Get Mystery Box with random crypto!

የጉጂ አባ ገዳ መኖሪያ ቤታቸው ላይ 'ኦነግ ሸኔ' ጥቃት መፈጸሙን ተናገሩ! የኦሮሞ አባ ገዳዎች | Ethio-zena

የጉጂ አባ ገዳ መኖሪያ ቤታቸው ላይ 'ኦነግ ሸኔ' ጥቃት መፈጸሙን ተናገሩ!

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ እና የጉጂ አባ ገዳ የሆኑት ጂሎ ማንዶ ታጣቂዎች በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።አባ ገዳ ጂሎ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ዕለት መጋቢት 14/2014 ዓ.ም. ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቤታቸው ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራውን እና መንግሥት ሸኔ የሚለውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ግን ታጣቂዎቻቸው 'የተባለውን ጥቃት አልፈጸሙም' ሲሉ አስተባብለዋል።አባ ገዳው ጥቃት በተፈጸመበት ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ባለመኖራቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውንና በንብረት ላይ ከደረሰው ውጪ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል።

"በቁጥር ስንት ሆነው እንደመጡ ባላውቅም በአራት ሞተር ሳይክሎች መጥተው ቤቱ ላይ ተኩስ ከፈቱ። በርካታ ጥይት ተኩሰው ቤት ሰባብረው፣ ቤት ውስጥ የነበረ አንድ ኩንታል ቡና በትነው ሄዱ እንጂ ሰው እና ከብት ምንም አልሆነም" በማለት የነበረውን ሁኔታ አባ ገዳ ጂሎ ያስረዳሉ።አባ ገዳው ታጣዊዎች ትጥቅ ፈትተው የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ ማስተላለፋቸው የጥቃቱ ዒላማ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ያምናሉ።"እነርሱ መጀመሪያም ቂም ይዘውብኝ ነበር። እየደወሉ፤ 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር በሰላም ግቡ እያልክ የምትቀሰቅሰው አንተ ነህ' ሲሉኝ ቆይተዋል" በማለት አባ ገዳው ይናገራሉ።

"እየደወሉ '600 የሚሆን ሠራዊት አስገብተህ (ትጥቅ አስፈትተህ) መሳሪያቸውን ወርሰሃል፤ ያን መሳሪያ እስክታመጣ በሕይወትህ ፍረድ' ይሉኛል" ሲሉ ጂሎ ማንዶ ከታጣቂዎቹ ይደርስባቸው ስለነበረው ዛቻ ያስረዳሉ።እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ቃል አቀባይ የሆነው ኦዳ ተርቢ፤ የኦሮሞ ነጻነት ጦር አባ ገዳዎችን እና የገዳ ሥርዓትን እንደሚያከብር ገልጸው፤ "በከረዩ አባ ገዳዎች ላይ የተፈጸመውን እና የመንግሥት (የዐቢይ) ጦር ለሥርዓቱ ያለውን ንቀት ከግምት በማስገባት ይህ የተፈጸመው በእነርሱ (በመንግሥት ጦር) ሊሆን ይችላል" ብለዋል።ከዚህ ቀደም የጉጂ እና የቦረና አባ ገዳዎች 'ኦነግ ሸኔ' የኦሮሞ ጠላት ነው በማለት ማወጃቸው ይታወሳል።ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲፈቱም ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via BBC
@etioz
@etioz