Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethzema — የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethzema — የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
የሰርጥ አድራሻ: @ethzema
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.79K
የሰርጥ መግለጫ

ኢዜማ ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎች መብት የተከበረባት፣ ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ሰላማዊ እና የበለፀገች ሀገር እንድትሆን የሚሠራ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነው።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 07:02:59
744 views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:02:47 የኢዜማ አመራሮች የሚድያ ቆይታ ከነሐሴ 6 - ነሐሴ 22/ 2014 ዓ.ም

የኢዜማ ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በአዲስ አበባ እና ኦሮምያ መንግስት ውሳኔ አሳልፌበታለሁ ስላለው የወሰን ማካለል ከ ኢሳት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ።





የኢዜማ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አንድነት ሽፈራው በአዲስ አበባ እና በኦሮምያ ክልል መንግስት ውሳኔ አሳልፌበታለሁ ስላለው የማካለል ጉዳይ ከ Ethio Fm 107.8 የኛ ጉዳይ ፕሮግራም ላይ ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ።

https://drive.google.com/file/d/1xfYIUSMplvBNuXV9Y9p0LQ5BZPGAMzP7/view?usp=sharing

ጦርነትን እያወገዝን ሰላምን ብናስቀድምም የሀገር ህልውናና ቀጣይነት ግን በፍፁም ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አንፈቅድም! ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለን!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ





የኢዜማ ዋና ፀሐፊ አበበ አካሉ EBC 97.1 ኤፍኤም አዲስ ራዲዮ፤ አዲስ ፎረም የውይይት ፕሮግራም ላይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተው ጦርነት ዙርያ ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ።

https://drive.google.com/file/d/1GFM4WgZiD0i_5qwVJG-O3fv6VaDmJrwT/view?usp=sharing

የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አንድነት ሽፈራው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተው ጦርነት ዙርያ ከ አዲስ ሚድያ ኔትወርክ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ከ ይመልከቱ።

https://fb.watch/feGqNTeufX/

የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምርያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተው ጦርነት ዙርያ ከ VOA አማርኛ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ከ18:30 ጀምሮ ይከታተሉ።

https://amharic.voanews.com/a/6700003.html

የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የገንዘብ ሚኒስቴር ትይዩ ካቢኔ ሀላፊ ግርማ ሰይፉ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተው ጦርነት ዙርያ ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ከ2:49 ጀምሮ ይመልከቱ።





የኢዜማ ወጣቶች መምርያ ሐላፊ የሆኑት ገነት አራጌ የኢትዮጵያ ወጣቶች ከትናንት እስከ ዛሬ በሚል ርዕስ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ።

https://www.ethiopianreporter.com/109835/

ኢዜማ ነሐሴ 22/ 2014 ዓ.ም (ኢዜማ) "በአዲስ ዓመት ለዜጎች ገፀ በረከት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ ግብር በ አዲስ ሚድያ ኔትወርክ የቀረበውን ዘገባ ይመልከቱ።





ኢዜማ ነሐሴ 22/ 2014 ዓ.ም (ኢዜማ) "በአዲስ ዓመት ለዜጎች ገፀ በረከት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ ግብር በEBC የቀረበውን ዘገባ ይመልከቱ።

https://drive.google.com/drive/folders/15jHwCQNIoJtc1Vjey2U5_xGxKHFxCk9C?usp=sharing

ኢዜማ ነሐሴ 22/ 2014 ዓ.ም  (ኢዜማ) "በአዲስ ዓመት ለዜጎች ገፀ በረከት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በተከሰተው ጦርነት ዙርያ የኢዜማ አመራሮች የሰጡትን ቃለምልልስ FBC ያቀረበው ዘገባ ላይ ይመልከቱ።

https://t.me/fanatelevision/51597
781 viewsedited  04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:04:14
751 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:04:12
688 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:03:45 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እሁድ ነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ምርጫ ክልል፤ ከየምርጫ ክልሉ የተወከሉ አምስት የስራ አስፈጻሚ አባላት በተገኙበት በተመረጡ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት አከናውኗል፡፡

በውይይት መድረኩ፤ የኢዜማ ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ትይዩ ካቢኔ እና የብሔራዊ ምክክር ኮሚቴ የ100 ቀን ዕቅድ እና በጀትን በተመለከተ የተዘጋጀበትን መሰረታዊ እሳቤዎች አብራርተዋል፡፡

ኢዜማ ከመንግስት ጋር ለመስራት በጉባዔ ሲወስን በቀጣይ አትኩሮት ሰጥቼ እሰራባቸዋለሁ ያለውን ሰባት ነጥቦች በተመለከተ የትይዩ ካቢኔ እና የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ እያንዳንዱ ነጥብ ስላለበት ሂደት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና ፖሊሲ ጥናት እና ምርምር መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ዳዊት በለው የመጪውን ሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ግቦችና የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ "ዕቅዱ ሀገራዊ እና ድርጅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት የተዘጋጀ ነው" ብለዋል።

በመጨረሻም የኢዜማ ምክትል መሪ አርክቴክት ዩሐንስ መኮንን በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ የአስተዳደር ወሰን ጉዳይ የተወሰነው ውሳኔ ጋር ተያይዞ የኢዜማን አቋም በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የሀገር ፓለቲካ ስሪቱ መሰረት ዜግነት ላይ እንዲሆን ሁሉም አባል ከልቡ አምኖ ሊሰራ እንደሚገባ ያስገነዘቡ ሲሆን የፓርቲው አባላት ሁሉ የዜግነት ፖለቲካ ምንነት ላይ አንድ አይነት አረዳድ መያዝ ግዴታ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ሁሉም አባል የጉባኤውን ውሳኔ አክብሮ መስራት እንደሚጠበቅበት እና የፓርቲውን ስነምግባር ደንብ በአግባቡ ተረድቶ እና አክብሮ በንቃት መሣተፍ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄዎች አቅርበው ምላሾች የተሰጡ ሲሆን፤ መሰል ውይይቶች በፓርቲው የተለያዩ መዋቅሮች እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
688 views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:21:37
859 views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:09:21 "በድንገት መጥቶ ህዝብን ከሚያጠቃው እኩይ አካል እኩል ዜጋውን የመጠበቅ ግዴታ ኖሮበት የማይጠብቀው መንግስት ተጠያቂ ነው"

የማያባራ ስቃይ፣ የማይረጋጋ ነፍስ፣ ጽልመት የዋጠው የሰቆቃ ኑሮ፣ የማያሳርፍ ጭንቀት ተሸክመው እጅግ መራር ህይወትን እንዲገፉ የተፈረደባቸው ወገኖቻችን ዛሬም የሰው አውሬ ስላገኛቸው እንዲሁም ጠባቂ ስላጡ ልባችን ክፉኛ በሃዘን ተሰብሯል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መንግስት ማንነትን መሰረት አድርገው የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ዜጎችን ከአሰቃቂ ጭፍጨፋ የመጠበቅ መንግስታዊ ግዴታውን እንዲወጣ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ እንዲሁም መፍትሔ ያላቸውን ምክረ ሐሣቦችም ሲያቀርብ ቆይቷል። ሆኖም መንግስት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማሳሰቢያዎችንም ሆነ ምክረ ሀሣቦቻችንን ለመቀበል ምንም አይነት ፍላጎት አላሳየም።

የህግ የበላይነትን የማስከበር ሃላፊነቱም ከዕለት ዕለት ጥያቄ ውስጥ እየገባ መምጣቱ በብርቱ አስግቶናል።

በትናንትናው ዕለት ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በቄለም ወለጋ አካባቢ በንጹሀን ዜጎች ላይ የተለመደ ተመሳሳይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ መፈጸሙ እጅግ አሳዝኖናል።

መንግስት፣ ታጣቂ ሀይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተከትሎ እየሸሹ የነበሩት ታጣቂዎች የፈጸሙት እንደሆነ ገልጿል። መንግስት እንዲህ አይነት እርምጃዎች ሲወሰዱ ታጣቂ ሀይሎች በሽሽት ላይ ምን አይነት ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ የሕወሓት ወራሪ ሃይል ከአማራና ከአፋር ክልል ሲወጣ ከፈጸመው እኩይ ድርጊት በመማር ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ሲገባው ሆነብሎ(በተባባሪነት)/በቸልተኝነት/በተለያዩ በአቅም ማነሶች እንዲሁም የእኩይ ሀይሉ ተባባሪዎች በመንግስት መዋቅር ውስጥ መሰግሰጋቸው እና የዜጎችን ነፍስ ለመታደግ የሚያስችሉ ተግባራትን በቁርጠኝነት ባለመተግበሩ ተጠያቂ ያደርገዋል።

መንግስት በተለይም በወለጋ አካባቢ በዚህ ደረጃ ለምን የጸጥታ ችግሮችን መቆጣጠር እንደተሳነው ለሕዝብ በግልጽ የማሣወቅ ግዴታ ያለበት ከመሆኑም በተጨማሪ ዘላቂ መፍትሔዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት እንዳለበት አጥብቀን ማስገንዘብ እንወዳለን።

ይህ መፍትሄ የጊዜ ገደብ ወጥቶለት አካባቢውን ከመሠል ጥቃቶች በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንደሚያወጣ በይፋ በመግለጽ መንግስት ለዜጎች ደኅንነት መጠበቅ ምን ያህል ቁርጠኛ እንደሆነ እና መንግስታዊ የማስፈጸም አቅም እንዳለው ሊያሳይ ይገባል። ይህን ማድረግ የማይችልና ዛሬም አድበስባሽ ሆኖ መቀጠል ካሰበ አካባቢውን የመቆጣጠር አቅምም ሆነ ፍላጎት እንደሌለው ያሳብቅበታል።

ከመንግስት የደህንነት ክፍተቶች ባሻገር በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች ከአብራካቸው የወጡ፣ አብረዋቸው ለረዥም ጊዜ የኖሩ እና በጋብቻ፣ በባህል፣ በእምነት፣ ወዘተ... የተጋመዱ ወንድምና እህት ዜጎችን የመኖር መብት ለማስከበር አብረው በመቆም፤ ከዚህ አይነቱ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በመከላከል ሰብዓዊ እና ኢትዮጵያዊ እሴቶችን እንዲያስቀጥሉ እንዲሁም በማህበረሰብ መካከል የተፈጠረ ጥላቻ እንዳልሆነና ደም የጠማቸው ግፈኞች እኩይ ተግባር መሆኑን በተግባር እንዲያሳዩ አበክረን እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ፓርቲያችን አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በቅርብ በዚህ እና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አቋም በስፋት ያሳውቃል፡፡

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
1.1K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:09:18
867 views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 00:26:20
የኢዜማ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው የአመራሮች ምርጫ ዶ/ር ጫኔ ከበደን እና ዶ/ር አማኑኤል ኤርሞን የኢዜማ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡

ሰኔ 26፣2014 ዓ.ም
#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
1.3K views21:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 00:25:56
የኢዜማ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ምርጫ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን እና አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንንየኢዜማ መሪ እና ምክትል መሪ አድርጎ መርጧል፡፡

ሰኔ 26፣ 2014 ዓ.ም
#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
1.2K views21:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ