Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል። በ | ETV.News

#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሲሆን ፤ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የምትሰራ አንዲት ግለሰብ ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሶስት አመት ህፃናትን ህይወት አጥፍታለች።

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፦

" ቦታው ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነው፤ ወረዳ አራት አራብሳ ኮንዶሚኒየም እዛ አካባቢ ነው።

ወንጀሉ ተፈፀመው አራት ሰዓት አካባቢ ነው። ግለሰቧ እጅግ ዘግናኝ የሆነ ወንጀል ነው የፈፀመችው።

የሁለት ዓመት እና የሶስት ዓመት (ክርስቲያን መላኩ እና ወንጌላዊት መላኩ) ህፃናትን ነፍስ ነው ያጠፋችው።

ምክንያቱ ገና እየተጣራ ነው ወንጀል ፈፃሚዋ ግን በቁጥጥር ስር ውላለች። እስካሁን ባለን መረጃ ከአሰሪዎቿ ጋር በተፈጠረ ፀብ ነው የሚባለው።

የአገዳደል ሁኔታው እየተጣራ ነው። በምንድነው የገደለችው እንዴት ነው የገደለችው የሚለው ነገር ... ግማሹ አርዳነው ያላል ግማሹ አንቃ ነው ይላል እየተጣራ ነው ዞሮ ዞሮ ግን የህፃናቱ ህይወት አልፏል ይሄ ነው አሁን ላይ በተጨባጭ ሊገለፅ የሚገባው።

ወንጀሉ እጅግ ዘግናኝ ስለሆነ ፖሊስ መስራት የሚገባውን ሰርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ያቀርባል ህብረተሰቡ መረጋጋት አለበት። "

#ኢትዮኤፍኤም

@tikvahethiopia