Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሩሲያ ጦርነትን ጨምሮ በትልልቅ ጉዳዮች ላይ በመጠመዱ እንዲሁም በ | መረጃ//mergaa

የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሩሲያ ጦርነትን ጨምሮ በትልልቅ ጉዳዮች ላይ በመጠመዱ እንዲሁም በፌዴራል መንግሥት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ በሰንካላ ምክንያት በማጓተቱ ዓለም ቸል ያለውና ትኩረት የነፈገው ህወሓት ጉዳዩ ሲያብሰከስከው ከርሟል፡፡ እናም ድጋሚ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አጀንዳ ለመሆን በተለያዩ ግንባሮች የማያሸንፈውን ጦርነት ለኮሱ እየተለበለበ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአሸባሪው የውጭ ክንፍ አስተባበሪ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ትኩረት ተነፍጎት የነበረው ህወሓት ዳግም እንዲያንሰራራ ከተሠጠው ሐላፊነት ውጪ በመላው ዓለም የቡድኑን ተልዕኮና አጀንዳ ማስፈጸም ዋናው ተግባሩ አድርጎታል።

የአሸባሪ ቡድኑ ቀደም ሲል ወደ ትግራይ የሚጓጓዘውን የሰብአዊ እርዳታ በማስተጓጎልና ለሕዝብ የተመደበ የሰብአዊ እርዳታን ለጦርነት እንዲውል በማድረግ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ሆኖ ሳለ የዓለም አቀፍ የግንኙነት መረቡን በመጠቀም አሳሳች መረጃዎችን እያሰራጨ ይገኛል።

በቅርቡ እንኳን በኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበለትን የሰላም ድርድር ወደ ጎን በመተው በተለያዩ ግንባሮች ወረራ ቢፈጽምም፤ የቡድኑ ቃል አቀባይ በራሱ ሚዲያ ወጥቶ ጦርነት ውስጥ የገባነው መንግሥት የከፈተብንን ጥቃት ለመመከት ነው ብሏል፡፡ የመከላከል ጦርነት ላይ ነን በሚል አንድም የትግራይ ሕዝብን ሁለትም የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አደናግሮ እራሱን እንደተጠቃ በማድረግ የዓለምን ትኩረት ለመሳብም ሲፍጨረጨር ይታያታል።

ይህን የቃል አቀባዩን ሥራ ለማሰካትም ይመስላል የአሸባሪው ቡድን ደጋፊዎች አቋርጠው የነበሩትን የመንከባለል ትርኢታቸውን (እምቦር ተንከብላይነት) በአሜሪካና አውሮፓ ከተሞች ማሳየት ጀምረዋል።