Get Mystery Box with random crypto!

ለመረጃ! ሙሉ ቫንና ግማሽ ቫን እንዲሁም ፓኔል ቫን ተሸከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን በተመለከተ:- | ኤቫን መንጃ ፈቃድ ማሠልጠኛ ተቋም

ለመረጃ!
ሙሉ ቫንና ግማሽ ቫን እንዲሁም ፓኔል ቫን ተሸከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን በተመለከተ:-
* ሙሉ ቫን ሹፌሩን ሳይጨምር 11 ሰው፣
* ግማሽ ቫን ሹፌሩን ሳይጨምር 4 ሰው እና 7 ኩንታል፣
* ፓኔል ቫን ሹፌሩን ሳይጨምር 1 ሰው እና 11 ኩንታል ነው፡፡

ኪን ካፕን በተመለከተ:-
* ተሽከርካሪው የመጫን የሚወሰነው በወንበርና በወንበር መካከል ባለው ስፋት ቢያንስ 70 ሴ.ሜ መሆን ያለበት በመሆኑ ግለሰቦች ከኃላ ያለው ቦታ ለሰነዶች ማስቀመጫ ሳይሆን ወንበር ስላለው ከኃላ 3 ሰው መቀመጫ ይፈቀድልን የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ እያቀረቡ በመሆኑ ተሽከርካሪው የተሰራው ከኃላ ለሰነድ ማስቀመጫ እንጂ ከስፋቱ አንፃር መመሪያውን የሚፃረር በመሆኑ ለ1 ሰውና 10 ኩንታል ብቻ የተፈቀደ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መረጃ፡- የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን