Get Mystery Box with random crypto!

“ አማራን የማንገላታት፣ የማሳቀቅ፣ ከከተማው የማራቅ እና አለፍ ሲልም የማገት ፓለቲካ በአስቸኳይ | ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹

“ አማራን የማንገላታት፣ የማሳቀቅ፣ ከከተማው የማራቅ እና አለፍ ሲልም የማገት ፓለቲካ በአስቸኳይ መቆም አለበት” ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙ መንገደኞች ላይ ባለፉት ጥቂት ቀናት የተፈጠረው የሰላማዊ መንገደኞችን ጉዞ ማስተጓጎል፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሰበብ አስባቡ አማራውን ማንገላታት እና ማገት ወዘተ ... የተጓዦችን በነፃነት የመንቀሳቀስ እና በፈለጉት የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሶ ሰርቶ የመኖር መሰረታዊ ሰብዓዊ መብትን የሚገድብ ግልጽ የሆነ የህግና ተደራራቢ የመብቶች ጥሰት ነው።

ድርጊቱ «ወንጀለኞች ወደ ከተማይቱ ሰርገው ገብተው ጥቃት እንዳይፈጽሙ ለመከላከል የሚደረግ ቅድመ ጥንቃቄ ርምጃ ነው» በሚል ሰበብ አማራን የማንገላታት፣ የማሳቀቅ፣ ከከተማው የማራቅ እና አለፍ ሲልም የማገት ፓለቲካ ሲሆን፣ ይሄንን እገታ በማን አለብኝነት የሚፈጽሙት አካላት ከዚህ ሀላፊነት የጎደለው የእብደት ድርጊታቸው ባስቸኳይ ሀይ ካልተባሉ ውሎ አድሮ የከፋ ችግር መፈጠሩ አይቀርም።

ይህ እብደት ዛሬ፣ ነገ ሳይባል በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል። ይሄንን የአገርን ሰላም ለማደፍረስ ታስቦበት በሚመስል መንገድ እየተሰራ ያለ ህገወጥ የወንጀል ድርጊት ምንም አይነት አመክንዮ እና የህግ መሰረት የሌለው፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ሊያወግዘው የሚገባ ተግባር ነው።

ድርጊቱን በአስቸኳይ ማስቆም ያለበት በዋነኝነት የፌደራል መንግስቱ ሲሆን፣ በፌደራል መንግስቱ ውስጥ በአማራ ስም ስልጣን ይዛችሁ ያላችሁ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ድኤታዎች፣ በተለይም ም/ጠ/ሚ/ሩ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ ሚ/ሯና ሌሎች ሚኒስትሮች ሀላፊነታችሁን በአግባቡ ባለመወጣታችሁ በህግ ተጠያቂ ባትሆኑ እንኳን በታሪክ ተጠያቂነት እንዳለባችሁ ልናሳስባችሁ ግዴታ አለብን። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ም/ር/ መስተዳድሮች፣ የካቢኔ አባላት እና የዞን አስተዳዳሪዎች እና የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላትም በተመሳሳይ።

የችግሩ ግዝፈት አንገታችሁን እንደሰጎን አሸዋ ውስጥ ቀብራችሁ፣ አላየንም አልሰማንም ብላችሁ ልታልፉት አትችሉም። ይሄንን የለየለት አገር አፍራሽ ድርጊት ከማስቆም በተጨማሪ በይፋ ወጥታችሁ ማውገዝና ተጠያቂ የሆኑ የኦሮሞ ክልል ባለስልጣናት ተጠያቂ እንዲደረጉ በይፋ መጠየቅ አለባችሁ። መቼም ይህን ጉዳይ እንደቀላል ነገር ትቆጥሩታላችሁ ብየ በግሌ አልጠብቅም። አገርን ወደ አለመረጋጋት ሊመራ የሚችል ከባድ ጉዳይ እንደሆነ ፈጽሞ አትስቱትም።

የአማራ ሕዝብ ለእገታ ፓለቲካ አራማጅ ሃይሎች ፈጽሞ አይንበረከክም። አማራን በዋና ከተማው አዲስ አበባ ሙሉ የባለቤት መብት፣ ሰርቶ ከመኖር፣ ለንግድ ለስራ፣ ለህክምና፣ ለማንኛውም ማህበረ ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች በፈለገው ጊዜ ከመውጣት እና ከመግባት የሚከለክለው አንዳችም ሀይል እንደሌለም ሊሰመርበት ይገባል።

https://t.me/ETHIOZENA24