Get Mystery Box with random crypto!

#Update በአዲስ አበበ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኢማ | Ewnet Media

#Update

በአዲስ አበበ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኢማሞች ህብረት የአቋም መግለጫ ተሰጥቷል።

መግለጫው ፤ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ አንዋር እና ኑር መስጅዶች ህዝበ-ሙስሊሙ ድምፅ በማሰማቱ ምክንያት በተከሰተዉ ችግር በሰዉ ሕይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱን አስትውሷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ብዙ ዜጎች በህግ ጥላ ስር ይገኛሉ ብሏል።

የኢማሞች ህብረት ፤ በሸገር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የመስጆዶች ፈረሳ ፍፁም ተገቢ ባለመሆኑ የሚያወግዝ መሆኑን ገልጾ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥያቄውን አቅርቧል።

በተጨማሪም የኢማሞች ህብረት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ እና ከዚህ ጋር በተያያዘ በምዕመናን ላይ የተወሰደዉን ተገቢ ያልሆነ እርምጃ በፅኑ አውግዞ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1. ከዛሬ ቀን ጀምሮ እስከ ዙልቂዕዳ ወር መጨረሻ ድረስ በሁሉም መስጅዶች ቁኑት እና ዱዓ አንዲደረግ ጥሪ አስተላልፏል።

2. በሁሉም መስጂዶች የፊታችን ጁሙዓ የኩጥባ ይዘት በሠላም፣ በአንድነት እና በሰብር ላይ እንዲያተኩር እና ህብረተሰቡ ይበልጥ በሚረዳው በአማርኛ ቋንቋ ዳዕዋ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፏል።

3. በነገዉ እለት ሐሙስ ዙልቂዕዳ 19 ፤ 1444 ዓ.ሂ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመፆም፤ በሰደቃ፣ በዱዓ እና በኢስቲግፋር ወደ አላህ በመቃረብ እና አላህ የተፈጠረውን ችግር እንዲያነሳልን እንዲለምን ጥሪ ቀርቧል።

4. በተፈጠረዉ ችግር ሕይወታቸዉ ያለፈ እና የተጎዱ ቤተሰቦችን ሙስሊሙ ማህበረስብ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባዘጋጀው የባንክ ቁጥሮች እንዲረዳ ጥሪ ቀርቧል።

5. የጁምዓ ሰላት በሠላም ተሰግዶ እንዲጠናቀቅ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ጥሪ ቀርቧል።