Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethopoeia — ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethopoeia — ኢትዮ-አዲስ መረጃ -NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethopoeia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 704
የሰርጥ መግለጫ

🇪🇹ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።
🇪🇹 ሼር በማድረግ ትክክለኛ መረጃ ከምንጩ ያግኙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-31 21:20:39
አልሸባብ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ መሳሪያዎች በምስራቅ ጀግኖች ተማርኮ ገቢ ሆኗል!
23 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 21:20:39
የሶሜሌ ክል ልዩ ሀይል መከላክያ ሰራዊት ሱማልያ ውስጥ ዘልቆ በመግባት እርምጃ እየተወሰደበት ያለው የአልሸባብ ቡድን ምስል 1
22 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 19:16:05
የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በረካታ የጦር መሣሪያዎችን ከአልሸባብ የማረከ ሲሆን በምሰሉ ላይ የምትመለከቱት ሁለቱ የቡዱን መሣሪያዎች በዛሬው ኦፕሬሽን ከአሸባሪው አልሸባብ በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል የተማረኩ የቡዱን ማሳሪያዎች ናቸው::
33 views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:26:46 የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌሮች

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሁለገብነትን ተከትሎ ዘርፉን ለማበልፀግና ብዙኃንን ተሳታፊ ለማድረግ ተቋማት እና ግለሰቦች የቴክኖሎጂውን ሶፍትዌሮችን በነጻ ያቀርባሉ፡፡ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከሚገኙት መካከል ሁለቱን ለዛሬ እናስተዋውቃችሁ፡፡

1.ቴንሰርፍሎው/ TensorFlow
ይህ ሶፍትዌር የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን ለማሰልጠን እና ለማበልፀግ በስፋት ግልጋሎት ላይ ይውላል፡፡ በተጨማሪም ዳታዎችን በማጠናቀር የትንበያ መላምቶችን ለማዘጋጀት የላቀ አቅም ያላቸው ቁጥርን ማስላት የሚያስችሉ ክምችቶችን ይዟል፡፡

ቴንሰርፍሎው ድምፅን እና ምስሎችን ለሚለዩ የተለያዩ መተግበሪያዎች የጀርባ አጥንት መሆኑ ይነገራል፡፡
ድሮፕቦክስ፣ ኢቤይ፣ ትዊተር፣ ኡበር እና ኢንቴልን የመሳሰሉ ትላልቅ ተቋማት ሳይቀሩ ይህንን ሶፍትዌር ጥቅም ላይ በማዋል ይታወቃሉ፡፡

2. አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን / IBM Watson
አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን በተቋማት የሚደረጉ ጥናት እና ምርምሮችን እንዲሁም ግኝቶችን ለማፋጠን የተሻለ አቅምን መፍጠር እንደሚችል ይነገርለታል፡፡ ብዙ ተቋማት ሶፍትዌሩ የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ዳታቸውን ለማጥናት፣ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለማሰባሰብ፣ ስለ ስራቸው ጥልቅ እይታን ለማግኘት እና ቀጣይ የስራ አፈጻጸማቸውን በቀላሉ ለመተንበይ አገልግሎት ላይ ያውሉታል፡፡

በትምህርት፣ በጤና ጥበቃ፣ በፋይናንስ፣ በትራንስፖርት እንዲሁም በኃይል ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት ሶፍትዌሩን አገልግሎት ላይ በማዋል ውጤት አግኝተውበታል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ሶፍትዌር በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል የዘርፉ ምሁራን ይጠቁማሉ፡፡


https://t.me/ETHOPOEIA
38 viewsedited  15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:24:09 " የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው " - የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምርኮኞችን አያያዝ ባልጠበቀ መንገድ ወታደሮቼን ገድሏል በሚል የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው እንዳልነበርና #የኢትዮጵያን_ግዛት_ዘልቆ የገባው የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር መጋጨቱ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ሕወሓት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ወረራ መፈጸሙን አስታውሶ፤ ጦሩ በተለያየ ጊዜ ውስጣዊ ችግሮች ባጋጠሙ ቁጥር በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ሰሞኑ ደግሞ የሱዳን ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት በአካባቢው በነበሩ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ላይ ጥቃት ማድረሱንና ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱን ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ነገር ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በስፍራው ባልነበረበት ሁኔታ " ምርኮኞችን ገደለ " በሚል የሱዳን ጦር ክስ ማቅረቡ ተቀባይነት የሌለውና መሰረተ ቢስ መሆኑ አስገንዝቧል።

የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ማጣራት የሚፈልግ አካል ካለ ከሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንዲጣራ ለመተባበር የኢትዮጵያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አረጋግጣል።
39 views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 00:10:06 በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር … የቦታው ስፋት በሰነድ 329.28 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 774,560 መሆኑ ታውቆ ሰኔ 24 ቀን 2004 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡

Deadline: ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ/ም (2022-07-01)

አዲስ ዘመን ረቡዕ ሚያዝያ 26 ቀን 2014 ዓ . ም

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ አቶ መለሰ ዘለቀ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ንጋቱ ዘለቀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/121474፤ 126200_በ29/10/2013 ዓም እና በዘ/06/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር 123 በካ/ቁ/ወ8/ ወ7/01/641/15021/00 በእነ አበራሽ ታፈሰ ስም የተመዘገበ የቦታው ስፋት በሰነድ 329.28 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 774,560 (ሰባት መቶ ሰባ አራት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ብር) የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5 ፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል ፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጎድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

https://t.me/ETHOPOEIA


የኢትዮጵያ ጨረታዎች የመረጃ ምንጭ
1.0K views21:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:26:17 #Update #ችሎት

ፍርድ ቤት በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለግንቦት 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አመልካች የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍና በተጠሪ ብርጋዴል ጄኔራል ተፈራ ማሞ መካከል በነበረው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ሀሳብ አዳምጧል።

ፍርድ ቤቱም ፤ ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 10 ቀን በመፍቀድ ለግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጠበቃ አቶ ሸጋው አለበል ብርጋዴር ጀነራሉ " ህገ መንገስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል " በሚል ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አሳውቀዋል።

tikvahethiopia
434 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:20:30 10ft, 20ft, 30ft , 40 & 50ft Containers Available. They are all solid wind & Watertight, CSC plated and available in the following types : Standard or General purpose Container , Side Opening, High Cube , Tunnel or Double Door shipping container with open top . All with multiple air vents . With inventory stretching from coast to coast and delivery available in all major cities In USA , CANADA , UK etc . We can meet any storage need . For more vital details with prices kindly Pm me at https://t.me/shippingcontainers20ft40ft
409 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:20:30 ማንኛውም የዕቃ መጫኛ ኮንቲነሮች እኛ ጋር ያገኛሉ።0912328745/0900480054 መነጋገር ትችላላችሁ እና ወደ ማንኛውም ሀገር መላክ እና ማስመጣት እቃዎችን ቀጥታ በአጭር ጊዜ ፕሮሰሱን እናማክራለን መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ።
343 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 19:04:49 " አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ " - የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሃይሌ ተናግረዋል፡፡

መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሚፈጽሙ የመንግስት ሰራተኞችም ሆነ ሃላፊዎችን ተጠያቂ በማድረጉም ሆነ ባለማድረጉ ፣ ከህዝብ የበለጠ ተጎጂ ስለሆነ ተጥያቂነት ማንበር እንደሚገባው በአፅንኦት ተናግረዋል።

ሃላፊው ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተገኝተው ለህግ ፣ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ 10 ወራት የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት ፡፡

ዋና ዕንባ ጠባቂው ከቋሚ ኮሚቴ አባላት በኩል ከተጠያቂነት አንጻር ለተነሳላቸዉ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ መመረጥ እና በስልጣን ላይ መቆየት የሚፈልግ ከሆነ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ሰራተኞች እና ሃላፊዎች ላይ እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባውና ጠቀሜታው ለራሱ እንደሆነ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

በተያያዘም ዶ/ር እንዳለ " እኛ እንደ አንድ ዴሞክራሲ ተቋም እንዲሁም የተከበረዉ ምክርቤት ማድረግ የሚችለዉ ነገር ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል ህግ እና ደንብ እንዲሁም ስርዓት፣ መመሪያ ወይም አዋጆችን ማዉጣት ነዉ፤ ከዛ ባለፈ የወጡ አዋጆችን ወይም ደንቦችን የመፈጸም ሃላፊነት ያለበት ግን የመንግስት አስፈጻሚ አካል ነዉ "ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በነዚህ ምክረሃሳቦች ላይ መግባባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በማንሳት መግባባት ከሌለ ግን ምክር ቤቱ ብዙ ህግ ቢያወጣ ፤ የዴሞክራሲ ተቋማት ምክረሃሳቦችን ቢሰጡ እና መፈጸም ባይችሉ ፤ መንግስት ተጎጂ እሆናለዉ ብሎ በማሰብ የበለጠ ቢሰራ የተሻለ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

https://t.me/ETHOPOEIA
418 views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ