Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እሁድ ነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ምር | የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እሁድ ነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ምርጫ ክልል፤ ከየምርጫ ክልሉ የተወከሉ አምስት የስራ አስፈጻሚ አባላት በተገኙበት በተመረጡ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት አከናውኗል፡፡

በውይይት መድረኩ፤ የኢዜማ ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ትይዩ ካቢኔ እና የብሔራዊ ምክክር ኮሚቴ የ100 ቀን ዕቅድ እና በጀትን በተመለከተ የተዘጋጀበትን መሰረታዊ እሳቤዎች አብራርተዋል፡፡

ኢዜማ ከመንግስት ጋር ለመስራት በጉባዔ ሲወስን በቀጣይ አትኩሮት ሰጥቼ እሰራባቸዋለሁ ያለውን ሰባት ነጥቦች በተመለከተ የትይዩ ካቢኔ እና የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ እያንዳንዱ ነጥብ ስላለበት ሂደት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና ፖሊሲ ጥናት እና ምርምር መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ዳዊት በለው የመጪውን ሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ግቦችና የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ "ዕቅዱ ሀገራዊ እና ድርጅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት የተዘጋጀ ነው" ብለዋል።

በመጨረሻም የኢዜማ ምክትል መሪ አርክቴክት ዩሐንስ መኮንን በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ የአስተዳደር ወሰን ጉዳይ የተወሰነው ውሳኔ ጋር ተያይዞ የኢዜማን አቋም በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የሀገር ፓለቲካ ስሪቱ መሰረት ዜግነት ላይ እንዲሆን ሁሉም አባል ከልቡ አምኖ ሊሰራ እንደሚገባ ያስገነዘቡ ሲሆን የፓርቲው አባላት ሁሉ የዜግነት ፖለቲካ ምንነት ላይ አንድ አይነት አረዳድ መያዝ ግዴታ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ሁሉም አባል የጉባኤውን ውሳኔ አክብሮ መስራት እንደሚጠበቅበት እና የፓርቲውን ስነምግባር ደንብ በአግባቡ ተረድቶ እና አክብሮ በንቃት መሣተፍ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄዎች አቅርበው ምላሾች የተሰጡ ሲሆን፤ መሰል ውይይቶች በፓርቲው የተለያዩ መዋቅሮች እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ