Get Mystery Box with random crypto!

የፖሊስ መልዕክት ! የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማ | መረጃ//mergaa

የፖሊስ መልዕክት !

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ የሰጡት ቃል ፦

" ምንም በማያውቁት ጉዳይ በህጻናቱ ላይ የተፈጸመው ይህ አሰቃቂ ወንጀል ሁሉንም በእጅጉ አሳዝኗል።

ወላጆች የሚቀጥሯቸው የቤት ሠራተኞችን ማንነት ጠንቅቀው ማወቅ ይገባቸዋል።

እንደ ቤተሰብ ሆነው የሚኖሩ የቤት ሠራተኞች እንዳሉ ሁሉ እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል የሚፈጽሙም ስላሉ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። "

#ተጨማሪ መረጃ ፦

• በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ሁለት ታዳጊ ልጆቻቸውን ያጡት ወላጆች በከባድ ሐዘን ውስጥ ይገኛሉ።

• ወንጀሉ በተፈጸመበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችም በእጅጉ ተረብሸው ነው የሚገኙት።

• ፖሊስ በወንጀሉ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ነው።

- ተጠርጣሪዋ ህጻናቱን አንቃ እና ስለት ተጠቅማ በአስቃቂ ሁኔታ መግድሏ የሚያመላክቱ መላምቶች አሉ።

- ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳት ወይም የአእምሮ ጤና ችግር እንዳለበት ለማወቅ ምርመራዎች እየተካሄዱ ነው።

- በወንጀሉ የተጠርጠረችው ግለሰብ በቤት ሠራተኛነት ግድያው ለተፈጸመበት ቤተሰብ ስታገለግል ቆይታለች።

• ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው ወላጆች የሌሉበትን ሰዓት ጠብቃ ነው።

መረጃው ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ ከሰጡት ቃል የተወሰደ ነድ።