Get Mystery Box with random crypto!

ጽንፈኛ የፖለቲካ ኃይሎች ጫና እያሳደሩብኝ ነው ሲል ኢዜማ አስታወቀ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ | Ewnet Media

ጽንፈኛ የፖለቲካ ኃይሎች ጫና እያሳደሩብኝ ነው ሲል ኢዜማ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጽንፈኛ የፖለቲካ ኃይሎች ጫና እያሳደሩብኝ ነው ሲል ኢዜማ አስታወቀ።

ኢዜማ በፓርቲው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ፓርቲው ባለፉት 4 ዓመታት በጽንፈኛ የፖለቲካ ኃይሎችና የሀገሪቱን ሁኔታ ከግምት ማስገባት ያልቻሉ አካላት ጫና እያደረሱበት መሆኑን ገልጿል።

ከፓርቲው የለቀቁ 7 አመራሮች ባለፉት ሳምንታት ሰፊ የስም ማጥፋት እንደፈጸሙበትም ፓርቲው አስታውቋል።

ይህን በማድረግ ላይ ያሉት በፓርቲው 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ለአመራርነት ተወዳድረው የተሸነፉ አካላትን ጨምሮ በየጊዜው ከፓርቲው የሚለቁ አባላት መሆናቸውን የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ ተናግረዋል።

ፓርቲው “የሃሳብ ብዝሃነትን አይቀበልም” በሚል በለቀቁ አባላቱ የሚቀርበው ክስም ሐሰት መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።