Get Mystery Box with random crypto!

መልአከ ምህረት ሐመልማል አሰፋ የአቃቂ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ!!! ነሐሴ | የተዋሕዶ መረጃ

መልአከ ምህረት ሐመልማል አሰፋ
የአቃቂ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ!!!
ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም
********************************************************
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የአቃቂ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ በነበሩት በመልአከ ፀሐይ ኃይለ ሚካኤል አድኃኖም ምትክ የሀገረ ስብከታችን የእስታስቲክስ ክፍል ኃላፊ የነበሩ መ/ምህረት ሐመልማል አሰፋ የአቃቂ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መልካም ፍቃድ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመልአከ ምህረት አባ ገ/መድህን ንጉሴ ተሹመዋል።
ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ልዑካን፣የወረዳ ሊቃነ ካህናት፣የአቃቂ ወረዳ ቤ/ክ/ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቃነ መናብርት፣የጽ/ቤት ሠራተኞች በተገኙበት
ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ለክብር መ/ም ሐመልማል አሰፋ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።