Get Mystery Box with random crypto!

#የዝንጅብል_ሻይ_የጤና_ሲሳዮች ዝንጅብል ውልደቱ ደቡብ ምስራቅ እስያ ነው፡፡ ይህ ተወዳጅ ቅመም | ጠቅላላ እውቀት

#የዝንጅብል_ሻይ_የጤና_ሲሳዮች

ዝንጅብል ውልደቱ ደቡብ ምስራቅ እስያ ነው፡፡ ይህ ተወዳጅ ቅመም በመላው ዓለም በየእለቱ ቀዳሜና ተመራጭ የምግብ ማጣፈጫ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ዝንጅብል በተፈጥሮ በታደለው ኬሚካላዊ ይዘት ለጤና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ በረከቶችን ይሰጣል፡፡ በተለይ የዝንጅብል ሻይ (ቀሽር) ወይም የዝንጅብል ውሃ ሳይንስ ያረጋገጣቸው ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጤና ጥቅሞች ይሰጣል፡፡
➊ፀረ-ብግነት( Anti-inflammatory) ፡- የዝንጅብል ሻይ አዘውትሮ መጠጣት ብግነትን ወይም መመረዝን ይከላከላል፡፡ባክቴሪያዎች፣ኬሚካሎችና ደካማ የምገባ ስርዓት ብግነት በሰውነታችን ውስጥ እንዲከሰት ምክንያት ናቸው፡፡ ብግነቱ እየጨመረ ሲሄድ ደግሞ ዘላቂ ለሆኑ በሽታዎች ይዳርገናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ለመከላከል የዝንጅብል ሻይ ያዘውትሩ ምክራችን ነው፡፡ አልርጂክ እና የጡንቻ ሕመምን በቀላሉ ያባርራሉ፡፡
➋ፀረ-ማቃጠል( Anti-oxidant) :- በሰውነታችን ውስጥ በኦክስጅን መቃጠል ምክንያት የሚከሰትን አላስፈላጊ ውጤቶች በማስወገድ የልብ በሽታን፣ከስነ አእምሮ ጋር የተያያዙ እንደ አልዛየመርና ፓርኪንሰን የመሳሰሉ በሽታዎችን ከመከላከሉም ባሻገር ካንሰርና የእርጅና ምልክቶችን ያጠፋል፡፡ የኩላሊት ድክመትንና የእጢ ዕድገትን ያዘገያል፡፡
➌ለጉንፋንና ለጉሮሮ ሕመም ወሳኝ የተፈጥሮ መድኃኒት ነው፡፡ ለሆድ ቁርጠትም ተመራጭ ነው፡፡ በተለይ በወር አበባ መምጫ ቀናትና በወር አበባ ጊዜ እህቶታችንና እናቶቻችን የዝንጅብ ሻይ ብታዘወትሩ ይመረጣል፡፡ ቁርጠት ከማስታገሱ ባሻገር የወር አበባው ያለምንም መቆራረጥ በቶሎ እንዲፈስ ይረዳዋል፡፡