለት አስታውቋል።


የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ ባንኩ ሰኔ 11 በ70 ቅርንጫፎች ስራውን በይፋ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

እስከ ሰኔ ሰላሳ ድረስም ሰራ የሚጀምሩ ቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል።


ሰኔ 11 ስራውን በይፋ የሚጀምረው ባንኩ በእለቱ ለአዲስ አበባና ዙሪያው ነዋሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ የሙሉ ቀን የጉዞ ክፍያን ባንኩ ይከፍላል ተብሏል።

በእለቱ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም የእንኳን ደስ ያላችሁ ስጦታም ይበረከትላቸዋል ተብሏል።


በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 06 ቀን 2014 ዓ.ም
407 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 10:40:59
ባለፉት 9 ወራት በማዕድን ዘርፍ ከ458 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል

ግንቦት 16/2014 (ዋልታ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በማዕድን ዘርፍ ከ458 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ዑማ ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ኢንጂነር ታከለ ዑማ ለምክር ቤቱ የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡት ወቅት እንደገለጹት በተጠቀሰው ጊዜ ከማዕድን ዘርፍ ከ458 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

ከምክር ቤት አባላት የግንባታ ዕቃዎች ዕጥረት እና የዋጋ ንረትን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ “የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምንም እንኳን ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ቢኖራቸውም ማሽኖቹን የሚያንቀሳቅሱ እጆች ልዩነት ስላላቸው የማምረት አቅማቸው ይለያያል” ብለዋል።

በዚህም የተነሳ ለዘርፉ የሚሆን ክህሎት የያዘ ሙያተኛ ለማፍራት በሆለታ የ TVET ማዕከል እንደሚገነባ ሚኒስትር አስታውቀዋል።
171 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 16:27:46 20 5 2022_Weekly Reference Price..pdf
393 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 16:27:46 Share '20 5 2022_ Weekly Reference Price.pdf'
379 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 16:27:46 The agreed-upon reference price for Logistics & Commodities for the upcoming week (May 23rd  until May 27th is attached
Trade Promotion Division 
State Minister's Office
363 viewsAysheshim Tiruneh Alemu, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ