Get Mystery Box with random crypto!

'እንደ አሁኑ አይነት ዘረኝነት አላየሁም። ከሀገሬና ከተቋሜ በማንነቴ ምክንያት ተሰድጃለሁ' ጋዜጠኛ | ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹

"እንደ አሁኑ አይነት ዘረኝነት አላየሁም። ከሀገሬና ከተቋሜ በማንነቴ ምክንያት ተሰድጃለሁ" ጋዜጠኛ እማዋይሽ ግርማ

ሁሉ ነገር ተጨመላልቋል። አይን ያፈጠጠ ዘረኝነት ነው ያለው። እኔ በሁለቱም ሰርዓት ሰርቻለሁ። እንደ አሁኑ አይነት ዘረኝነት ግን አላየሁም። በአጠቃላይ ETV የሀገሪቱን ምስቅልቅል ፖለቲካ ይመስላል።

በግሌ ለ10 አመት ከሰራሁበት ETV በማንነቴ ተገፍቻለሁ። ሌሎችም በማንነታቸው ተገፍተዋል። ችሎታ ሳይሆን ማንነት ተቆጥሮ የማይመጥነን ቦታ ተመድበናል። ሀላፊዎቻችን ETV ን እየመሩ የማህበራዊ ሚዲያ ኘሮፋይላቸው ግን የOBN ጋዜጠኛ ነው የሚለው።

ፈጣሪ ካልታከለበት የሚመጣ ለውጥ ያለ አይመስለኝም። ነገሮች እየተወሳሰቡ ሄደዋል። በሀገሬ ተስፋ ቆርጫለሁ። በተቋሜ ተስፋ ቆርጫለሁ። በዚህም ለስልጠና በሄድኩበት ሀገረ ኔዘርላድ ጥገኝነት ጠይቄ ቀረቻለሁ። ከሀገሬና ከተቋሜ በማንነቴ ተሰድጃለሁ።

እማዋይሽ ግርማ - የETV ጋዜጠኛ የነበረች