Get Mystery Box with random crypto!

EBS TV

የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_newss — EBS TV E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_newss — EBS TV
የሰርጥ አድራሻ: @etv_newss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.18K
የሰርጥ መግለጫ

worldwide news🌍

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:57:59
#OromiaRegion

" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://oromia.ministry.et/#/home ላይ መመልከት ይችላሉ " - ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኢንተርኔት የሚያዩበት አድራሻ ‘https://oromia.ministry.et/#/home መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መረጃ ፦

451 ሺሕ 21 ተማሪዎች ለፈተና ተመዝግበው 98 ነጥብ 3 በመቶ ፈተናውን ወስደዋል።

የ9ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ እና ለሴቶች 47 በመቶ ነው።

በአርብቶ አደር አካባቢ የ9ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 47 % ለሴቶች 44 % ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44% እና ለሴቶች 41% ነው።

Credit : WMCC

@tikvahethiopia
124 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:57:59
#ነዳጅ

የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
101 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:57:58
#Update

የደሴ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።

ነዋሪዎች በሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎች፣ መረጃዎችና አሉባልታ አትደናገሩ ብሏል።

ማንኛውም የተለየና አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል።

ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነገር ግን በዚህም መሃል ሰርገው ሊገቡ የሚችሉ የጥፋት ኃይሎች ካሉ በመከታተል ለሚመለከተው የጸጥታ ኃይል መጠቆም እንደሚገባ አስተዳደሩ ገልጿል።

የባንክና መሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍት ሆነው እየተሰጡ መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት የተሰጠ ሲሆን አገልግሎት በሚያቋርጡና ዋጋ አላግባብ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

በከተማው የታወጀውን አሰገዳጅ ህግ ሁሉም ሊያከብረው የሚገባ ሲሆን ጥሰት የሚታይ ከሆነ አስተዳደሩ ትእግስት እንደማያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ አጥብቆ አስጠንቅቋል።

በሌላ በኩል ፤ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በየመዝናኛ ቤቶችና ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታዎች ላይ አሉባልታ ወሬ በማናፈስ ህብረተሰቡ እንዳይረጋጋ በማድረግ ኗሪው በፍርሃት ከተማውን ለቆ እንዲወጣ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንዳሉ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ይህንን በማወቅ በአሉባልታ ሳይደናገር የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።

የከተማው ጸጥታ ማዋቅር የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑንም የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።

ወልድያን በተመለከተም ዛሬም #ሰላማዊ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎች ከአሉባልታ በመራቅ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁና ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
96 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:57:58
#OFC

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በላከው መግለጫ " በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት እና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት በመባባሱ እጅግ አዝናለሁ " ብሏል።

ፓርቲድ የነዚህ ግጭቶች መባባስ እና መቀጠል ህዝቡን ዳግም ለከፋ ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ ከመሆኑ ባሻገር ለንብረትና መሰረተ ልማቶች ውድመት የተዳረጉ አካባቢዎችን ለበለጠ አለመረጋጋት ይዳርጋል ብሏል።

ኦፌኮ ጦርነቶቹ ከመቀሰቀሳቸው ቀድም ብሎ ጦርነት ለኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል እንደገለፅኩት አሁን ዳግም በአፅንዖት እገልፃለሁ ብሏል።

አሁን ያሉት ችግሮች በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት በእውነተኛ እና ሁሉን አቀፍ ድርድር ብቻ ነው ሲል እምነቱን ገልጿል።

በሁሉም ወገን ያሉ ተፋላሚ ሀይሎች ግጭቱን በማብረድ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲሹ ጠይቋል።

ዓለም አቅፊ ማህበረሰብ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ሁሉ ተጨማሪ ሞት እና የዜጎችን መከራ ለማሰቀረት በንቃት እና በተቀናጀ መልኩ ይረባረብ ሲልም ጥሪ አሰምቷል።

ኦፌኮ በኦሮሚያ እየተስፋፋ ነው ያለውን ግጭት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመፍታት ቀርቶ እውቅና ሊሰጠው አልቻለም ያለ ሲሆን ይህ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በክልሉ በተለይም በግጭትና በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲልም ገልጿል።

የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እየተባባሰ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በድርድር እንዲፈታ ሁኔታዎችንን እንዲያመቻች ጠይቋል።

ፓርቲው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ገዥው ፓርቲ፣  ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎች እና አክቲቪስቶች ግጭቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲታቀቡ እና ችግሩን ለማርገብና ለመፍታት በአንድ ድምፅ እንዲተባበሩ ተማጽኗል።

@tikvahethiopia
76 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:57:58
የጃራ ተፈናቃዮች ጉዳይ!

የጃራ ተፈናቃዮች ትናንት ወደ አፋር ጭፍራ ቢሄዱም አትገቡም ተብለው ዛሬ ወደነበሩበት መመለሳቸውን ተናግረዋል።

በጃራ በመጠለያ ጣቢያ የሴቶችና ህፃናት አስተባባሪ ወ/ሮ ዘነበወርቅ ጣውዬ ፥

" በካምፑ ውስጥ ከተለያዩ የራያ፣ ኮረም ቆቦና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያው የነበሩ ከ30 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ባገረሸው ግጭት በስጋት ሳቢያ ወደ ጭፍራ ተጉዘው አዳራቸውን በዚያው አድርገዋል።

ተፈናቃዮቹ ከማንነት ጋር በተያያዘ ከ 'ህወሓት' ጥቃት ይደርስብናል በሚልና ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የውሃና የምግብ እጥረት በመከሰቱ ጭምር የሸሹ ናቸው። "

ከተፈናቃዮች መካከል አቶ ዝናቡ መሰለ ፦

" ሁሉም ተፈናቃይ ለሶስት ቀናት በመጠለያ ጣቢየው ቢቆይም፣ የምግብና የውሀ እጥረት በመከሰቱ እንደገና ለመፈናቀል ተገደናል።

የአማራ ክልልን አቋርጠን አፋር ክልል ብንደርስም ጠብቁ ተብለን እዛው ሜዳ ላይ አድረን ወደመጣቹበት ተመለሱ ተለናል።

በዚህም ምክንያት ዛሬ እየተመለስን ቢሆንም ብዙዎች አቅመደካሞች ህፃናትና እናቶች በየበረሀው ቀርተዋል።

አካባቢው እጅግ ሙቀት በመሆኑ ህፃናትና የሚያጠቡ እናቶች ለከፍተኛ የውሀ ጥምና ርሀብ ተጋልጠዋል። "

ትናንት ከጃራ ጭፍራ ዛሬ እንደገና ከጭፍራ ጃራ ተጉዘው ወደ መጠለያ ጣቢያው ከደረሱት መካከል አንዳንዶቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችና የማብሰያ እቃዎች በመዘረፋቸው፣ የውሀና የምግብ አቅርቦት ባለመኖሩ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዓለሙ ይመር ፦

" መጠለያ ጣቢያውን ሁሉም ተፈናቃዮች አለቀቁም። የሄዱትም ቢሆኑ እተመለሱ ነው ብለዋል፡፡  የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ በተመለከተ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቦታው ይላካል " #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
75 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:57:58
#UnitedNation

የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትላንት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይን አንስተው ነበር።

ስቴፋን ዱጃሪች ምን አሉ ?

- በሰሜን ኢትዮጵያ አሁንም ግጭት መቀጠሉን እና አሁን ላይ ያለድ ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ገልፀዋል።

- የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች ማለትም በያሎ እና ጉሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለ ውጊያ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

- በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታ ጭፈራ ወረዳ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚገልፅ ሪፖርት መኖሩን አመልክተዋል።

- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከሚገኘው የጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ተጠልለው የነበሩ 30 ሺህ ሰዎችም ለሁለተኛ ጊዜ ተፈናቅለዋል።  

- ዳግም ባገረሸው ግጭት ሰዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ የሰብዓዊ መብት ፍላጎትን ይጨምራል ብለዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተይይዟል)

@tikvahethiopia
76 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:57:57
#Update

የኢፌዴሪ መንግስት ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር (አማራ ክልል) አካባቢ ወረራ ከፍቷል ሲል አሳወቀ።

ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ ያወጣው የኢፌዴሪ መንግስት ፤  " ሕወሐት በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም " ብሏል።

በዚህ ምክንያት ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ነው ብሏል።

ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ መክፈቱን የገለፀው የኢፌዴሪ መንግስት ወራራውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ ይገኛል ብሏል።

ዛሬም ድረስ ለሰላም አማራጮች የተዘረጉ እጆች አልታጠፉም ያለው የኢፌዴሪ መንግስት ይህ ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን ያድርግ ሲል አሳስቧል።

" ወገን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሓት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ ያውጣ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

(የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
84 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:57:57
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ6 ሳምንታት ውስጥ በአዲስ አበባ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚጀምር የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር አስነብቧል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀናት በፊት በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ መጀመሩ ይታወሳል። አገልግሎቱ በራሱ መሰረተ ልማት የተጀመረ መሆኑ ተጠቁሟል።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ሲካሄድ የነበረው የመሠረተ ልማት ስምምነት በቶሎ ባለማጠናቀቁ አገልገሎቱን ለማስጀመር ጊዜ መውሰዱን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትርፍ ለማግኘት ቢያንስ 5 ዓመታት ሊፈጅበት እንደሚችል አስታውቋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ፣ በሲሚንቶና በሌሎች ግብዓች ላይ ዋጋ መጨመሩ ኩባንያው በቶሎ ትርፍ ለማግኘት እንቅፋት ሊሆንበት እንደሚችል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ባልቻ ሬባ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሠጡት ቃል ፤ ኩባንያው እስከ ሚያዚያ 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን 25 በመቶ የኅብረተሰብ ክፍል የሚሸፍን አገልግሎት እንዲያቀርብ ውል ገብቷል ብለዋል።

በዚሁ በተጠቀሰው ጊዜ የሚጠበቅበትን ካላሟላ ኦዲት ተደርጎ በገባው ውል መሠረት ቅጣት ይጣልበታል እንደሚጣልበት፤ ይሁን አንጂ የቴሌኮም ኩባንያው አሁን በተሳካ ሁኔታ ሥራውን እያከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ኩባንያቸው የዋጋ ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን የቴሌኮም አገልግሎት እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-08-31

@tikvahethiopia
107 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:50:30
#ATTENTION

ኮምቦልቻ !

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት የከተማድን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል ፦

- ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

- በከተማው አሉባልታ ማናፈስ በህብረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር የሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል።

- በከተማ ደረጃ  አገልግሎት የሚሰጡ  ታክሲዎች እስከ 11 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  ተወስኗል።

- ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን  በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እረምጃ  እንዲወሰድ ታዟል።

- በምግብ ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፌዎችና ግረሶሪዎች ከ11 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት ተከልክሏል።

- DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ  ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

- የአልጋ አከራ ሆቴሎች፣ የመኖሪያ እና መደብ አከራዮችን አገልግሎት ሲሰጡ የተገልጋዩን ማንነት የሚገልፅ መረጃ በመያዝ አገልግሎት እንዲሰጡና መታወቂያ ኮፒ ማድረግ እንዳይዘነጉ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

ለመረጃ እና ጥቆማ፦ በስልክ ቁጥሮች 0335510005
0335510945
0921038804 ላይ መደወል ይቻላል።

@tikvahethiopia
125 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:50:30
#ATTENTION

ሰቆጣ !

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የፀጥታ  ሁኔታ በማስመልከት ውሳኔዎችን አሳልፏል።

- ማንኛውም እግረኛ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጣቸው ተሸከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- ከጸጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ሰዓትና ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- ማህበረሰቡን የሚያውኩ የሃሰት አሉባልታዎች / የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ተከልክሏል።

- ተፈናቃዮች ከተሰጣቸው የመጠለያ ካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ በብቅ ተከልክሏል።

- ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ሆቴል እና መስል የመንግስትና የግል ድርጅቶችን መዝጋት በጥብቅ ተከልክሏል።

- በከተማው የሚገኙ የመንግስትና የግል ታጣቂዎች መንግስት በሚያሰማራው የፀጥታ ስራ ላይ ተሳታፊ የመሆን ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

- ማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ  ተጠቃሚ ግለሰብ ሆነ ድርጅት የትኛውንም  ሚዲያ ተጠቅሞ የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት፣ በተለይ ስለጦርነቱ አሉቧልታ መዘገብ ሆነ መግለጫ መስጠት በጥብቅ ተከልክሏል።

- ማንኛውም የቤት አከራይ ወይም አልጋ ቤቶች ተከራዮቻቸውን የመለየትና የገለሰቦቹን ማንነት የሚለይ ህጋዊ መታወቂያ ስለመያዛቸው የማረጋገጥ ግደታ አለባቸው።

- ማንኛውም የከተማው ማህበረሰብ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር የመቀናጀትና የመተባበር  ግዴታ አለበት።

እንዚህ በማይከብር ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ታዟል።

@tikvahethiopia
109 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ