Get Mystery Box with random crypto!

የወልድያ ከተማ ሕዝብ ለወገን ጦር የሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። አማራ ሚዲያ | መረጃ//mergaa

የወልድያ ከተማ ሕዝብ ለወገን ጦር የሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ያነጋገራቸው የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ለጀግኖቹ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለፋኖ እና ለሚሊሻ በያሉበት ግንባር የምግብና የውኃ አቅርቦት እያደረሱ ነው።

አስተያየት ሰጪዎቹ ጀግኖቹ የወገን ጦር አባላት የኢትዮጵያን ጠላት እያርበደበዱ ባሉበት በዚህ ወቅት እኛ የምናደርገው ድጋፍ እጅግ ቀላሉ ነው ብለዋል። እናም የበለጠ እና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሶሪያውያን ሀገር ቢያጡ በመላው ዓለም ተበትነዋል ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፤ ኢትዮጵያ እንድትኖር ስለምንፈልግ ሁሉንም መስዋዕትነት እንከፍላለን ብለዋል። ስለዚህ መላው ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላት ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ተሳታፊ እንዲሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ደምስ አለባቸው፤ የወልድያ ከተማ ሕዝብ በየቀበሌው እና በየመንደሩ ተደራጅቶ ለፀጥታ ኀይሉ ሁሉን አቀፍ እና የተጠናከረ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነግረውናል፡፡ ነዋሪው ትኩስ ምግቦችን ጭምር ግንባር ድረስ እያቀረበ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

አቶ ደምስ ሕዝቡ የደጀንነት ተግባሩን በሚገባ እየተወጣ ነው፤ ለወገን ጦር
እየሰጠውም ያለው ድጋፍ አስደሳች ነው ብለዋል።