Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር መረጃ!! መንግስት 'በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘውን የሥላሴ ገዳም ከለ | Ewnet Media

ሰበር መረጃ!!

መንግስት "በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘውን የሥላሴ ገዳም ከለላ በማድረግ መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ጽንፈኛ ባላቸው ኃይሎች ላይ በተወሰደው እርምጃ በእስክንድር ነጋና በግብረዓበሮቹ  ለውጊያ ሲውል የነበረው ምሽግ መሰበሩንና
#በ200 ታጣቂዎችም ላይ እርምጃ መወሰዱን(መገደላቸውን) የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ!!


የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ባወጣው መግለጫ <በደብረ ኤሊያስ ገዳም ሳካሂድ ቆይቻለሁ > ያለው < ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማው እስክንድር ነጋ ላይ እርምጃ ለመወሰድ መሆኑን > አረጋግጧል። የጋራ ግብረሀይሉ በመግለጫው < በጎጃም ደብረ ኤልያስ ሥላሴ ገዳም መሽገው መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ > ነበሩ ባላቸው <እስክንድር ነጋና ግብረዓበሮቹ ላይ በተወሰደው እርምጃ ክልሉን የማተራመስ ሴራቸው ከሽፏል > ብሏል።

መግለጫው አክሎም < በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘውን የሥላሴ  ገዳም ከለላ በማድረግ መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወደስዷል> ሲል ይፋ አድርጓል።በዚህም <በእስክንድር ነጋና በግብረዓበሮቹ  ለውጊያ ሲውል የነበረው ምሽግ መሰበሩንና በ200 ታጣቂዎችም ላይ እርምጃ መወሰዱን > አስታውቋል፡፡ 

<የታጣቂ ቡድኑ መሪና አስተባባሪ  የነበረው > ያላቸው <እስክንድር ነጋና ጥቂት ግብረዓበሮቹ  ከአካባቢው ለመሰወር ቢሞክሩም በዋናነት የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እግር በእግር በመከታተል የተቀናጀ ኦፕሬሽን እያካሄዱ መሆኑንም > አመልክቷል

<ግለሰቡ[እስክንድር] ይህ እንዳልተሳካለት ሲያውቅ፤ መንግሥትን በኃይል ለመጣል በማቀድ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተባለ አደረጃጀት በመፍጠር ሽመልስ ስማቸው፣ ሰውመሆን ወረታውና መንበሩ ካሴ ከተባሉ ግብረዓበሮቹ እንዲሁም ከሌሎች ጥቂት የክልሉ ጽንፈኛ ኃይሎች ጋር በመቀናጀትና በህቡዕ በመንቀሳቀስ  ታጣቂዎችን ሲመለምል፣ ሲያደራጅና ስምሪት ሲሰጥ ነበር > ሲል ወንጅሏል።

< ግንባሩን በሀገር ውስጥ ራሱ ሲመራ በውጭ ደግሞ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የተባለ ግለሰብ ያስተባብራል > ሲል የገለፀው መግለጫው፤ < ሁለቱ  በፈጠሩት ትስስር በክልሉ የትጥቅ ትግል በማድረግ ሕዝቡን ወደማያባራ ጦርነት ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል > ሲል ከስሷል።

<በተለይ የገዳሙ አስተዳዳሪ የሆኑትን አባ ኤልሳን ለዚህ ሕገወጥ ተግባር ሲጠቀሙ ነበር > ብሏል። አስተዳዳሪውም ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ውጭ በገዳሙ ውስጥ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ከመፍቀድ ባሻገር ከሌሎች መነኮሳት ጋር በማበርና የጦር መሣሪያ ጭምር በማንገብ ከጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ጋር  ተሰማርተው ነበር > ሲል ወንጅሏቸዋል።

<የጥፋት ቡድኑ አባላት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴውን እንዲያቆሙና በውይይት ወደ ሰላም እንዲመጡ ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ አካላት ተደጋጋሚ ጥረት > እንዳደረገ የሚገልፀው መግለጫው ይህ ግን ፍሬያማ ሊሆን እንዳልቻለ አስታውቋል።

<200 የጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ታጣቂዎች  መደምሰሳቸውነና የቀሩትም ከመማረካቸውና ከመሸሻቸው ውጪ፤ ቡድኑ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በሚነዛባቸው የማኅበራዊ ትስስር ገፆች በመንግሥት ጸጥታ አካላት በገዳሙና በምዕመናን ጉዳት እንዳደረሰ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው > ሲል አጣጥሏል።

መግለጫው በመቋጫው <በቀጣይም ክልሉ ከጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች ጸድቶ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲሰፍን ለሚደረገው ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ ኅብረተሰቡ የጋራ ጥረቱንና አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል >  ጥሪ አስተላልፏል፡፡