Get Mystery Box with random crypto!

Ethio pharmaceuticals and Health

የቴሌግራም ቻናል አርማ etpdhids — Ethio pharmaceuticals and Health E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etpdhids — Ethio pharmaceuticals and Health
የሰርጥ አድራሻ: @etpdhids
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 875
የሰርጥ መግለጫ

Info
A channel created for pharmaceutical product ,pharmacy service promotion , drug and health related information delivery .
For comment @demass_bot

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 09:51:16 የጆሮ ህመም

ጆሮ ሶስት ክፍሎች ሲኖሩት ውጨኛው መሀለኛዉ እና ውስጠኛ ብለን እንከፍላለን።

የውጨኛው የጆሮ ክፍል የጆሮ ቅጠል (auricle) ና እስከ ጆሮ ታንቡር የሚደርሠውን ቱቦ (external ear canal) ያጠቃልላል።

የመሀለኛው ክፍል ድምጽ ለማስተላለፍ የሚያገለግሉ ጥቃቅን አጥንቶች፡ በሙከስ የተሸፈነ በአየር የተሞላ ቦታ እና ጆሮን ከአፍንጫ የሚያገናኝ ቱቦን ያጠቃልላል።

የውስጠኛው ክፍል ባላንስን ለመጠበቅ እና ድምጽን ለመቀበል የሚችሉ ነርቮች የሚገኙበት ነው።

የጆሮ ህመም ስንል የእነዚህ ክፍሎች በተለያዮ ችግሮች መጠቃት ነው። ከነዚህም ውስጥ ኢንፌክሽን ዋነኛው ነው። በተጨማሪም እብጠት ፡ጆሮ ውስጥ ያለ ፈሳሽ መረበሽ (በመጠን ፡በውስጡ ያለው ካልሽየም ያለ ቦታው መገኘት፡) በመድሀኒቶች ምክነያት መስማት መቀነስ፡ በከፍተኛ ድምጽ ምክነያት መቀነስ፡ ከእድሜ ጋር የ ተያያዙ የመስማት ችግሮች እና ሌሎችም ለጆሮ ህመም ምክነያቶች ናቸው።

ለዛሬ የውጨኛው የጆሮ ክፍል ኢንፌክሽንን እናያለን

1. የውጨኛው የጆሮ ክፍል ኢንፌክሽን የሚከሠትበት ዋና ዋና ምክነያት
፨በተደጋጋሚ ውሀ ወደ ጆሮ ማስገባት
፨የማሳከክ ስሜት ሲኖር በተለያዩ ነገሮች ጆሮን መጎርጎር
፨ኩክ ለማውጣት በምንሞክርበት ሠአት የቱቦውን ቆዳ መጉዳት ሲኖር የሚከሠት ነው።

ይህ የውጨኛው የጆሮ ክፍል ኢንፌክሽን ለበሽታ ተጠቂ በሆኑ ሠወች በተለይም በ ስኳር ታማሚዎች ላይ ከፍተኛ ወደ ሆነ ደረጃ የመለወጥ እድሉ የሠፍ ነው።ይህ ማለት በጆሮ አካባቢ ያሉ አጥንቶችን ብሎም ነርቭን የማጥቃት ባህሪ ያመጣል። (malignant otitis externa)

የህመሙ ምልክቶች

፨ ጆሮን የመብላት አብዝቶ የማሳከክ ስሜት
፨ መጠኑ አነስተኛ የሆኘ እዥ ወይም መግል
፨ ጆሮ ድፍን የማለት ስሜት
፨ አንዳንዴም መስማት መቀነስ ሊያስከትል ይችላል

መከላከያ መንገዶች
፨ ኡድ ስናደርግ ፡ሻወር ስንወስድ፡ ወይም በየትኛውም መንገድ ውሀን ወደ ጆሮ አለማስገባት

፨ ዋና ለሚያዘወትሩ ሠዎች በተለይም ከዚህ ቀደም የታመው የሚያውቁ ከሆነ ቅድመ መከላከያ ጠብታን መጠቀም

፨ የማሳከክ ስሜት ሲኖር ስለታማ ሹል ነገሮችን በመጠቀም ጆሮን መጎርጎር ማቆም

መፍትሔወች

፨ በጆሮ የሚደረጉ ጠብታወች ከሚዋጡ መድሀኒቶች የተሻለ መፈወስ አቅም አላቸው ነገር ግን እንደ አስፈላጊነቱ ጠብታወችን ከሚዋጡ መድሀኒቶች ጋር ሊታዘዝ ይችላል ችግሩ ከፍተኛ ከሆነም በመርፌ መድሀኒት ያስፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ የተጠራቀመ መግል ካለ ስቦ ማውጣት ያስፈልጋል።

ሰለዚህ፦ መከላከል ላይ እናተኩር።

ዶር አለማየሁ እሸት ፤ ከአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት
30 viewsRaphael Raphael, 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:17:10 "ጆሮ ደግፍ" (Mumps) ስለሚባለው በሽታ እንወያይ

1.ጆሮ ደግፍ (mumps) ምንድን ነው

-ጆሮ ደግፍ (mumps)የምንለው በሽታ በብዛት የሚያጠቃው በጆሯችን ስር የሚገኙትን ምራቅን የሚያመርቱትን የምራቅ አመነጪ ከረጢቶች (salivary glands) ሲሆን ይህም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ላይ mumps በሚባል ቫይረስ በበሽታው ከተጠቃ ሰው በሚስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከላይኛው የመተነፈሻ አካል በሚወጣ ጠብታዎች ወደ ጤነኛ ሰው መተንፈሻ አካል በሚገባበት ጊዜ እነዲሁም በንክኪ ይተላለፋል።

-እንደ የአለም የጤና ድርጅት (WHO) አገላለፅ በአብዛኛው ይህ በሽታ በብዛት በአማካይ ከ5-9 አመት የእድሜ ክልል ላይ ያሉ ልጆች ላይ ይከሰታል።ይህ በሽታ በተለይም የmumps ክትባትን ያልወሰዱ ሰዎች ላይ ይስተዋላል።

አጋላጭ ምክንያቶቹስ?

-የmumps ክትባት ያልወሰዱ፣ደካማ የበሽታ መከላከያ አቅም (immune defficiency) ያላቸው ሰዎች ተጋላጭ ናቸው።

ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?

-ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ከገባ በዃላ የበሽታውን ምልክት ምልክት እስከሚያሳይ ከ2-3 ሳምንት ጊዜ ሊቆይ ይችላል።

-ከጆሮ ዝቅ ብሎ ባለው የፊት ክፍል እብጠት መኖር ፣ ትኩሳት ፣ በምራቅ ከረጢት አካባቢ የህመም ስሜት፣በሚያኝኩበት እና በሚውጡበት ጊዜ የህመም ስሜት መኖር ፣የእራስ ምታት ፣ የጡንቻ ህመም ፣ ትኩሳት፣ የድካም ስሜት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ይስተዋላል።

የሚያመጣውስ መዘዝ?

-Mumps በሽታ በሰውነታችን አካሎች ላይ የመቆጣት እና የማበጥ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ለምሳሌ የወንድ የዘር ፍሬ መቆጣት (orchitis)፣ የሴት ዘር ማኮረቻ መቆጣት (Oophoritis)፣ በተለምዶ የማጅራት ገትር (meningitis)፣ የቆሽት መቆጣት (pancreatitis)፣ የመገጣጠሚያ መቆጣት (arthritis)፣ ለመስማት መሳን (deafness) ሊከሰት ይችላል።

እንዴት መከላከል እንችላለን?

-ወላጆች ልጅዎን የmumps ክትባት (MMR vaccine) መውሰድ በተለይ እድሜያቸው ከ 12-15 ወር ህፃናት የመጀመሪያውን ዙር ከዛም ሁለተኛውን ዙር ክትባት ደግሞ እድሚያቸው ከ4-6 አመት ክልል ሲሆኑ መውሰድ ከበሽታው ተጋላጭ እነዳይሆኑ ይረዳል።

ህክምናዎቹስ ምንድን ናቸው?

-ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ ስለሆነ በበሽታው የተጠቃውን ሰው ቢያንስ ለይቶ ማቆየት፣ ፈሳሽ ነገሮችን በብዛት መውሰድ፣ አሲዳማ ምግቦችን ለምሳሌ እንደ ብርቱካን እና ሎሚ አለመጠቀም፣ ብዙ ማኘክ የሚፈልጉ ምግቦችን አለመመገብ፣ ህመም ካለ የህመም ማስታገሻ በሀኪም ትእዛዝ መውሰድ፣ ሞቅ ባለ ወይም ቀዝቀዝ በላ ነጠር እብጠቱ ላይ መያዝ እንዲሁም በቂ እረፍት ማድረግ የህክምናው አካል ነው።

-በቫይረሱ ምክንያት ተያያዥ መዘዞች ካሉ እንደ አስፈላጊነቱ ተኝቶ መታከም ሊጠበቅ ይችላል።

-በሽታው በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ስለሆነ ፀረ ባክቴሪያ መጠቀም ምንም ጠቀሜታ የለውም።
97 viewsRaphael Raphael, edited  08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:29:17 "ህፃናት መች ነው ጥርስ ማብቀል ያለባቸው?" - ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ሐኪም

ህፃናት እስከ መች መብቀል አለበት? ካልበቀለ መች ወደ ባለሙያ መመሄድ አለባቸው? የጥርስ መብቀል ከተቅማጥ በሽታ ጋር ይገናኝ ይሆን? ስለ ህፃናት የጥርስ እድገት ትንሽ ጀባ ልበላችሁ

ብዙ እናቶች ልጆቻቸው ጥርስ መች ማብቀል እንደሚጀምሩ በግልፅ ስለማያውቁ ልጄ እስካሁን ጥርስ አላበቀለም/ አላበቀለችም ብለው ጤና ተቋም ሲመጡ ማየት የተለመደ ነገር ነው። አንዳንድ እናቶች ደግሞ እስከመች ድረስ ሊያድግ እንደሚችል አያውቁም በዚህ የተነሳ እራሳቸውን ሲያጨናንቁ እናያለን ይህን ጭንቀታቸውን ለመቅረፍ እኔም ካነበብኩት ትንሽ ጀባ አልኳችሁ።

የህፃናት የጥርስ እድገት በጨቅላዎች እና በልጆችዎ ድድ ውስጥ የጥርስ መብቀልን ያመለክታል ይህ የሚጀምረው ብዙውን ጊዜ ልጅዎ ከ6 እስከ 8 ወር ዕድሜ ሲኖረው ሲሆን፡፡ ልጅዎ የ30 ወራት ዕድሜ ላይ ሲደርስ ሁሉም 20 የህጻናት ጥርሶች ቦታቸውን ይይዛሉ ፡፡

አንዳንድ ልጆች ግን ከ8 ወር ዕድሜያቸው በሗላም ቢሆንም ምንም አይነት ጥርስ ላያሳዩ ይችላሉ ፣ ይህ ግን ብዙውን ጊዜ የተለመደ ቢሆንም ምንም ጥርስ አስከ 13 ወር ካልበቀለ ለባለሙያ ማሳየት ይገባል፡፡

ብዙውን ጊዜ ሁለቱ የታችኛው የፊት ጥርሶች (የታችኛው ኢንሲዘሮች) ቀድመው ይበቅላሉ፡፡ ቀጥለው ሁለቱ የላይኛው የፊት ጥርሶች (የላይኛው ኢንሲዘሮች) ያድጋሉ፡፡

ከዚያም ሌሎች ወተት ጥርሶች (ኢንሲዘሮች) ፣ የላይኛውና የታችኛው መንጋጋዎች ፣ የውሻ ክራንቻዎች፣ በመጨረሻም የላይኛውና የታችኛው በጥልቀት የሚገኙት መንጋጋዎች ይበቅላሉ፡፡

ልከጆች ጥርስ ማብቀል ሲጀምሩ ምን አይነት ምልክቶች ያሳያሉ ??

- መነጫነጭ ወይም ብስጩነት ማሳየት
- ጠንካራ ነገሮችን መንከስ ወይም ማኘክ
- ልጋግ ማዝረብረብ ብዙውን ጊዜ ጥርስ ማደግ ከመጀመሩ በፊት የሚከሰት ነው
- የድድ ማበጥና መጠንከር
- ምግብ እምቢ ማለት
- የእንቅልፍ ለመተኛት መቸገር

መፍትሄውስ ምን ይሆን?

በዚህ ጊዜ ማድረግ ያለብን ልጅዎ የማያኝካቸው ቀዝቃዛ ነገሮች መስጠት። ለልጅዎ ለስለስ ያሉ ምግብ ይስጦቸው ፤ በቀስታ ጥርስ የሚበቅልበት ቦታ በእጅ መንካት። በዚህ መንገድ የልጅዎን የጥርስ እድገት አብረው በመሆን የተሳካ ያድርጉላቸው።
53 viewsRaphael Raphael, 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:26:02 የጤናው ግዴ ክኒን

“ምግብህን መድኃኒት መድኃኒትህን ምግብ አድርግ” ይላል የምዕራቡ ዓለም የህክምና አባት ተብሎ የሚታወቀው ሄፖክሪተስ፡፡ የእኛም አባቶች የዋዛ አይደሉም፤ “አይገኝም እንጂ ምግብ በሰዓቱ፤ የተፈተነ ነው ምድኃኒትነቱ” ይሉሀል/ ይሉሻል፡፡

ነጭ ሽንኩርትን ፋርማሲ በጓሮ ብንላት አያንስባትም። ነጭ ሽንኩርትን የኬሚካል ኮክቴል ልንላትም እንችላለን።
የምግብ መድኃኒትነት ፍልስፍና በትክከል የሚሰራው ለነጭ ሽንኩርት ነው፡፡

ነጭ ሽንኩርትን ከቅመም ወይም እጽ(herb) ምድብ ሊሆን ይችላል፡፡ የነጭ ሽንኩረት መድኃኒትንት ከልምድ ነጥሮ የወጣና ተቀባይነት ያገኜኘ ነው፡፡ ነጭ ሽንኩርት ምግብም ነው፡፡ የምግብ ማጣፈጫም ነው።

የምግብ መድኃኒትነት ምስጢር የሚነሳው በሽታን በመዋጋት ሳይሆን ሰውነት በራሱ በሽታን እንዲዋጋ በማድረጉ መቻሉ ላይ ነው፡፡ ምግብ ቅስምን(natural immune system) ያበረታል፤ ይደግፋል፤ ያፋፋል፡፡ ምግብ መድኃኒት ሲሆን ትልቁ ጥቅሙ የጎንዮሽ ጉዳት አልባ መሆኑ ነው፡፡ በአንድ ምሳሌ ላስረዳ፤ ቪታሚን ኤ የተባለውን የቪታሚን ዓይነት ከምግብና በመድሀኒት መልክ ልናገኘው እንችላለን፡፡

"ታዲያ ልዩነቱ ምን ይሆን?" ብለን ብንጠይቅ፣ በመዲኃኒት መልክ የምንወስደው ከመጠን ያለፈ ከሆነ በመመረዝና በሕይወት ላይ አደጋ ያደርሳል፤ የግድ የባለሙያ ክትትል እና ምክር ያስፈልጋል፤ ያ ካልሆነ ያድናል ብለን የወሰድነው ያብሳል ወይም ገዳይ ሊሆን ይችላል፡፡

ወደ ምግቡ ስንመጣ ይህ ችግር የለበትም፡፡ ምግብ ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የለውም። ለምሳሌ፣ ካሮትና ቀይ ሥርን ወደ ባለሙያ መሄድ ሳያስፈልግ ሆዳችን እስከቻለው ድረስ ብንወስድ ምንም ጉዳት የለበትም፡፡ ከምግብ ጋር የገባውን ቪታሚን ኤ (ቤታ ካሮቲን፤ በሰውነት ውስጥ ወደ ቪታሚን ኤ ይቀየራል) ህዋሶች የፈለጉትን ያህል በራቸውን ከፍተው ያስገቡና ትርፉን ያስወግዱታል፡፡ ህዋሶች የሚፈልጉትን ያህል ወስደው ትርፉን ይወገድ በሚሉበት ጊዜ ትክከልኛው አመጋገብ(cell nutrition) እውን ሆነ እንላለን፡፡

እንደ ነጭ ሽንኩርት ያሉ የምግብ ምንጮችን ምግበ-መድኃኒት እላቸዋለሁ፡፡ ይህን የምለው እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ነገሩ በሁሉም የዓለም ክፍል (በተለይ በጃፓን) የታወቀ ነው፤ ሳይንሱም ይደግፈዋል፡፡

ትንሽ ሳይንሳዊ መረጃ ጣል አድረጌ ማለፍ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
ለነጭ ሽንኩርት ጠቃሚ ባህርያት ምክንያት ነው ተብሎ የሚታሰብ አንድ ኬሚካል አለ፤ ይህ ኬሚካል አሊሲን(allicine) ይባላል፡፡ አሊሲን የሚሰራው ነጭ ሽንኩረቱ በሚደቆስበት ወቅት ነው፡፡ ሲደቆስ በውስጡ ያለው አሊን(alliin) የተባለው ኬሚካል እና አሊኔስ(alliinease) የተባለው ኢንዛይም ሲቀላቀሉ አሊሲን ይፈጠራል፡፡ በዚህ ከሚካል ላይ ብዙ ምርምር ተሰርቶበታል። ነጭ ሽንኩርት ብዙ ከበሽታ የሚከላከልበት ባህርያትም በብዛት የሚመነጨው ከዚህ ኬሚካል ነው።

በምንም መልኩ ይፈጠር፣ ዋናው ነገር እንዴት እንመገበው? የሚለው ነው፡፡
ነጭ ሽንኩርትን በሚከተሉት መንገዶች መመገብ ይቻላል፡፡ ለዛሬው አራቱን እንመልከት፤
1. ጥሬውን፤ እንዲያውም በጣም ምርጡ ዘዴ በጥሬው መመገብ ነው፤
2. ከምግብ ጋር በማዘጋጀት፤
3. ከማርና ከስኳር ጋር በመቀላቀል፤
4. በዘይትና በአረቂ በመመዝመዝ

ትንሽ ፈታ ላድርገው፤

1. በማር ለመመገብ የሚደረግ ዝግጅት፤
ተልጦ የተከተፈ ነጭ ሽንኩረት ግጣም ባለው ብርጭቆ ውስጥ አድርጎ የማር ወለላ መሙላትና ሞቅ ባለ ቦታ ማስቀመጥ፡፡ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማሩ የነጭ ሽንኩረቱን ኬሚካል መዝምዞ ያወጣዋል፡፡ ይህን ምዝምዝ ነጭ ሽንኩረትና ማር ቅይት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ተጠቅሞ መጨረስ ያስግልጋል(የመድኃኒቱ “ኤክስፓየር ዴት” መሆኑ ነው)፡፡

ምራቂ ነጥብ፤ ወጣቶች ሆይ፤ ይህን ወደ ቢዝነስ መቀየር አይቻል ይሆን? ነጭ ሽንኩርትና የነጭ ሽንኩረት ውጤቶች ማቀነባበሪያ ድርጅት ያስፈልጋል። ከዚያ በፊት ግን በገፍ የሚመረትበትን ዘዴ ማበጀት የግድ ይላል።

2. ነጭ ሽንኩረት በስኳር፤
አንድ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ስንኩርት ከአንድ ማንኪያ ስኳር ጋር በመቀላቅል ማዋሀድና ወዲያው መጠቀም፡፡

3. ነጭ ሽንኩረትና የወይራ ዘይት፤
ተልጦ የተፈጭ ነጭ ሽንኩርት በትልቅ ጠርሙስ (አፈ ሰፊ) አደርጎ የወይራ ዘይት(ሌላም ንጹህ የአትክልት ዘይት ሊሆን ይችላል) መጨመር፡፡ ጠቅጥቆ ከድኖ ለተወሰነ ቀን በመወዝወዝ ነጭ ሽንኩርቱ እንዲመዘመዝ ማደርግ፡፡ ይህንም አስከ ሦስት ወር ጊዜ መጠቀም ይቻላል፡፡

4. የነጭ ሽንኩርት አረቂ፤
አረቂ ምንም ጥቅም የሌለው መጠጥት ነው፡፡ ከእነ አካቴው ቢቀር ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን ከተጠጣ አይቀር በነጭ ሽንኩርት ቢጠጣ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
200 ግራም የሚሆን የተፈጭ ነጭ ሽንኩረት አንድ ሊትር በሚሆን አረቂ ውስጥ ለ14 ቀን ያህል በቀን በርከት ላለ ጊዜ እየወዘወዙ ምዝመዛ እንዲካሄድ ማድረግ፡፡ ይህ ምዝምዝ ለደም ግፊት ጥሩ ነው ይባላል፤ለዚህም በቀን እስከ 10 ሲሲ መውሰድ ይፈቀዳል፡፡ ደም ግፊትን እና ተከታዩን ስትሮክን( ለአንጎል በሁለት ምክንያቶች ደም አለመድረስ የሚከሰት አደገኛ በሽታ ነው) መከላከል ከተቻለ የጣልሁትን እቀባ አንስቻለሁ፡፡

የግብርና ሰዎች ሆይ፣ ነጭ ሽንኩርት በቤታችን(በእቃ ላይ) እንዴት ማምረት አንደምንችል ብትጽፉልን፤ የነምጭ ሽንኩርት ያህል ክብር እንሰጣችኋለን።
ጤናው ግዴ ከሆንህ የነጭ ሽንኩርትን ሌሎች በረከቶች ቆፍረህ ድረስበት።

ጤናችን በእጃችን ከምግባችን!
Via:- Yihunie Ayele
45 viewsRaphael Raphael, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:17:44 ፎሮፎር | Seborrheic dermatitis

ፎሮፎር ምንድነው?

ፎሮፎር እየተመላለሰ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፍ የቆዳ ህመም አይነት ነው። ፎሮፎር በባህሪው ጠንካራ ያልሆነ ብዙም ምልክት የሌለው እና ትንንሽ ብናኞች ያሉት ሊሆን ይችላል፤ይህ የተለመደው አይነት ፎሮፎር ሲሆን ዳንድረፍ (dandruff) በመባል ይታወቃል።

በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የሚባለው የፎረፎር አይነት አብዛኛውን የራስ ቆዳችንን እንዲሁም ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን ላይ ጭምር ሊከሰት ይችላል፤ ቅርፊቶቹም ወፍራም እና ከራስ ቆዳችን ጋር የተጣበቁ ሊሆኑ ይችላሉ

ፎሮፎር ምን አይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል?

- ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ አመት ባሉ ህጻናት እና ከጉርምስና እድሜ በላይ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ይከሰታል
- አብዛኞቹ ፎሮፎር የሚኖርባቸው ግለሰቦች ሌላ ተጓዳኝ ህመም አይኖራቸውም አንዳንድ ጊዜ ግን ከHIV ፣ Parkinson ፣ የሚጥል ህመም (Epilepsy) ፣ ጭንቀት ገር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል

ፎሮፎር መንስኤው ምንድነው?

-የፎሮፎር መንስኤ በትክክል ይሄ ነው ተብሎ መናገር ባይቻልም ከቆዳችን ጋር ተስማምተው በሚኖሩ (normal flora) የፈንገስ አይነት (Malassezia) ምክንያት ይከሰታል ተብሎ ይታሰባል

-ፎሮፎር ወዝ አመንጪ እጢዎች (Sebaceous glands) ተከማችተው በሚገኙበት የአካል ክፍሎቻችን (የራስ ቆዳ ፣ ፊት፣ ደረት አካባቢ፣ የላይኛው የጀርባችን ክፍል ፣ የውጭኛው የጆሮ ክፍል ፣ ብብት ፣ ጡት ስር ፣ በላይኛው የጭን ክፍል እና ብልት መሀከል በሚገኘው ቦታ) ላይ ይከሰታል

ፎሮፎር እንዴት ይታከማል ?

- መድሀኒትነት ያላቸው መታጠቢያ ሻምፖዎችን (ketoconazole 2%, Selenium sulfied, Ciclopirox , Zinc pyrithione) በመጠቀም ፎሮፎርን መቆጣጠር ይቻላል።
- ሻምፖውን ተቀብተን ከ5-10 ደቂቃ አቆይተን መታጠብ ይህንንም በሳምንት ከ 2-3 ጊዜ መደጋገም ያስፈልጋል
- ከዚህ በተጨማሪ የማሳከክ ስሜት ካለው፣ጠንካራ የሚባለው የፎሮፎር አይነት ከሆነ፣ከራስ ቆዳችን ውጪ ከተከሰተ፣ተጓዳኝ ህመሞች ካሉ እንዲሁም ህጻናት ላይ ከተከሰተ የቆዳ ሐኪም በሚያዘው መሰረት ተጨማሪ መድሀኒቶች ያስፈልጋሉ።

ፎሮፎር ለምን ይመላለሳል?

መንስኤው በትክክል ስለማይታወቅ እና ምክንያት ነው ተብሎ የሚታሰበው የፈንገስ አይነት ከቆዳችን ጋር ተስማምቶ የሚኖር በመሆኑ ፎሮፎርን በህክምና ማዳን አይቻልም(not curable) ለዚህም ነው የሚመላለሰው ፤ ነገር ግን ምልክቶቹን መቆጣጠር እና የሚመላለስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል

ፎሮፎር እንዳይመላለስብን ምን እናድርግ?

ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ምልክቶቹ እስኪጠፉ በሻምፖ መታጠብ ያስፈልጋል(የቆዳ ሐኪሙ ተጨማሪ መድሀኒቶችን ሊያዝ ይችላል)፤ ምልክቶቹ ከጠፉ በኋላ ሻምፖውን በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ መጠቀም ፎሮፎር እንዳይመላለስ ይረዳል

ፎሮፎር ፀጉር እንዲነቃቀል ያደርጋል?

በፎሮፎር ምክንያት የፀጉር መነቃቀል የተለመደ አይደለም ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የማሳከክ ስሜት ካለ ጊዜያዊ የሆነና ተመልሶ የሚተካ የፀጉር መነቃቀል ሊያስከትል ይችላል

በመጨረሻም የቆዳ ሐኪም ሳያማክሩ መድሀኒቶችን ባለመጠቀም ቆዳዎን ከተጨማሪ ጉዳት ይጠብቁ!!

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
102 viewsRaphael Raphael, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:27:01 "የህጻናት አስም" - በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ : የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም

- አስም ምንድን ነው?
አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ የትንፋሽ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገት ለተወሰነ ጊዜ መጥበብ ነው። ይህ የአየር ቧንቧ ጥበት መድሀኒት ሲዎስዱ ወደ ነበረበት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ነው።

- ምክንያተ መንስኤ
ዋና ምክንያቱ ተፈጥሯዊ ፣ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ በሆኑ ምክንያቶች ይነሳል። የሚፈጠረው መስተጋብር አየር ባንቧን ለዘለቀ ቁስለት/ብግነት በማጋለጥ አለርጅ ቀስቃሽ ሽታዎች ሲኖሩ የአየር ቧንቧ ከልክ ያለፈ ተለዋጭ ጥበት እና የቆሸሸ አየር ከሳንባ በሚፈለገው ልክ አለመውጣት ሳል እና የመታፈን ምክንያትን ያመጣል። ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ ምክንያቶችን መቀነስ ይቻላል።

- የአስም አይነቶች
1. በተደጋጋሚ የሚነሳ አስም/recurrent asthma/seasonal
ይህ ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚያስነሱት አስም ነው። ቀስቃሽ ምክንያቶችን በመቀነስ ድግግሞሹን መቀነስ እና ደረጃውንም መቆጣጠር ይቻላል።
2. ረጅም ጊዜ የቆየ አስም /chronic asthma
ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስም

- አለርጅ/አስም ቀስቃሾች ምንድን ናቸው?
1. የሲጋራ ፣ የከሰል እና የማገዶ ጭስ
2. የአበባ፣ቆሻሻ፣ የፅዳት መጠበቂያ/ዴቶል/ ፣ የሽቶ እና ላበት ማጥፊያዎች ሽታ
3. ላባ እና ጸጉር ያላቸው የቤት እንስሳት
4. የከብቶች ሽንት እና አዛባ
5. በረሮ የሚረጨው ኬሚካል
6. እርጥበት እና ቅዝቃዜ ያለው ስፍራ
7. የጉንፋን ቫይረስ
8. የኬሚካል ሽታ
9. ጭንቀት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
10. ሻጋታ
11. የጨጓራ አሲድ ቅርሻ/Gastro esophageal reflux disease
12. የአፍንጫ አለርጅ እና ሳይነስ ህመም

- ለአስም አጋላጭ ሁኔታዎች
1. የቆዳ አለርጅ/የቆዳ አስም
2. የአፍንጫ እና አይን አለርጅ
3. የምግብ አለርጅ
4. አስም ያለበት እናት ፣ አባት ፣ እህት ወይም ወንድም
5. ከጉንፋን ጋር የማይያየያዝ ሳል

- የህመም ምልክቶች
1. በቅዝቃዜ ወቅት እና ማታ ማታ የሚባባስ ደረቅ ሳል
2. የደረት መጨነቅ/የመታፈን ስሜት
3. የትንፋሽ መፍጠን
4. የድካም ስሜት
5. የሰውነት መዛል እና ላበት
6. ሙዚቃዊ ትንፋሽ
7. ራስ ምታት፣ የትኩረት መቀነስ፣ እና አቅልን መሳት

- አስም አመላካች ነገሮች ምን ናቸዉ
1. በጥርጣሬ የአስም መድኃኒት ሲሰጥ በቶሎ የሚሻል ከሆነ
2. ወላጅ አስም ወይም አለርጅ ካለበት
3.ነባር የትንፋሽ አለርጅ ካለ
4. ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አለርጅ:

- ህጻናት ላይ አስም ይምንለው በአመት ውስጥ ሶስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የሆነ ሀኪም ያረጋገጠው የመተንፈሻ አለርጅ ካለ ነው።

- አስምን በምን እናረገግጣለን
1. የሳንባ ምርመራ:
በጤንነታቸው ወቅት ያላቸው የሳንባ አየር የማስገባት እና የማስወጣት የመጨረሻ አቅም ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል በህመሙ ምክንያት ቀነሰ የሚለውን በመለካት።
2. የአየር ቧንቧ ለትንፋሽ ቧንቧ አስፊ ህይዎት አድን መድሀኒት ያለውን ፈጣን ምላሽ በማየት።
3. በአለርጅ አምጭ/ቀስቃሽ መድሃኒት አስም የመከሰት እድሉን መሞከር(ይህ ምርመራ ብዙ አይመከርም)
4. በእስፓርታዊ እንቅስቃሴ ያለውን የተቃጠለ አየር የማስውጣት አቅም በመለካት።

- የአስም ህክምና
1. የአየር ቧንቧን ጥበት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች
2. የአየር ቧንቧ ቁስለትን/ብግነትን የሚቀንስ መድሃኒት
3. አለርጅን የሚቀንስ መድሃኒት
4. አስም ቀስቃሽ የሆነውን ህመም ማከም
5. ቤትን ከአስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ነጻ በማድረግ አስም እንዳይነሳ መከላከል
6. በቅዝቃዜ እና ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች የአስም ቅድመ መከላከል መድሃኒት መስጠት

- እንደ መውጫ
የህጻናት የመተንፍሻ ቱቦ በተፈጥሮ ጠባብ በመሆኑ ምክንያት አስም ጋር የሚመሳሰሉ ብዙ ህመሞች ስላሉ አስም አለ የምንለው በታፈኑ ወቅት በአስም መድሀኒት ያላቸው ለውጥ አመርቂ ከሆነ እና ለአስም ተጋላጭነት ካላቸው ነው።

እድሜያቸው ከ4 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የሳንባን በአግባቡ መስራት ወይም አለመስራት ለማወቅ ለምርመራ እድሜያቸው ስለማይፈቅድ በብዛት በክትትል ብቻ ነው መለየት የሚቻለው። አካባቢያዊ አስም ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስተካከል አስምን መከላከል ዉጤታማ ነው።
145 viewsRaphael Raphael, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:18:39 86 መድኃኒት ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል

ለሽያጭ እንዳይቀርቡ የተከለከሉና ምንጫቸው የማይታወቁ መድኃኒቶችን የሸጡ 86 መድኃኒት ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ኃይለኢየሱስ አድነው እንዳሉት፣ ከሐምሌ 1/2013 እስከ ሰኔ 30/2014 ባሉት ጊዜያት ባለሥልጣኑ ባደረጋቸው ድንገተኛ ፍተሻዎች ለሽያጭ መቅረብ የሌለባቸውን ያቀረቡ፣ ምንጫቸው የማይታወቁ መድኃኒቶችን በኮንትሮባንድ አስገብተው የተገኙ፣ ካለደረሰኝ መድኃኒቶችን የሸጡ የግል መድኃኒት ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል።
ምንጭ:—አዲስ ማለዳ
195 viewsRaphael Raphael, 12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:09:15 ቋቁቻ (Pityriasis versicolor) ምንድነው?

ቋቁቻ የተለመደና በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ የቆዳ ህመም ነው

ምልክቶቹ
ቋቁቻ በአብዛኛው ጀርባ ፣አንገት፣ደረትና የላይኛው የእጃችን ክፍል አካባቢ ይወጣል

ጠቆር ያሉ (hyperpigmented) ፣ ነጣ ያሉ (hypopigmented) አንዳንዴም ቀላ ያሉ ክብ ወይም እንቁላል ቅርጽ(oval) ሽፍታዎች ሲኖሩት እነዚህ ሽፍታዎች ላይም ትንንሽ ቅርፊቶች ይታያሉ

ሽፍታዎቹን በጣታችን ስንለጥጠው ወይም ፋቅ ፋቅ ስናረገው ቅርፊቶቹ በደንብ ይጎላሉ

የተለመደ ባይሆንም አንዳንዴ የማሳከክ ስሜት ሊኖር ይችላል

ምን አይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል
በአብዛኛው በወጣትነት እና በጎልማሳነት የእድሜ ክልል ውስጥ ይከሰታል

ለቋቁቻ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች
- በተፈጥሮ ተጋላጭነት (genetic predisposition) ይህም በቤተሰብ አባላት ውስጥ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል
- ሞቃታማ አካባቢ መኖር
- የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
- እርግዝና
- ቆዳችን ወዛም ከሆነ
- Oily የሆኑ ቅባቶችን መጠቀም
- ከመጠን ያለፈ ላብ

ቋቁቻ እንዴት ይታከማል?
ሽፍታው በቆዳ ሐኪም ታይቶ ከተረጋገጠ በኋላ ሐኪሙ በሚያዘው መሰረት በሚቀባ፣ በሻምፖ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ህክምናው ይሰጣል

ከህክምናው በኋላ ሽፍታው ላይ የነበሩት ቅርፊቶች ይጠፋሉ ይህም የህመሙን መዳን ያመለክታል

ነገር ግን ሽፍታው ወጥቶበት የነበረው ቦታ ወደ መደበኛው የቆዳችን ቀለም ለመመለስ ሳምንታትን/ወራትን ሊወስድ ይችላል

ቋቁቻ ከሰው ወደሰው ይተላለፋል?
ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም

ለቋቁቻ መንስኤ የሆኑት የፈንገስ አይነቶች(በጥቅሉ Malassezia ተብለው ይጠራሉ) ከቆዳችን ጋር ተስማምተው የሚኖሩ (normal flora) ሲሆኑ ለህመሙ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወደ በሽታ አምጪነት የሚቀየሩ ናቸው፤ለዚህም ነው ህመሙ ደጋግሞ የሚከሰትብን

እንዴት እንከላከለው?

ቋቁቻ ደጋግሞ የሚከሰትብን ከሆነ እና በተለይም በሞቃታማ አካባቢ የምንኖር ከሆነ ከቆዳ ሐኪም ጋር በመመካከር ህክምናውን በሳምንት ወይም በሁለት ሳምንት ወይም በወር አንድ ጊዜ ለተወሰኑ ወራቶች በመውሰድ ቋቁቻ የሚመላላስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል

በተጨማሪም፡-

Oily የሆኑ ቅባቶችን አለመጠቀም

ከጥጥ የተሰሩ ልብሶችን መልበስ(በተለይ ከውስጥ የምንለብሳቸው)

ሰውነታችን ላይ የሚጣበቁ ልብሶችን አለማዘውተር

በመጨረሻም
ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
142 viewsRaphael Raphael, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:48:04 KITCHEN TIPS

1. Never store Onions and Potatoes together because both produce a gas that causes either of them to spoil quickly.

2. Put two or three orange leaves in your hot palm oil on the fire. Let the leaves turn black before removing it. By then your palm oil becomes pure groundnut oil also giving your food a nice taste.

3. To avoid feeling a peppering hotness on your hands after cutting pepper with bare hand scrub your hand with salt and red oil then wash it.

4. If you happen to over salt a pot of soup, just drop in a peeled potato. The potato will absorb the excess salt.

5. If your Soup or Stew goes sour while warming it, add little piece of Charcoal and remove after warming, the taste will come back.

6. Never put citrus fruits (oranges, lemon, lime, etc) or tomatoes in the fridge. The low temperature degrades the aroma and flavor of these fruits.

7. When storing empty airtight containers, throw in a pinch of salt to keep them from getting stinky.

8. If your salt is becoming lumpy, put a few grains of rice in with it to absorb excess moisture.

9. To reuse cooking oil without tasting whatever was cooked in the oil previously, cook a 1/4" piece of ginger in the oil. It will remove any remaining flavors and odors.
79 viewsDemiss Mohammed, 12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:46:35 FACTS ABOUT CUCUMBERS

1. Cucumbers contain most of the vitamins you need every day, just one cucumber contains Vitamin B1, Vitamin B2, Vitamin B3, Vitamin B5, Vitamin B6, Folic Acid, Vitamin C, Calcium, Iron, Magnesium, Phosphorus, Potassium and Zinc.

2. Feeling tired in the afternoon, put down the caffeinated soda and pick up a cucumber. Cucumbers are a good source of B vitamins and Carbohydrates that can provide that quick pick-me-up that can last for hours.

3. Tired of your bathroom mirror fogging up after a shower? Try rubbing a cucumber slice along the mirror, it will eliminate the fog and provide a soothing, spa-like fragrance.

4. Are grubs and slugs ruining your planting beds? Place a few slices in a small pie tin and your garden will be free of pests all season long. The chemicals in the cucumber react with the aluminum to give off a scent undetectable to humans but drive garden pests crazy and make them flee the area.

5. Looking for a fast and easy way to remove cellulite before going out or to the pool? Try rubbing a slice or two of cucumbers along your problem area for a few minutes, the phytochemicals in the cucumber cause the collagen in your skin to tighten, firming up the outer layer and reducing the visibility of cellulite. Works great on wrinkles too!!!

6. Want to avoid a hangover or terrible headache? Eat a few cucumber slices before going to bed and wake up refreshed and headache free. Cucumbers contain enough sugar, B vitamins and electrolytes to replenish essential nutrients the body lost, keeping everything in equilibrium, avoiding both a hangover and headache!!

7. Looking to fight off that afternoon or evening snacking binge? Cucumbers have been used for centuries and often used by European trappers, traders and explores for quick meals to thwart off starvation.

8. Have an important meeting or job interview and you realize that you don't have enough time to polish your shoes? Rub a freshly cut cucumber over the shoe, its chemicals will provide a quick and durable shine that not only looks great but also repels water.

9. Out of WD 40 and need to fix a squeaky hinge? Take a cucumber slice and rub it along the problematic hinge, and voila, the squeak is gone!

10. Stressed out and don't have time for massage, facial or visit to the spa? Cut up an entire cucumber and place it in a boiling pot of water, the chemicals and nutrients from the cucumber will react with the boiling water and be released in the steam, creating a soothing, relaxing aroma that has been shown the reduce stress in new mothers and college students during final exams.

11. Just finish a business lunch and realize you don't have gum or mints? Take a slice of cucumber and press it to the roof of your mouth with your tongue for 30 seconds to eliminate bad breath, the phytochemicals will kill the bacteria in your mouth responsible for causing bad breath.

12. Looking for a 'green' way to clean your taps, sinks or stainless steel? Take a slice of cucumber and rub it on the surface you want to clean, not only will it remove years of tarnish and bring back the

shine, but is won't leave streaks and won't harm you fingers or fingernails while you clean.

13. Using a pen and made a mistake? Take the outside of the cucumber and slowly use it to erase the pen writing, also works great on crayons and markers that the kids have used to decorate the walls!!
93 viewsRaphael Raphael, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ