Get Mystery Box with random crypto!

የራያ ቆቦ እና የቆቦ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች የትግል ውሳኔያቸውን አሳወቁ። የራያ ቆቦና እና የ | Mereja Daily

የራያ ቆቦ እና የቆቦ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች የትግል ውሳኔያቸውን አሳወቁ።

የራያ ቆቦና እና የቆቦ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ዛሬ በወልድያ ከተማ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱም የህዋሓት ወራሪ ቡድን በሕዝባዊ ማዕበል ነው የመጣው እኛም በሕዝባዊ ማዕበል እንታገላለን። ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ከጥምር ጦሩ ጎን ሁነን እንዘምታለን በማለት በትግል የሚሳተፉበትን መንገድ ከሚመለከተው አካል ጋር በመምከር ወደ ትግል አደረጃጀት ገብተዋል።

በሕዝባዊ ማዕበል ከመዝመት አማራጭ የለንም ያሉት ወጣቶቹ ሆኖም ለሀገራችን ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችንና ለጥምር ጦራችን አቅም እንጅ እንቅፋት በማንሆንበት ስልት መቀየስ ካለበት በፍጥነት ይነገረን ብለዋል።

ውይይቱን ከመሩት መካከል የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ዳዊት መለሰ ያለመከራ ጸጋ አይገኝም ሁላችንም ወደ ትግል እንግባ ሲሉ መክረዋል።
ከውይይቱ በኋላ ቀጥታ ወደ ትግል አደረጃጀት ዝግጅት ተጀምሯል!!!
ተጨማሪ መረጃዎች አሉ ጠብቁኝ።
====================
ፈጣን መረጃ ለማግኘት
@EtMerejaDaily
@EtMerejaDaily
በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ