Get Mystery Box with random crypto!

ድንቅ የበረከት ልጅ ይችን ድንቅ ብላቴና ሎዛ ትባላለች በትምህርቱዋ እጅግ ድንቅ ብቃት በማስመዝ | የተዋሕዶ መረጃ

ድንቅ የበረከት ልጅ
ይችን ድንቅ ብላቴና ሎዛ ትባላለች በትምህርቱዋ እጅግ ድንቅ ብቃት በማስመዝገቡዋ የ 10 ሽ ዶላር ሽልማት ትምህርት ቤቱዋ ይሸልማታል ልበ በርሀኑዋ ሎዛ በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች እየዞሩ ለፈረሰችው ወልድያ እና ላሊበላ ገንዘብ እየሰበሰቡ ለሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ቃል ገብታ ሰነበተች

ታዲያ ዛሬ በቅዱስ ገብርኤል ዲሲ የተገኙት ብጽእነታች እዚህም በመሰብሰብ ላይ እያሉ ይች ትንሽየ ብላቴና ካለኝ ላይ ቀንሸ ሳይሆን የተሸለምኩትን ሙሉ ብር ይሄው እውቀቱን የሰጠኝ አምላክ ነው እሱ የሰጠኝን ለሱ ብላ ሙሉውን ሰጠች።

እንዴት መባረክ መመረጥ ነው የዘመኑ ሰው እንኩዋን ያለውን ካለው ላይ ማካፈል በማይፈልግበት በዚህ ዘመን ልበ ብርሀኑዋ ሎዛ ሙሉ የሽልማት ገንዘቡዋን ለግሳለች 10$ዶላር አሜሪካ ላይ ትልቅ ገንዘብ ነው ።ይህ ለኛ ንፍጎቹ ትልቅ ትምህርት ነው

እባካችሁ ሎዛን መርቁልኝ ከዚህ በላይ እውቀቱን ያድልሽ በሉልኝ ተባረኪ እህቴ
ለወቅታዊ መረጃ በቴሌግራም
https://t.me/ethomereja/3725?single
ይቀላቀሉ