Get Mystery Box with random crypto!

#የኮቪድ19_በሽታ_የየቀኑ_ምልክቶች ከ1-3 ቀን • በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን | ኢትዮጵ(ትግ)

#የኮቪድ19_በሽታ_የየቀኑ_ምልክቶች

ከ1-3 ቀን
• በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን መሰል ሆኖ ቀለል ያለ ትኩሳት እና
ጉሮሮ ህመም ብቻ ሲኖር የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ጥሩ ነው ።
• የሰውነት መከላከያ ደከም ያለባቸው ስዎች ቀለል ያለ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽ
ሊኖራቸው ይችላል ።

በ 4 ኛው ቀን
• የጉሮው ህመም ይጨምራል እንደዚሁም የድምፅ መወፈር ይኖራል ።
• ብዙ ጊዜ ትኩሳት አይኖርም 36.5 degree ብቻ ይሆናል
• ቀለል ያለ እራስ ምታት እና የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ሊስተገዋጎል ይችላል ።

በ 5 ኛው ቀን
• ስሜቶች የበለጠ ይጨምራሉ ፦ የጉሮሮ ህመም ይጨምራል ፣ ድምፅ የበለጠ
ይጎረንናል ።
• በእንቅስቃሴ ወቅት የስውነት ህመምና ቁርጥማት ይኖራል ፤ የሰውነት ድካም ይኖራል ።

በ 6 ኛው ቀን
• ትኩሳት ይጀምራል
• ደረቅ ሳል ከጉሮሮ ህመም ጋር ይበረታል
• ምግብ በመመገብ ፣ የሚጠጣ ነገር ሲወስድ እንደዚሁም በንግግር ጊዜ የጉሮሮ
ህመም ይኖራል ።
• ተቅማጥና ማቅለሽለሽ የበለጠ ይጨምራል ።

በ 7 ኛው ቀን
• ትኩሳት ከ 38 ድግሪ በላይ ይሆናል
• ደረቅ ሳል ይኖራል ፣ ይጨምራል
• የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ፣ ተቅማጥና ማቅለሽለሽ ይጨምራል ።

በ 8 ኛው ቀን
• መተንፈስ መቸገር
• የደረት መክበድና ህመም
• ደረቅ ሳል ይኖራልም ይጨምራልም
• የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ይቀጥላልም በጣም ይጨምራል ።
• ትኩሳት ይቀጥላል ፣ ይጨምራል

በ 9 ኛው ቀን እና በሚቀጥሉት ቀናት
• ሁልም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በጣም ይጨምራሉ ።

ምንጭ፦ የአለም የጤና ድርጅት ድሕረ ገጽ

@Yottor_3

#Share