Get Mystery Box with random crypto!

ዱባይ! ዱባይ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ዘግታ የቆየችውን ከሀገር የመውጣት ዕገዳ ከዛሬ ጀም | etv zena

ዱባይ!

ዱባይ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ዘግታ የቆየችውን ከሀገር የመውጣት ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ ሀገራት መጓዝ እንደሚችሉ በመፍቀድ አንስተዋለች።

ከዚህ በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩና ወደ ዱባይ መግባት ለሚችሉ ሰዎች ከሐምሌ ሰባት ጀምሮ ወደ ዱባይ መግባት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዱባይን ለመጎብኘት የሚመጡ የውጭ ዜጎች በቅርቡ ከኮሮና ቫይረስ ተመርምረው ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዱባይ አየር መንገድ ውስጥ እንደገና ለመመርመር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል - #ENA